Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በኢትዮጵያ ቡና ላይ ያስቆጠርናቸው አራት ግቦች ቢያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለም” አቤል ያለው /ቅ/ጊዮርጊስ/

“በኢትዮጵያ ቡና ላይ ያስቆጠርናቸው አራት ግቦች ቢያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለም”
አቤል ያለው /ቅ/ጊዮርጊስ/
ቅ/ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን በሸገር ደርቢ 4-0 ባሸነፈበት ጨዋታ የክለቡ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች አቤል ያለው የድሉን ግብ ካስቆጠሩ ተጨዋቾች መካከል አንዱ ሲሆን ሌሎቹን ግቦች በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ከወላይታ ድቻ በመምጣት ፊርማውን ያኖረው ቸርነት ጉግሳ፣ ፍሪምፖንግ እና አዲስ ግደይ ሊያስቆጥሩ ችለዋል።
የሸገር ደርቢው በአዳማ ከተማ ላይ ከ23 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደበት ጨዋታ ቅ/ጊዮርጊስ ግጥሚያውን በድጋሚ ባሸነፈበት ጨዋታም አቤል ያለው ከአማኑሄል ገብረሚካሄል በመቀበል ማራኪዋን የመጀመሪያ የድል ግብን ማስቆጠሩን እና ግጥሚያውን ማሸነፋቸውን ተከትሎም የተሰማውን የደስታ ስሜት የገለፀ ሲሆን ባሸነፉበት የግብ መጠን ዙሪያም በኢትዮጵያ ቡና ላይ ከነበራቸው ብልጫ አኳያ ያስቆጠሯቸው አራት ግቦች የሚያንሱ እንጂ የሚበዙ እንዳልነበሩም ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል።
የቅ/ጊዮርጊሱ አቤል ያለው ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ ጋር በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የሸገር ደርቢውን ጨዋታ ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለጋዜጣችን የሰጠን ቃለ-ምልልስም በሚከተሉት መልኩ ቀርቧል።
ሊግ፦ በቅድሚያ ለቃለ-ምልልሱ ፈቃደኛ ስለሆንክ ከልብ እናመሰግናለን?
አቤል፦ እኔም ቃለ-ምልልሱን እንዳደርግ ስለጠየቃችሁኝ ከልብ አመሰግናለሁ።
ሊግ፦ ወደ መጀመሪያ ጥያቄዬ ላምራ ኢትዮጵያ ቡናን በሸገር ደርቢው በሰፊ የግብ ብልጫ አሸንፋችኋል፤ በጨዋታው ዙሪያ ምን ትላለህ? ባገኛችሁት ድልስ ምን ተሰማህ?
አቤል፦ የሁለታችንን የሸገር ደርቢ ጨዋታ በተመለከተ እንዳየከው እኛ እንደ ቡድን በመጫወት ነበር የተንቀሳቀስነው። ምክንያቱም ቡድናችን ለዋንጫ ባለቤትነት የሚጫወት ከመሆኑ አኳያም ወሳኙ 3 ነጥብ የሚያስፈልገው ስለሆነም ነበርና በእዛ መልኩ ተጫውተን ባለ ድል ልንሆን ችለናል። ኢትዮጵያ ቡናን በሰፊ የግብ ልዩነት ከማሸነፋችን ጋር በተያያዘ በጣም ደስተኛ ነኝ። ይሄ ደስታዬ ከፍ ሊል የቻለውም አግጥሚያው የደርቢ ስለሆነና በእዚህ የደርቢ ጨዋታ ላይም ከተቆጠሩት የአሸናፊነት ግቦች ውስጥ አንዱን ስላስቆጠርኩም ነው።
ሊግ፦ በኢትዮጵያ ቡና ላይ አራት ግቦችን በማስቆጠር ነበር ጨዋታውን ያሸነፋችሁት፤ ከግጥሚያው በፊት በእዚህን ያህል የግብ ልዩነት እናሸንፋለን ብላችሁ ጠብቃችሁ እና ገምታችሁ ነበር?
