Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በእግር ኳስ ዘመኔ ምርጡ ጨዋታዬ የምለው ለሐዋሳ ከተማ ስጫወት ቅዱስ ጊዮርጊስን የረታንበትን ነው”ዩሃንስ በዛብህ /ጆኒ/ /መብራት ሀይል /

በመሸሻ ወልዴ

“መብራት ሀይልን ወርሃዊ ደመወዛችንን ሳያቋርጥ እንደዚሁም አስቀድሞ እየከፈለን ባለበት ሁኔታ በጣም እናመሰግነዋለን”
የኢትዮጵያኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ በቀድሞው ጊዜ በርካታ ተተኪ ተጨዋቾችን በማፍራት ከሚታወቀው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ቡድን ተገኝቶ በተለያዮ ክለቦች ውስጥ በግብ ጠባቂነት ተጫውቶ አሳልፏል። ሜታ ቢራ አየር ሀይል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሐዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡናም የተጫወተባቸው ክለቦች ናቸው። በግብ ጠባቂነትም ጥሩ ችሎታ ስለነበረው ለብሄራዊ ቡድን የሚመረጥባቸው እና በኋላም ላይ አሰልጣኞቹ ከሚፈልጉት አጨዋወት አንፃር መጨረሻ ላይ እሱን ከስኳዱ ውጪ የሚያደርጉበት ጊዜያቶችም ነበሩ።
የኢትዮ ኤሌትሪክ እግር ኳስ ክለብን የአሁን ሰዓት ላይ በኮቪድ 19 ምክንያት የከፍተኛው ሊግ ውድድር ተቋረጠ እንጂ ቡድኑን በግብ ጠባቂነት ሲያገለግል የነበረውን ይኸውን ተጨዋች በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የሊግ ስፖርት ድረ ገፅ አናግራው ምላሽ ሰጥቷታል።
በኮቪድ 19 የእግር ኳስ ጨዋታዎች ስለመቋረጣቸው እና ውድድሮቹ ስለመሰረዛቸው
“እንደ አንድ የእግር ኳስ ተጨዋች ይሄን ውድድር መሰረዝ አስመልክቶ እኔ ማለት የምፈልገው የእግር ኳስ ጨዋታ ምንም እንኳን የሚወደድ አይነት ስፖርት ቢሆንም ወረርሽኙ ግን ዓለም አቀፍ እና በርካታም የሰው ልጆችን ህይወት እየቀጠፈ በእኛም ሀገር ላይም በሽታው እየተስፋፋ በመሆኑ የተወሰነው ውሳኔ ትክክል እና የሚደገፍም ነው” ።
አሁን ላይ በጣም ስለናፈቀው ነገር
“ይሄ ክፉ ወረርሽኝ ከሀገራችን ጠፍቶ ወደ ምንወደው እና ስራችንም ወደሆነው እግር ኳስ ጨዋታችን ቶሎ መመለስ። ስለዚህም በጣም የናፈቀኝ ነገር ኳስ መጫወቱ ነው”።
ግብ ጠባቂው ጊዜውን በምን እንደሚያሳልፍ
“በቤት ውስጥ ብቻዬን ስለምኖር እዛ ነው የማሳልፈው። አልፎ አልፎም ራሴን ጠብቄ ቤተሰቦቼ ጋር እሄዳለው። ከዛ ውጪም ደግሞ ለራሴ የሚጠቅሙኝን መፅሀፎች አነባለው። የእንግሊዘኛ ፊልሞችንና የኳስ ፊልሞችን በማየትም ነው እያሳለፍኩ ያለሁት”።
ለእሱ ቁጥር አንድ ስለሆነው ተጨዋች
“በዓለም ላይ ከሆነ ዚነዲን ዚዳን ነው። በእኛ ሀገር ደግሞ ብዙ ስላሉና አንዳቸውንም ከአንዳቸው መለየትም በጣም ከባድ በመሆኑ ነጥዬ የምጠራው ተጨዋች የለም”።
ከአገራችን ተጨዋቾች በየሚጫወቱበት የመጫወቻ ስፍራስ በቀዳሚነት የምታደንቃቸውስ
