Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በኦዚል ስም ብጠራም ከፋብሪጋስ አላስበልጠውም” “ሲዳማ ቡና አሁንም ከዋንጫው ፉክክር አልወጣም” ዳዊት ተፈራ /ኦዚል//ሲዳማ ቡና/

በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/

ዳዊት ተፈራ /ሲዳማ ቡና/
የመከላከያ የተስፋ ቡድን ያፈራው፤ በአሁን ሰዓት ላይ ደግሞ ለሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ በመሀል ሜዳው ላይ በመጫወት ጥሩ ብቃቱን እያሳየ
የሚገኘው ዳዊት ተፈራ ብዙዎቹ ሲጠሩትም /ኦዚል/ የሊጉ ውድድር ላይ ቡድናቸው ምንም እንኳን በመሪው ክለብ መቐለ 70 እንደርታ በ8
ነጥብ ተበልጠው በሁለተኛ ደረጃ ላይ ቢቀመጡም አሁንም ከዋንጫው ፉክክር እንዳልወጡ አስተያየቱን ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ ሰጥቷል፡፡
የሲዳማ ቡናው አማካይ በሊጉ ውድድር ላይ ምርጥ ብቃታቸውን በመሀል ሜዳ ላይ ከሚያሳዩ የሀገራችን ተጨዋቾች መካከል ስሙ የሚጠቀስ
ሲሆን በሻሸመኔ ከተማ ተወልዶ እና አድጎም ወደ አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ ለመከላከያ የተስፋ ቡድን በአሰልጣኝ መቶ አለቃ ምንያምር እየሰለጠነ
በሚጫወትበት ጊዜ ድንቅ የሜዳ ላይ ብቃቱን አሳይቷል፡፡ ከክለቡም ጋር የተስፋ ቡድኖች ውድድርን ዋንጫ ሊያነሳም ችሏል፡፡
ዳዊት ተፈራ /ኦዚል/ በእግር ኳስ ህይወቱ በኋላም ላይ ለጅማ አባቡና እና ለሲዳማ ቡናም ሲጫወት በግራ እግሩ ኳስን እንደፈለገ ሲያንሸራሽር እና
ለጓደኞቹም ሲያቀብል የተመለከቱት ሁሉ ከፍተኛ አድናቆትን የሰጡት ተጨዋች ሲሆን ትልቅ ደረጃ ላይ ይደርሳል ተብሎ ከወዲሁ ግምት የተሰጠውን
ይኸውን ተጨዋች በኳስ ህይወቱና በሌሎች ጥያቄዎች ዙሪያ ጥያቄን አቅርበንለት ምላሹን ሰጥቶናል፤ ተከታተሉት፡፡

ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ጉዞአችሁን እንዴት ትመለከተዋለህ? የሊጉን ዋንጫ ለማንሳትስ የሚኖራችሁ ዕድል የቱን ያህል ነው?
ዳዊት፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳትፎአችን ላይ ክለባችን ለዋንጫው ፉክክር እንደመጫወቱ በአሁን ሰዓት እየሄደበት ያለው ጉዞ
ጥሩ እና አበረታች ነው፤ በመጀመሪያው ዙር የውድድር ተሳትፎውም መልካም እና ከዚህ በፊት የነበረውን የውጤት ሪከርድም ያሻሻለበት ሆኖ
ውድድሩ ተጠናቋል፤ በሁለተኛው ዙር ላይ ደግሞ ከመጀመሪያው ዙር የተሻለ የሚባል ውጤትን ስለምናስመዘግብ ቡድናችን የበለጠ ጠንካራ ይሆናል፡፡
የፕሪምየር ሊጉ ውድድራችን ላይ ዋንጫውን ለማንሳት ስለሚኖረን እድልም መናገር የምፈልገው የአሁን ሰዓት ላይ ምንም እንኳን በመሪው ክለብ
መቐለ 70 እንደርታ በ8 ነጥብ ልዩነት ተበልጠን በሁለተኛ ደረጃ ላይ ብንገኝም አሁንም ከዋንጫው ፉክክር ያልወጣን በመሆኑ ዋንጫውን የማንሳት
እድሉ አለን፤ ሊጉ በአሁን ሰዓት በርካታ ግጥሚያዎች ነው የሚቀሩት፤ የእኛ ቡድን ደግሞ በወጣቶች የተገነባ እና ኳስንም መስርቶ የሚጫወት ቡድን
ስለሆነ ዘንድሮ ጥሩ ነገርን ከቡድናችን እንጠብቃለን፡፡

ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው ዙርን በሽንፈት ጀምራችኋል፤ ሲዳማ ቡናን እስከ ውድድሩ ማብቂያ ድረስ በምን መልኩ እንጠብቀው?
ዳዊት፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው ዙር ውድድራችንን ከፋሲል ከነማ ጋር አድርገን በሽንፈት ብንጀምርም በእግር ኳስ እንዲህ ያሉ
ሽንፈቶች ስለሚያጋጥሙ ከሽንፈታችን ለመማር ዝግጁ ነን፤ ሲዳማ ቡናን እስከ ሊጉ ማብቂያ ድረስ የምንጠብቀው ከመጀመሪያው ዙር የውድድር
ተሳትፎው ተሸሎ በመቅረብ ነው፤ ክለባችን በመጀመሪያው ዙር አንድ ጨዋታን ብቻ ነበር የተሸነፈው፤ እሱንም የተሸነፍነው በመቐለ 70 እንደርታ
ነው፤ ከዚህ በኋላ ግን በሚኖረን የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎችን በአንድም ግጥሚያ ላለመሸነፍ ለራሳችን ቃል ስለገባን ካሉን ጨዋታዎች ውስጥም
ግማሽ ያህሉን ካሸነፍን እና ከመሪው ክለብ ጋርም በሜዳችን ጨዋታ ስላልንም እሱንም ማሸነፍ ከቻልንም ሻምፒዮና ልንሆን ስለምንችል ቀሪው
የሊግ ውድድር ከባድ ፉክክርን የምናደርግበት ነው፡፡
ሊግ፡- የሲዳማ ቡና ጠንካራ እና ደካማ ጎኑ ምንድን ነው?
ዳዊት፡- የክለባችን ጠንካራው ጎን ኳስ ይዘን መጫወታችን እና ያገኘናቸውን የጎል እድሎች የምንጠቀም መሆናችን ነው፤ ከዛ ውጪም
እያንዳንዱን ጨዋታ ስናደርግ እናሸንፋለን ብለን ወደሜዳ ስለምንገባ ይህ ጠንካራ ጎን ስላለንም ነው ዘንድሮ በክለቡ ታሪክ አንድም ጊዜ በሲዳማ ቡና
ተሸንፎ የማያውቀውን ቅ/ጊዮርጊስንም ልናሸንፍ የቻልነውና ይሄ ጥንካሬያችን ለውጥ እያመጣልን ስለሆነ በዚሁ የምንቀጥልበት ይሆናል፡፡
በደካማነት ደግሞ ቡድናችን ላይ የማነሳው ጎን ብዙም የለም፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ህይወትህ ደስተኛ ነህ?
ዳዊት፡- አዎን፤ ኳስ ተጨዋች ሆነህ እንዴት ነው ደስተኛ የማትሆነው፤ ኳስ እኮ የምትዝናናበት እና የሚወደድ አይነት ስፖርት ነው፤ እኔም
ወደሙያው ከገባው በኋላ ከክለብ ወደ ክለብ ስዘዋወር ማለትም ከመከላከያ ተስፋ ቡድን ወደ ጅማ አባቡና ቀጥሎ ደግሞ ወደ ሲዳማ ቡና
ዝውውርን ሳደርግ በችሎታዬ ከፍተኛ መሻሻልን እያሳየው እና እድገትንም እያመጣሁበት ስለተጓዝኩ በኳሱ ህይወቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ተጨዋችነት ህይወትህን የት ድረስ ማድረስ ነው የምትፈልገው?
ዳዊት፡- የእግር ኳስ ህይወቴን በአጭር ዓመታት ጊዜ ውስጥ እዚህ ደረጃ ላይ ማድረስ ከቻልኩ በቀጣይነት ደግሞ ከፈጣሪ እርዳታ ጋር ከፍተኛ ስፍራ
ላይ ለማድረስ ብዙ የማስባቸው ነገሮች አሉና እዛ ላይ ትኩረትን እያደረግኩ ነው፤ ለምሳሌ ወደውጪ ሃገር በመጓዝ የፕሮፌሽናል ተጨዋች መሆን
እፈልጋለሁ፤ የሀገሬን ብሔራዊ ቡድን ማልያንም በተደጋጋሚ ጊዜ ለብሼ መጫወትንም እፈልጋለው፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን ልጅ ሆነህ ስትጫወት የአንተ ተምሳሌት ተጨዋች ማን ነበር?
ዳዊት፡- ምንም እንኳን የመሃል ሜዳ ተጨዋች ሆኜ ብፈጠርም ከልጅነቴ አንስቶ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ በጣም የማደንቀው እና
ተምሳሌቴም ያደረግኩት ተጨዋች ሳላህዲን ሰይድን ነው፤ ሳላህዲን በችሎታው ልዩ ብቃት ያለው ተጨዋችም ነው፡፡
ሊግ፡- ከዳዊት ስምህ ይልቅ ኦዚል በሚለው የቅፅል ስም መጠሪያህ ትታወቃለህ፤ ኦዚል ለምን ተባልክ? እሱን ስለምታደንቀው ነው? ማንስ ነው
ስሙን ያወጣልህ?
ዳዊት፡- ኦዚል የሚለው ስም የወጣልኝ ለጅማ አባቡና ስጫወት የክለቡ ደጋፊዎቹ ናቸው በመሃል ሜዳው ላይ ጥሩ ስንቀሳቀስ እና ለአጥቂዎችም
ኳስን አሲስት ሳደርግ ተመልክተው ስሙን ያወጡልኝ፡፡
በኦዚል ስም አሁን ላይ ልጠራ እንጂ በባህር ማዶ የኳስ ክትትሌ እኔ በጣም የማደንቀው ተጨዋች ቢኖር ፋብሪጋስን ነው፤ ኦዚልን ባደንቀውም
ከፋብሪጋስ አላስበልጠውም፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን መጫወትህ ላይ የቤተሰቦችህ አመለካከት እና ፍላጎት የቱን ያህል ነበር?
ዳዊት፡- የእግር ኳስን ልጅ ሆኜ ስጫወት በቤተሰቦቼ አካባቢ የነበረው አመለካከት ምንም አይነት ተፅህኖ አይደረግብኝም ነበርና ጥሩ ነበር፤ ኳስን
ልጅ ሆኜም ጀምሮ እወድ እና የእኛ ሀገርንም ሆነ የውጪ ሀገር ኳስንም በቴሌቭዥን እከታተልም ስለነበርም ለቤተሰቦቼም እነዚህ ተጨዋቾች
የደረሱበት ደረጃ ላይም እደርሳለሁ ብዬም እነግራቸው ስለነበርና እነሱም በዛ በመገረማቸው የሀገራችን ተጨዋቾች በአሁን ሰዓት የደረሱበት ደረጃ ላይ
ለመገኘት በመቻሌ በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ ስለ እኔ እነሱንም ልጠይቃቸው ትችላለህና በዚሁ አጋጣሚ ከእኔ ጎን የሆኑ ቤተሰቦች ስለነበሩኝ በጣም
ላመሰግናቸው እፈልጋለው፡፡
ሊግ፡- ብዙዎች በችሎታህ እና ፀጉርህንም ቀለም ተቀብተህ በመጫወትህ ያውቁ ነበር፤ የኢትዮጵያ ቡናን በተፋለማችሁበት የህዳሴው ግድብ ጨዋታ
ላይ ግን የፀጉር ቀለምህ በጭንቅላትህ ላይ አብሮ ስለሌለ በብዙዎች ዘንድ ሜዳ ላይ መኖርህ ተረስቶና እሱ ነው አይደለም የሚሉም ክርክር አስነስቶ
ነበር እና የፀጉርህን ቀለም ወደየት ወሰድከው? ከአሁን በኋላስ አይኖርም ማለት ነው?