አቤል፦ ከቅርብ ዓመታቶች ወዲህ ብዙ ጊዜ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ስንገናኝ በርካታ የግብ እድሎችን እያገኘን ያለመጠቀም ችግራችን ስለሆነ እንጂ ተደጋጋሚ ጎሎችን ማስቆጠር እንደምንችል በእዚህም ጨዋታ ላይ ተማምነን ነበር ወደ ሜዳ ለመግባት የቻልነው። ያም በዕለቱ እነሱን በሰፊ ግብ እናሸንፋለን የሚል ግምታችን ከፈጣሪ እርዳታ ጋር ተሳክቶልንም ድል ልናደርጋቸው ችለናል።
ሊግ፦ ያስቆጠራችኋቸው አራት ግቦች ግን አልበዙም?
አቤል፦ በፍፁም፤ በዕለቱ እንደነበረን ብልጫ እና እንዳገኘናቸው የግብ እድሎች እንደውም ብዙ ግቦች ስተናል። በተለይም በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ያልተጠቀምንባቸው የግብ ዕድሎች ነበሩና እንዳጠቃላይ ሳየው በኢትዮጵያ ቡናዎች ላይ ያስቆጠርናቸው አራት ግቦች የሚያንሱ እንጂ የሚበዙ አልነበሩም።
ሊግ፦ ኢትዮጵያ ቡናን ባሸነፋችሁበት የደርቢው ጨዋታ የእነሱን አቋም በምን ሁኔታ ተመለከትከው?
አቤል፦ በኢትዮጵያ ቡና ክለብ ውስጥ የሚጫወቱ ብዙ ጓደኞች አሉኝ፤ እነሱ ጥሩ የመጫወት አቅሙም አላቸው። በእኛ ቡድን ሲሸነፉ በጨዋታው እንደታየው አሳማኝ በሆነ መልኩ ተጫውተንና ልዩነት ኖሮን ነው ያሸነፍናቸው። አሁን እያስመዘገቡት ባለው ውጤት ግን ያሉበት ነገር ቡድኑን የሚመጥነው ስላልሆነ በቀጣይነት በሚደረጉት ግጥሚያዎች ወደ ተሻለ ነገር እንደሚመጡ ተስፋ አደርጋለሁ።
ሊግ፦ በሸገር ደርቢው በአዳማ ከተማ ላይ ብቻ ሳይሆን ከእዚህ በፊት በነበሩት ሌሎች ግጥሚያዎች ላይም ለመጫወት ችለሃል፤ በሸገር ደርቢው መጫወት የተለየ ስሜት ይሰጣል?
አቤል፦ አዎን፤ ምክንያቱም ይኸው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ሀገራችን ውስጥ ካሉት ትልቁ እና ተጠባቂው ግጥሚያዎች መካከልም አንዱ ነውና፤ ከዛ ውጪም በእዚህ ጨዋታ ላይ መሳተፍ መቻልም ግጥሚያው በዲ. ኤስ. ቲቪ በመላው ዓለም የሚተላለፍ እና አንተንም ብዙዎች የሚከታተሉህ ከመሆኑ አኳያም በጣም ክብርም ስለሆነ ነው የተለየ የደስታ ስሜት ሊሰማኝም የቻለው።
ሊግ፦ በሸገር ደርቢው ፍልሚያ በሜዳ ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ ስትወድቅ ይታይ ነበር?
አቤል፦ አዎን፤ መውደቄ የእውነት ነው የወደቅኩት ያለ ምክንያት አልነበረም። ጨዋታው ላይ ፋውል ይሰራ ነበር፤ እኔም ተረከዜን ስመታ የዕለቱ አልቢትር ጥፋት ብሎ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለእዛ ነው እግሬን አሞኝ ስወድቅ እና ለመታከምም ከሜዳ ስወጣ የነበርኩት፤ በኋላ ላይ በእግሬ ላይ ስፕሬይ ተደርጎልኝ ስመጣና እየቆየም በእግሬ ላይ ያለው የህመሙ ስሜት ደንዝዞልኝ እየቆየ ሲሄድም ነው በሜዳ ላይ ልቆይ ቻልኩ።
ሊግ፦ በሸገር ደርቢው ጎል ስታስቆጥር፣ ሌሎች ተጨዋቾቻችሁ ሲያስቆጥሩ እና ግጥሚያው ከተጠናቀቀ በኋላም የአንተ የደስታ አገላለፅ ከሌሎች ከፍ ባለ መልኩ ይታይ ነበር፤ ለዛ የተለየ ምክንያት አለው?
