Google search engine

“በአፍሪካ ዋንጫው እንደ ሞሮኮ ምርጥ ቡድንን አላየሁም፤ በመጀመሪያው ጨዋታ እኛም ጎዶሎ ሆነን መጫወታችን ጎዳን እንጂ መጥፎ የምንባል አልነበርንም” ሀይሌ ገብረትንሳይ /ኢትዮጵያ ቡና/

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን /ዋልያዎቹ/ በካሜሩን አስተናጋጅነት እየተደረገ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታው ኬፕቨርዴን በመጀመሪያው ጨዋታ ገጥሞ 1-0 በሆነ ውጤት የተሸነፈ ሲሆን ይህን የዋልያዎቹን ጨዋታ አስመልክቶና ስለ ራሱ እንደዚሁም ደግሞ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ስለሚጫወትበት ክለብ ኢትዮጵያ ቡና አጠር ያሉ ጥያቄዎችን ለሀይሌ ገብረትንሳይ አቅርበንለት የሚከተለውን ምላሾቹን ሰጥቶናል፤ ቃለ-ምልልሱም በሚከተለው መልኩ ቀርቧል፡፡

በአፍሪካ ዋንጫው ብሔራዊ ቡድናችን ከኬፕቨርዴ ጋር ስላደረገው የመጀመሪያ ጨዋታው

“እንደ መጀመሪያ ጨዋታችን ቡድናችንን ስመለከተው ያሬድ ባየህ በጊዜ በቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣቱ ያቀድነውን የጨዋታ ታክቲክ እንዳንተገብር አደረገን እንጂ ያንን ያህል መጥፎ የምንባል አልነበርንም፤ ያሬድ በጊዜ ከመውጣቱ በፊት ጥሩ መንቀሳቀስ ጀምረን ነበር፤ የእሱ መውጣት በእግር ኳስ አንድ ሰው አይደለም በቀይ ካርድ በጉዳት እንኳን ሲያርፍብህ በውጤትህ ላይ ተፅህኖን ያመጣልና ያ መሆን መቻሉ በጣም ጎድቶናል፤ ከዛ ውጪ ሌላም ቡድናችን ሊያሻሻል የሚገባው ነገር አለና ያን ካሟላ በጣም ጥሩ ብቃቱን ሊያሳየን ይችላል”፡፡

ከመጀመሪያ ጨዋታ በመነሳት ዋልያዎቹ ሊያሻሽሉት የሚገባው

“ኳስን በመቆጣጠሩና በማንሸራሸሩ ላይ ጥሩ ጎን እንዳለን ይታወቃል፤ ያም ሆኖ ግን ኳሱን ወደፊት እያስኬድን አንጫወተውም፤ ይህን ልናሻሽለው ይገባል”፡፡

የአፍሪካ ዋንጫውን እንደ አጠቃላይ ሲመለከተው

“በአፍሪካ ዋንጫው እስካሁን የተደረጉትን አብዛኛውን ጨዋታዎች ስመለከታቸው ጉልበት ላይ ያተኮረና ጥለዛም የበዛበት ነው፤ ጎልም በቀላሉ አይገባም፤ የጎል ድርቅም እየታየ ነው፤ በአጨዋወት ደረጃ የእኛ ቡድን ረጋ ብሎ ስለሚጫወት ጥሩ ነገርን ተመልክቼበታለው፤ ከሁሉም በተሻለ ደግሞ አስቀድሞ ባይጠበቁም የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድንን እንደ ቡድን ስለሚጫወቱና ታክቲካል ዲሲፕሊንም ስለሆኑ ምርጡ ቡድን ሆነው አግኝቼያቸዋለሁ”፡፡

የአፍሪካ ዋንጫውን በቴሌቪዥን መስኮት ሆነህ ስትከታተለው ለዋልያዎቹ ተመርጬ መጫወት ነበረብኝ ብለህ አልጓጓህም…

“ፈጣሪ ስላልፈቀደው ነው እንጂ መጓጓቱማ የት ይቀራል ብለህ ነው፤ ሀገርን ወክሎ መጫወት ሁሉም ይፈልጋል፤ የመጫወት አቅሙም ነበረኝ፤ ሆኖም ግን ለብሔራዊ ቡድን የመምረጥ ስራውን ለአሰልጣኙ ስለሰጠው በቀጣይነት ይህን እድል ለማግኘት ጥረትን አደርጋለሁ”፡፡

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ሐዋሳ ላይ ስላደረገው ተሳትፎና የአሁኑ ዝግጅቱ

“በሐዋሳ የውድድር ቆይታችን ጅማሬያችን ላይ የጣልናቸው ነጥቦች ዋጋ አስከፍለውን ነበር፤ ከዛም ተከታታይ ድሎች ገጥሞን ወደ ሪትማችን መምጣታችንን በመልካም ጎኑ ስለምንመለከተው ከእንቅስቃሴ አንፃር የያዝነውን ነገር ቀጥለንበት በተሻለ ደረጃ ላይ ማለትም በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጥን ነው የምንፈልገው፤ አሁን እያደረግን ስላለው ዝግጅት ደግሞ መናገር የምፈልገው፤ ከበዓል መልስ ወደ ስራችን ገብተናል፤ ከፊትነስ ጋርና ከኳስ ጋር የተያያዘ ስራንም እየሰራን ይገኛል”፡፡

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሊያመጡ ስለሚያስቡት ውጤት

“የእኛ እልም ሁሌም ሊጉን በአንደኛ ደረጃ ላይ ሆነን ስለማጠናቀቅ ነው፤ ይህን ለማሳካት እንድንችልም ገና በርካታ ጨዋታዎች ስላሉ በርትተን የምንሰራ ነው የሚሆነው”፡፡

በመጨረሻ…..

“እንደ ኢትዮጵያ ቡና ክለብ ተጨዋችነቴ በእዚሁ ክለብ ቆይታዬ አንድ ታሪክ ብሰራ በጣም ደስ ይለኛል፤ ለእዛም ነው በየጨዋታው ጥሩ ነገርን ለመስራት የምለፋው፤  ደግሞም ይህን ታሪክ ማሳካቴ አይቀርም፤ ይህን ካልኩ በኳስ ህይወቴ እስከአሁን ለመጣሁበት መንገድ የረዳኝን ፈጣሪዬን፣ ቤተሰቦቼን፣ የቡና ደጋፊዎችን፣ የሰፈሬ ጓደኞችንና አብረውኝ የተማሩትን ማመስገን እፈልጋለውኝ”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P