ዳዊት፡- የኢትዮጵያ ቡናን በተፋለምንበት የህዳሴው ግድብ ጨዋታ ላይ ለብዙዎች ሜዳ ላይ ልጠፋባቸው የቻልኩት ብራውን ከሆነው የፀጉሬ ቀለም
ጋር አብሬ ወደ ሜዳ ለመግባት ስላልቻልኩ እንጂ የመሀል ሜዳው ላይ ስጫወት የነበርኩት እኔው ራሴ ነኝ፤ የፀጉር ቀለሙም አብሮኝ ያልነበረው
በአጋጣሚ የእዚያ አይነት ማለትም ብራውን የሆነውን ከለር ላጣው ስለቻልኩም ነበር፤ የፀጉር ቀለሙን መቀባት የጀመርኩት ለጅማ አባቡና
ስጫወት ጀምሮ ነው፤ መቀባቱና ከለሩም ደስ ስላለኝ በእዛው ቀጠልኩበት፤ የሆነ ጊዜ ሳጠፋውም ብዙዎች እንዳታጠፋው ያምርብካል ሲሉኝ
በድጋሚ ተቀባውት እና ወደፊትም የፀጉሬ ብራውን የሆነው ቀለም አብሮኝ የሚኖር እንጂ የሚጠፋ አይሆንም፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ?
ዳዊት፡- የእግር ኳሱ ላይ ዛሬ ለደረስኩበት ደረጃ በቅድሚያ የማመሰግነው ፈጣሪዬን ነው፤ በመቀጠል ደግሞ ቤተሰቦቼን፤ ከዛም ሻሻመኔ እያለሁ
ያሰለጠነኝ እና ለትምህርት ቤቶች ጨዋታም የሰውነት ደቃቃነቴን ሳይሆን ችሎታዬን ብቻ በማየት ከብዙዎች ኮሚቴዎች ጋር ክርክር ፈጥሮ እና
ኃላፊነቱንም እኔ እወስዳለው ብሎ ወደ አዳማ ተጉዤ እንድጫወት ያደረገኝን አሰልጣኝ መስፍን ይባላል እና እሱንም አመሰግናለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P