አቤል፦ አዎን፤ እንደምታውቀው ይኸው ጨዋታ ተጠባቂ የደርቢ ግጥሚያ ነው፤ ከዛም ውጪም ካለን የተቀናቃኝነት ስሜት አኳያ የግድ ማሸነፍ ያለብንና የክብር ጉዳይ ስለሆነ ሌሎቹ ተጨማሪ ነገሮች ደግሞ ክለባችን ለዋንጫው ባለቤትነት የሚጫወት እና በብዙ ደጋፊዎቻችን ፊትም ከአራት ዓመታት በኋላ የተጫወትንበት አጋጣሚም ተፈጥሮ ስለነበር ነው በጣም ስሜታዊ አድርጎኝ ደስታዬን በሁሉም መልኩ በተለየ ሁኔታ ስገልፅ የነበረው።
ሊግ፦ ቅ/ጊዮርጊስ ያለምንም ሽንፈት የሊጉን ዋንጫ ከእዚህ ቀደም ያነሳበት ወቅት ነበር፤ አሁንም ሳይሸነፍ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን እየመራ ይገኛልና ከእዚህ ጉዞው ጋር በተያያዘ አሁንም ሳይሸነፍ ይህን ዋንጫ ያነሳል ትላለህ? ወይንስ….?
አቤል፦ ዋንጫን ከማንሳት ጋር በተያያዘ በኳስ ጨዋታ ምን እንደሚፈጠር ስለማይታወቅ አሁን ላይ በእዚህ ጉዳይ ብዙ አስተያየት አልሰጥም። ገና የ13 ሳምንታት የጨዋታ መርሀ ግብሮች አሉ። ያም ሆኖ ግን የእኛ ቡድን ሁሌም ቢሆን ለሻምፒዮንነት የሚጫወት ክለብ ስለሆነ በመጨረሻ የሚፈጠረውን ነገር አብረን የምናየው ነው የሚሆነው።
ሊግ፦ በቅ/ጊዮርጊስ ውስጥ ካለህ የተጨዋችነት ቆይታ አንፃር ቡድኑን በምፈልገው መልኩ እያገለገልኩት እና እየጠቀምኩት ነው ብለህ ታስባለህ?
አቤል፦ በፍፁም፤ በእዛ ደረጃ ጠቅሜዋለሁ ብዬ አላስብም፤ ለእዛ ምክንያቶችም አሉኝ። የመጀመሪያውም ያለፉትን አራት አመታቶች የእኛ ክለብ ውጤት ከማጣት ጋር በተያያዘ በብዙ ውጣ ውረድ ነገሮች ያለፈበት ሁኔታም ስለነበርና በእዛ ውስጥ ሆነህ ስትጫወት ደግሞ አንድ ተጨዋች ነጥሮ ሊወጣ የሚችልበት ሁኔታም ስለማይኖር በምፈልገው መልኩ ክለቡን ገና አልጠቀምኩትም።
ሊግ፦ በደደቢት የምናውቀው ምርጡ አቤል በቅ/ጊዮርጊስስ አሁን ላይ እየታየ ይገኛል?
