Google search engine

“በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ተሳትፎአችን ዘላቂና ረጅም ጉዞን አልመናል” አምሳሉ ጥላሁን /ፋሲል ከነማ/

የአፍሪካ ቶታል ቻምፒዮንስ ሊግ እና
የኮንፌዴሬሽን ካፕ ጨዋታዎች ከትናንት
አንስቶ በመከናወን ላይ ሲሆኑ ግጥሚያዎቹም
ዛሬና ነገ እሁድ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት
ሜዳዎች ላይ የሚካሄዱ ይሆናል፤ በእነዚህም
ውድድሮች አገራችን ሁለት ክለቦቿን
የምታሳትፍ ሲሆን በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ
ውድድር መቐለ 70 እንደርታ የፕሪምየር ሊጉ
ሻምፒዮና በመሆኑ የኢኳቶሪያል ጊኒ ካኖ ክለብን
ከሜዳው ውጪ ይፋለማል፤ ለእዚህም
ጨዋታው ወደ ስፍራው ተጉዟል፡፡ ሌላው
የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ አሸናፊ የሆነው ፋሲል
ከነማ ደግሞ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ላይ
የመጀመሪያ ጨዋታውን ከታንዛኒያው አዛም
ክለብ ጋር የሚፋለም ሲሆን ይሄም ጨዋታ
ነገ እሁድ በባህርዳር ስታዲየም የሚካሄድ
ይሆናል፡፡
ፋሲል ከነማ የታንዛኒያውን አዛም
ስለሚፋለምበት ጨዋታና ስላደረገው ዝግጅት
እንደዚሁም ደግሞ ከግጥሚያው ሊያመጣ
ስላሰበው ውጤት ለቡድኑ ጠንካራ የግራ
መስመር ተከላካይና የኮሪደር ስፍራ ተጨዋች
ለሆነው አምሳሉ ጥላሁን /ሳኛ/ ጥያቄዎችን
አቅርበንለት ምላሾቹን ሰጥቶናል፡፡
የታንዛኒያውን አዛም ለመፋለም እያደረጉ
ስላሉት ዝግጅት
“የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የመጀመሪያ
ጨዋታችንን ከታንዛኒያው አዛም ክለብ ጋር
ለማድረግ እስካሁን ስንሰራው የነበረው
ዝግጅትና ልምምድ በጣም ጥሩ ሲሆን የአሁን
ሰዓት ላይም ለብሄራዊ ቡድን ተመርጠን
የነበርነው አራት ተጨዋቾችም ካለፉት አራትና
አምስት ቀናቶች ወዲህ ስኳዱን በመቀላቀል
የተሟላ ልምምድን እንደ ቡድን በመስራት
ላይም ነው የምንገኘው፤ ከዛ ውጪም ቡድናችን
ለእዚህ ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶትም
የጨዋታውን የመጀመሪያ ሰዓት በመጠባባቅም
ላይ ይገኛል”፡፡
ለፋሲል ከነማ የመጀመሪያው
ኢንተርናሽናል ግጥሚያው ስለመሆኑና
ስለሚያመጣው ውጤት
“የታንዛኒያውን አዛም የምንገጥምበት
የነገው የእሁድ ጨዋታ የመጀመሪያነቱ ለእኛ
ብቻ ሳይሆን ለክልላችንም ነው፤ ፋሲል ከነማ
ደግሞ ይሄን የመጀመሪያ የኢንተርናሽናል
ጨዋታ ተሳትፎ ማግኘት መቻሉ ቡድኑ ምን
ያህል ጠንካራ ክለብ እንደሆነ ያመላከተም
ሆኗልና ከአዛም ጋር የምናደርገውን
ጨዋታ በሜዳችን እዚህ ግብ ሳናስተናግድ
አሸንፈን ለመውጣት ተዘጋጅተናል፤ ደግሞም
ጨዋታውን አሸንፈን እንደምንወጣም እርግጠኛ
ነኝ”፡፡
ስለተጋጣሚያቸው አዛም ክለብ መረጃን
አግኝተው ስለመሆናቸው
“የእሁዱ ተጋጣሚያችን ስለሆነው
የአዛም ክለብ የጨዋታ እንቅስቃሴን የሚገልፅ
የቪዲዮ መረጃን አግኝተን እየተመለከትን
ይገኛል፤ ክፍተቶቻቸውንም በማየት ላይ ነንና
ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ግጥሚያችንን
እናደርጋለን”፡፡
በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የውድድር
ተሳትፎ ፋሲል ከነማ የት ድረስ ለመጓዝ
አልሟል?
“ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ
የውድድር ተሳትፎው ዋንኛው እልሙና ግቡ
በእዚህ ውድድር ላይ ረጅምና ዘላቂ የሆነን
ጉዞ ማድረግ ሲሆን ከዛ ውጪ ሌላ ነገርን
አያስብም፡፡ በአፍሪካ ክለቦች የውድድር ተሳትፎ
ታሪክ አሁን አሁን ላይ የሀገራችን ቡድኖች
በመጀመሪያው ዙር ላይ ሲሰናበቱ አይተናል፤
ይሄ ውጤት በእኛ ቡድን ላይ እንዲደገም
አንፈቅድምና የፋሲል የውድድር ጉዞው ዘላቂ
የሆነ ነገርን ማግኘት መቻል ነው”፡፡
የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች የእሁዱን
ጨዋታ በምን መልኩ እየጠበቁት እንደሆነ
“የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች የታንዛኒያውን
አዛም ለምንፋለምበት የነገው ጨዋታ ከሐሙስ
ጀምሮ ባህር ዳር ገብተው ግጥሚያውን
በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቁት የሚገኝ ሲሆን
እነዚህም ደጋፊዎች በጨዋታው ላይ
እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ አስገራሚ የሆነ
ድጋፋቸውን ሊሰጡንም ተዘጋጅተዋል፤ እኛም
እነሱን በውጤት ልናስደስታቸው በሁሉም
መልኩ ተዘጋጅተናል”፡፡
ፋሲል ከነማን ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ
ስላበቃው የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የዋንጫ
ጨዋታ
“ፋሲል ከነማ ሐዋሳ ከተማን በማሸነፍ
ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ስላለፈበት
የፍፃሜ ጨዋታ አሁን ላይ በድጋሚ ማለት
የምፈልገው ያን ዕለት ጨዋታውን ያደረግነው
የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ አስቀድሞ በበደልና
ግፍ ተፈፅሞብን ያለ አግባብ አጥተን ስለነበርና
አሁንም ይህን ዋንጫ ማጣት ስለሌለብን
ውስጣችን ተወጥሮ ነበር ግጥሚያውን
ያከናወንነው፤ ያም ሆኖ ግን የፍፃሜውን
ጨዋታ በጭንቀት ማድረግ የቻልን ቢሆንም
በመጨረሻ በፍፁም ቅጣት ምት በማሸነፍ
የዋንጫው ባለቤት ለመሆን ችለን ሀገራችንን
በአፍሪካ የኮንፌዴሬሽን ካፕ የውድድር መድረክ
ላይ ልንወክል ችለናል፤ ከዛ ውጪም ከሜዳችን
ባሻገር የተለያዩ የክልል ከተማ ስታዲየሞች ላይ
በመገኘት በድንቅ ሁኔታ እኛን የሚደግፉንን
ደጋፊዎቻችንን ልናስደስታቸውና ውጤቱም
ለእነሱ ሲያንሳቸው እንጂ የሚበዛባቸው
እንዳልሆነም ልናረጋግጥላቸውም ችለናል”፡፡
በመጨረሻ
“ጠብቁን፤
“ጠብቁን፤ የእሁዱን ጨዋታ ከፈጣሪ
እርዳታ ጋር እናሸንፋለን”::

PHOTO CREDIT – KZG

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P