“በግብ ጠባቂነት ያዕቆብ ፍስዐን ነው። እሱን ልክ ሌላ እንደምወደው አይነት ተጨዋች እንደቫንደር ሳር ነበር በቀድሞ ጊዜ የማደንቀው። የተከላካይ መስመሩ ላይ ደግም አስቻለው ታመነን የመሀል ሜዳው ላይ ደግሞ ነጥሎ መጥራቱ ቢከብደኝም እነ ኤልያስ ማሞ መስዑድ መሀመድ ዳዊት እስጢፋኖስን የመሳሰሉትን ሳደንቅ የአጥቂው ስፍራ ላይ ደግሞ ሳላህዲን ሰይድን ነው የማስቀምጠው። እነዚህን ከላይ የጠራዋቸው ተጨዋቾች ሁሌም በተለየ መልኩም ነው የምገልፃቸው”።
የግብ ጠባቂ ሆኖ እሱ ለሚፈልገው እንቅስቃሴ የተከላካይ መስመሩ ላይ አብሯቸው ከተጫወታቸው መካከል የሚያደንቃቸው እና ከአጠገባቸው ሆኖ ሊጫወታቸው የሚመኛቸው
“በእዚህ ሁኔታ ውስጥ አብረውኝ ከተጫወቱት ውስጥ ለእኔ ምቾት ሰጥተውኝ ያደነቅኳቸው ተጨዋቾች ለቡና እና ለኤልፓ ስጫወት ኤፍሬም ወንደሰን ለሐዋሳ ስጫወት ደግሞ አዲስ ዓለም ተስፋዬ ናቸው። አብረውኝ እንዲጫወቱ የምመኛቸው ደግሞ አስቻለው ታመነና አንተነህ ተስፋዬ ናቸው። የእነዚህ መሰል አይነት ተጨዋቾች ከፊትህ ሲሆኑ ጥሩ የራስ መተማመን ስሜት ይኖርሃል”።
ለእሱ ምርጥ የሚላቸው አሰልጣኞች
“በቀዳሚነት የምጠቅሰው ውበቱ አባተን ነው። እንደ እሱ ሁሉ ክፍሌ ቦልተናንም እጠቅሰዋለው። ሁለቱ አሰልጣኞች በኳስ ዘመን ቆይታዬ እነሱ የሚፈልጉት ኳስ መስርቶ የመውጣት አይነት አጨዋወትን እኔም የምፈልገው በመሆኑና በእዛም እንቅስቃሴ ስለተግባባንና በሜዳ ላይ የምፈልገውን ነገርም እንዳደርግ ስለተግባባንም ነው ምርጫዬ ያደረግኳቸው”።
ስለ ምርጡ ጨዋታው
“ለሐዋሳ ከተማ ስጫወት ቅ/ጊዮርጊስን ቢያንስ ለሁለት ደቂቃ ያህል ኳስ ይዘንበት በታፈሰ ሰለሞንና በአባት ግቦች 2-0 ያሸነፍናቸውን ጨዋታ ነው። በጨዋታ ዘመኔ በእዚህ መልኩ እኔ እየተጫወትኩ እንዲህ ያለ ብልጫን ተመልክቼ አላውቅም”።
አንድ ቡድን ሲሸነፍ በቅድሚያ በረኞች ስለሚወቀሱበት ሁኔታ
“ይሄ ወቀሳ በእኛ ሀገር ተደጋግሟል። ስለዚህም ብዙ መናገርም አያስፈልግም። ምክንያቱም ያልሰራክበትን ስራ እንዴት ትጠይቃለህ። የእኛ ሀገር በረኞች እኮ በራሳቸው ጥረት ነው እዚህ የደረሱት። እንደዛም ሆኖ ቅድሚያ ጥሩ ችሎታ ለሌላቸው ዜጋ በረኞች የመሰለፍ እድሉ ስለሚሰጥ እና አልፎ አልፎ ብቻ የእኛዎቹ ስለሚጫወቱ ግብ ጠባቂን ደግሞ በድግግሞሽ ካላጫወትከው እና ሲሳሳትም እያረምከው ካልሄድክ ወጥ የሆነ አቋምን ስለማያሳይህ የዜጋ በረኞች መብዛት ነው የአሁን ሰዓት ላይ የእኛን በረኞች ለወቀሳ ያበቃቸው እና የኢንተርናሽናል ጨዋታ ሲኖርም የሚሰለፉት የራሳችን ግብ ጠባቂዎች ስለሆኑም ከጨዋታ መራቅ አንፃር አገራችንም እንድትጎዳ እያደረግን ያለነው።”
በፍፁም ቅጣት ምት ማደን ምርጡ ግብ ጠባቂ
“ይድነቃቸው ኪዳኔን በቀዳሚነት የማስቀምጠው ቢሆንም እኔም ራሴ በእሱ ደረጃ እቀመጣለው”።
የእግር ኳሱን በበቂ መልኩ ተጫውቶ እንደሆነ