አቤል፦ በቅ/ጊዮርጊስ ቆይታዬ ከላይ እንደገለፅኩት ባሳለፍኳቸው ያለፉት ዓመታት የቡድኑ ቆይታዬ በምፈልገው መልኩ ክለቡን ገና እየጠቀምኩት አይደለም ብዬ ነበር። አሁን ላይ ደግሞ በብዙ ነገሮች በቡድናችንም ላይ በራሴም ላይ የተመለከትኳቸው ነገሮች ስላሉና ቡድናችንንም እየጠቀምኩትም ስለሆነ በደደቢት ክለብ ውስጥ የነበረኝን ጥሩ ብቃትን ወደማሳየት ደረጃ ላይ ለመድረስ ችያለው።
ሊግ፦ ብዙዎች በእግር ኳሱ ላይ ካለህ ወቅታዊ አቋም በመነሳት በብሄራዊ ቡድን ውስጥ ተካትቶና ተሰልፎ መጫወት ነበረበት፤ ወደ አፍሪካ ዋንጫውም መጓዝ ነበረበት እሱ እያለ ግን ብዙ ጊዜ ሌሎች ተጨዋቾች ለብሄራዊ ቡድኑ ይመረጡ ነበር በማለት ሲናገሩ ይደመጥ ነበር። ከእዚህ ከብሄራዊ ቡድን ምርጫ ጋር በተያያዘ ምን የምትለው ነገር አለ? ወደ አፍሪካ ዋንጫው በወቅቱ ባለመጓዝህስ ምን ስሜት ተፈጠረብህ?
አቤል፦ አሁን በእርግጥ አልፏል። የአፍሪካ ዋንጫው ላይ ወደ ብሄራዊ ቡድኑ ሊጋዝ በተዘጋጀው ቡድን ውስጥ እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ እኔ እንደነበርኩበት ነው የማውቀው። ያ የመጓዜ ሁኔታ ግን በኋላ ላይ ሲያከትም ጊዜ እንደ አንድ ተጨዋች ከፍተኛ የቁጭት ስሜት ነው የተፈጠረብኝ። ወደ ስፍራው ካለመሄዴ ጋር በተያያዘ ከአሰልጣኙ ውበቱ ጋር ተነጋግረንበታል፤ ተመልሼ ቡድኑን የምቀላቀልበት ሁኔታም ይኖራል። ባለፈው ጊዜም በጉዳት ምክንያት ነው ያልተመረጥኩትና ከእዚህ በኋላ በሚኖረው ቡድን ውስጥ ለብሄራዊ ቡድን በመመረጥ እና ብዙ ትምህርቶችንም በመውሰድ ሀገሬን በትልቅ የውድድር መድረኮች ላይ ማገልገልን እፈልጋለው።
ሊግ፦ ለብሄራዊ ቡድን በማትመረጥበት ሰዓት ወይንም ደግሞ አንተ መመረጥ እየተገባ ሌሎች ተጨዋቾች በሚመረጡበት ሰዓት እንደ አንድ ተጨዋች የምርጫው መስፈርት ያሳምንሃል?
አቤል፦ የተጨዋቾችን ምርጫ በተመለከተ እንዴት ብዬ እንደምገልፅልህ አላውቅም፤ የአሰልጣኝ እይታ፣ ፍላጎት እና ውሳኔ ነው አንተን የሚያስመርጥህ እና ያን አሰልጣኙ የሚሰራውን ስራ አከብርለታለው።
ሊግ፦ ስለ ቀጣይ ጊዜ የኳስ ህይወትህ ምን ትላለህ? ኳሱንስ ጠግበህ ተጫውተሃል?
አቤል፦ መጫወቱን ገና መች ጀመርኩና! /በመሳቅ ነበር ምላሹን የሰጠን/ በኳስ መጫወቱ ላይ ገና ጅማሬ ላይ ነኝ፤ ወደ ውጪ ሀገር በመውጣትም ጭምር ነው እስከ ፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ድረስ መዝለቅ የምፈልገው፤ ለእዛም ደረጃ የሚያደርስ አቅሙም አለኝ።
ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የዘንድሮን ዋንጫ ማን ያነሳል?
አቤል፦ ሊጉ ገና ነው፤ በርካታ ጨዋታዎችም ይቀሩታል። አሁን ላይ ሆኖም ዋንጫውን የሚያነሳውን ቡድንም መገመት አይቻልም። ያም ቢሆን ግን የእኛ ቡድን ካለው ወቅታዊ ብቃቱ አንፃር ይህን ስኬት ሊጎናፀፍ የሚችልበት እድሉ ከሌሎች ቡድኖች አንፃር ከፍ ያለም ነውና ዘንድሮ ምንአልባት ድሉ ወደ እኛ ሊያመራ ይችላል።
ሊግ፦ ላለፉት አራት ዓመታት ክለባችሁ ከዋንጫ ባለቤትነት ርቋል፤ በአንተ እና አሁን ባሉት አብዛኛው የቡድኑ የተጨዋቾች ዘመንም ነው ይህ የውጤት ማጣት ያጋጠመውና በእዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ?
አቤል፦ ልክ ነህ፤ እኔም ሆንኩ ብዙዎቹ የቡድኑ ተጨዋቾችም ናቸው ወደ እዚህ ቡድን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ይኸውን ዋንጫ ሊያጡ የቻሉትና ክለቡ ያ የለመደውን የድል ነገር ሲያጣ በጣም ያስቆጫል። አሁን ላይ ግን ቡድናችን በስኬት ደረጃ ያን ሊያሳካ የሚችልበት አሪፍ የሆነ እድልን አግኝቷልና ከፈጣሪ እርዳታ ጋር ያንን አጋጣሚ በርትተን በመስራት ልንጠቀምበት ተዘጋጅተናል።
ሊግ፦ በሸገር ደርቢው ከብዙ ጊዜያቶች በኋላ ነበር በብዙ ተመልካቾች ፊት ኳስን የተጫወታችሁት፤ በደጋፊ ፊት መጫወቱ ናፍቆህ ነበር?
አቤል፦ አዎን፤ ለእዛ ምንም ጥያቄ የለውም። በጣም ናፍቆኝ ነበር። በተለይም ደግሞ በእኛው የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ፊት ታጅበህ በደርቢው ጨዋታ ላይ ስትጫወት ያለው የደስታ ስሜት ከፍ ያለም ነውና ያንንም የመጫወት ዕድል በሸገር ደርቢው ጨዋታ ላይ ስላገኘው ፈጣሪዬን አመስግኜዋለሁ።
ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ዋንጫን ከማንሳት ጋር በተያያዘ የቱ ቡድን ስጋት ይሆንባችኋል?
አቤል፦ ሊጉን እንደምታየው ብዙ ቡድኖች ነጥብ እየተጣጣሉ ነው። እኛ አሁን እንደበፊቱ የምናየው የሌላውን ውጤት ሳይሆን የራሳችንን ብቻ ነው። በፊት የሌሎቹን እናይ ስለነበር ጥፋት ነው። አሁን ከበፊቱ ብዙ ተምረናል። ሶስት ነጥብን ብቻ ከየጨዋታው ይዘን ስለምንወጣበት ነገርም ብቻ ነውና እያሰብን የምንገኘው ይሄ ጥሩ የቡድን ለውጣችን ነው።
ሊግ፦ ቅ/ጊዮርጊስ ዘንድሮ እያስመዘገበ ላለው የውጤቱ ማማር በጠንካራ ጎንነቱ የሚጠቀስለት ነገር ምንድን ነው?
አቤል፦ አንደኛው ሊጠቀስ የሚችለው ጠንካራው ጎን የአሰልጣኛችን ዘርዬ /ዘሪሁን ሸንገታ/ ከተጨዋቾች ጋር ያለው ቅርበት ነው። እሱ ተጨዋቾችን የሚይዝበት መንገድ ጥሩ መሆኑ እና ለቡድኑ ያለውም ፍቅር ተጨዋቹን አንድ እንዲሆን ማድረጉ ከእሱ ውጪም የኮቺንግ ስታፉ ህብረትም ወደ እኛ ጋር ከመጋባቱ ባሻገር ደስተኛም እንድንሆን አድርጎናልና እነዚህን ነው ለመጥቀስ የምፈልገው።
ሊግ፦ በማሸነፍ እና በውጤታማነት ውስጥ ክፍተቶችም አለ፤ የዘንድሮው ቅ/ጊዮርጊስ እስካሁን በሊጉ ያልተሸነፈ ቡድን ነውና እሱስ ክፍተት የለበትም?