“እንደ ግብ ጠባቂነቴ ኳሱን ለጥቂት ጊዜያት እንጂ ገና ብዙ አልተጫወትኩም። ያንን እንድታሳካም አንተን የሚረዳ እና በጥሩ መልኩም የሚያሰለጥንህ ባለሙያ ሊኖርህ ይገባል። ከዛም ባሻገር በእንቅስቃሴው በኩልም ሜዳ ላይ አንተ ለምትፈልገው እሱም ለሚፈልገው አይነት አጨዋወትም ሁለታችሁ መጣጣም መቻል አለባችሁ እና በዚህ መልኩ ስትጓዝ ነው ለረጅም ጊዜ ልትጫወት የምትችለው እና እንዲህ ያሉ ነገሮችን እየጠበቅኩኝ ነው። አንድ ቀን ደግሞ አይቀርም ይሄን እድል እስከ ብሄራዊ ቡድን ደረጃ አግኝቼ ግብ ጠባቂም እንደመሆኔ ለረጅም ዓመታቶች እጫወታለው”።
የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን አንስቶ ስላለማወቁ
“የሊጉን ዋንጫ እስካሁን ከተጫወትኩባቸው ክለቦች ጋር ለአንዴም ቢሆን አለማንሳቴ እንደ አንድ የእግር ኳስ ተጨዋች የሚሰማኝ የራሱ የሆነ የቁጭት ስሜት አለና ይህን ክብር አንድ ቀን ፈጣሪ ሲፈቅድ የማሳካው ነው የሚሆነው”።
ለኮቪድ 19 መከላከያ እንደ አንድ ተጨዋች እያደረገ ስላለው የበጎ አድራጎት ተግባርና ስለ ክለባቸው መብራት ሀይል
“በመጀመሪያ የአሁን ሰዓት ላይ ለዓለምም ለኢትዮጵያም ከፍተኛ ስጋት ስለሆነው ኮቪድ 19 መከላከያ ይሆን ዘንድ እየተደረገ ባለው የበጎ አድራጎት ስራ ላይ ከተሳተፍኩበት ሰዓት ጀምሮ ያደረግኩት ነገር ቢኖር እንደ ቡድኑ ምክትል ካፒቴንነቴ ከቡድን ጓደኞቻችን ጋር ተደዋውለን አንድ ነገር ማድረግ አለብን በሚል እያንዳንዳችን አንድ አንድ ሺ ብር አዋጣንና በ25 ሺ ብር የተለያዩ ቁሳቁሶችን በመግዛት አቅም ለሌላቸው ሰዎች እንዲሰጥልን ለኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል የተጨዋቾች ማህበር አስረከብን። በመቀጠል ደግሞ በካፒቴንነት ተጠርቼና ከክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ደንድርም ጋር በመነጋገር እያንዳንዳችን ተጨዋቾች ከደመወዛችን ላይ 10 ፐርሰንት እንዲቆረጥ በማድረግም የበኩላችንን ማህበራዊ ሀላፊነት ተወጥተናል። ከዛም ዉጪም እኔ በግሌ በሰፈሬ ገዳም ሰፈርም የሚጠበቅብኝን አድርጌያለውና ይሄ የሚያስደስት ነገር ነው። ወደ ክለባችን ኤልፓ ስመጣ ደግሞ ምንም እንኳን ክለቡ አሁን ላይ በከፍተኛ ሊግ ደረጃ ወርዶ ይጫወት እንጂ ለሀገሪቷ እግር ኳስ ብዙ አስተዋፅኦ ያበረከተ ነው። በእዚህ ደረጃ ላይ መገኘትም አልነበረበትም አንድ ቀን ተመልሶ መምጣቱም አይቀርም። ይህን ካልኩ ቡድኑ በእዚህን ሰዓት በርካታዎቹ ወርሃዊ ደመወዝ መክፈል ባቃታቸው ሰዓት የእኛ ክለብ ግን እንደውም ከቀናቶች በፊት ደመወዛችንን ሳያቋርጥ እየከፈለን ይገኛልና በቡድኑ ተጨዋቾች ስም ላመሰግነው እፈልጋለው”።
በመጨረሻ
“ኮቪድ 19 ዓለምንም እኛንም እያስጨነቀን ነው። ይሄን ወረርሽኝም ለመከላከል ሁላችንም እጃችንን ቶሎ ቶሎ ልንታጠብ እና ሳኒታይዘርም ልንጠቀም ይገባል። ከዛም ባሻገር ሰዎች በሚበዙበት ቦታ ላይ ባለመገኘት ቢቻል እቤት ውስጥ በመዋል ጊዜውን ማሳልፍ ይጠበቅብናል። ፈጣሪም ይሄን ወረርሽኝ እንዲያጠፋልንም ፀሎታችንን ልናደርግም ይገባል”።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P