አቤል፦ አለበት እንጂ! በኳስ ጨዋታ ሁሌም ፐርፌክት አይኮንም። እኛም ጋር ይሄ ችግር አለ። በተለይም ወደ ማጥቃቱ ላይ ስናመራ በግብ ማስቆጠሩ ላይ ብዙ ኳሶችን ከማባከን ጋር በተያያዘ የአጨራረስ ድክመት አለብን፤ እሱን ሙሉ ለሙሉ ለማረም የዝግጅት ስራዎችን እየሰራን ይገኛል።
ሊግ፦ ቅ/ጊዮርጊስ ዘንድሮ ካደረጋቸው ግጥሚያዎች ውስጥ በጣም ያስቆጨህ የቱ ነው?
አቤል፦ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረግነው ጨዋታ ነው ያስቆጨኝ፤ ይሄ ሊሆን የቻለውም የገባ ኳስ ተሽሮብን ስለነበር ነው። ያም ሆኖ ግን በኳስ እንዲህ ያሉ ነገሮች ስለሚያጋጥሙ ያንን አምነን ልንቀበለው ችለናል።
ሊግ፦ የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊዎችን አጠር ባለ መልኩ ስትገልፃቸው?
አቤል፦ እነሱ ይለያሉ፤ የትም ሄድን ተጫወትን ሁሌም ከጎናችን ናቸው። ቡድኑን በጣም ነው የሚወዱትና የሚያበረታቱት ይሄን ዓመት ለእነሱ ስንልም ታግለን ተጫውተን ባለድል ልንዳርጋቸውም እንፈልጋለን።
ሊግ፦ የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር አምና ጎልቶ ወጥቶ ነበር፤ የውድድር ዘመኑም ምርጡ ተጨዋች ተብሎ ተሸልሞም ነበር። ዘንድሮስ በጥሩ ተጨዋችነቱ የተመለከትከው ተጨዋች አለ?
አቤል፦ አቡኪ አምና ልዩ ተጨዋች ነበር። ሁሉንም ባሳመነ መልኩም ነው ለታላቅ ስኬት ሊበቃ የቻለው፤ በእስካሁን ጨዋታ በእሱ ደረጃ ያየሁት ተጨዋች ባይኖርም የእኛው የአብስራ ተስፋዬ ዘንድሮ ባለው አቋም ጥሩ ግልጋሎቱን ለክለባችን እየሰጠ ይገኛልና የእሱን ስም ነው በቅድሚያ የምጠራው።
ሊግ፦ ወደ ግል ህይወትህ ላምራ፤ በምን ሁኔታ ላይ ነው የምትገኘው?
አቤል፦ ባለትዳር ነኝ። የትዳር ህይወቴም ጥሩ ነው። ከስድስት ወር በፊት ከባለቤቴ ያፈራዋት አንዲት ራኬቭ የተባለች ሴትም ልጅም አለኝና አጠቃላይ ቤተሰቡ ኑሮን በጥሩ ሁኔታ እያጣጣምነው ነው።
ሊግ፦ ከአንተ የእግር ኳስ ህይወት ጀርባ የባለቤትህን ሚና ብትገልፅልን? ስሟስ ማን ይባላል?
አቤል፦ ባለቤቴ ሄለን መሀመድ ትባላለች። እሷ ለእኔ ብርታቴም ነች። እንደዚሁም ልጅ ያለኝ መሆኑም ብርታቴን ከፍ አድርጎታልና የእሷ የባለቤቴ ከኳሱ ጀርባ በመሆን ለምታደርግልኝ እገዛ አመሰግናታለሁ።
ሊግ፦ ወደማጠቃለሉ እናምራ?
አቤል፦ ቅ/ጊዮርጊስ እስካሁን ለመጣበት ስኬታማው የውጤት መንገድ ከፈጣሪ በታች የክለብ ጓደኞቼን የኮቺንግ ስታፉን፣ አመራሮቹን እና ደጋፊዎቻችንን ለማመስገን እፈልጋለሁ።

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P