Google search engine

“በኮሮናው ቫይረስ ከእግር ኳስ መራቁ ስሜቱ በጣም ከባድ ሆኖብኛል፤ ከጤናና ከሕይወት የሚበልጥ ነገር ስለሌለ ይሄን ጊዜ በትግስት ልናሳልፈው ይገባል”አስቻለው ታመነ /ቅዱስ ጊዮርጊስ/


ኮቪድ 19 /ኮሮና ቫይረስ/ ለዓለምም ለውዲቷ አገራችንም ከፍተኛ ስጋት በሆነበት እና በርካታ ሰዎችንም እያሳጣንና ለህመምም እየዳረገ ባለበት የአሁኑ ሁኔታ ቫይረሱን ለመከላከል እንዲቻል እግር ኳስን ጨምሮ በርካታ ነገሮች የቆሙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግም ውድድር አንዱ ነው፤ ይኸው የሊግ ውድድር ከቆመ በኋላም ክለቦች ተጨዋቾቻቸውን በትነው ወደየቤተሰቦቻቸውም እንዲያመሩም አድርገዋል፤ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝም ከዕለት ወደ ዕለትም በዓለም ላይ እያገረሸ በመምጣቱም በአንድ አንድ ሀገራት ውድድሮች እስከመሰረዝም የተደረሰባቸው ሁኔታዎችም አሉ፤ በአንድ አንድ አገራት ደግሞ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ የሊግ ውድድር ለማድረግ ውይይት ላይ እንደሆኑም ተሰምቷል፤ የእኛን ሀገር በተመለከተ ደግሞ ካፍ ስለሊጋችሁ ቀጣይ ውድድሮች አሳውቁን የሚል መረጃ እየወጣ ይገኛል፡፡
የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በሚመለከት ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ የሊጉ ተጨዋቾች በአሁን ሰዓት ከየቤተሰቦቻቸው ጋር መሆናቸውን ተከትሎ ስፖርተኛ እንደመሆናቸውና ከስፖርቱ መራቅ ደግሞ የሚያስከትልባቸው ችግር ስላለ ቤት በመዋላቸው ምን እየሰሩ ነው? ቫይረሱን በጋራ ለመከላከል እንዲቻልስ በምን በምን ሁኔታዎች ላይ እየተሰማሩ ነው? በሚለውና በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመናቸው ስለራሳቸው ምርጥ ግጥሚያ እና ከግብ ጠባቂ፣ ከተከላካይ፣ ከአማካይ እና ከአጥቂዎች የእነሱ የመጀመሪያ ተመራጭ ስለሆነው ተጨዋች ይናገራሉ፤ ለዛሬው የቅዱስ ጊዮርጊሱን አስቻለው ታመነን አናግረነዋል፤ ተከታተሉት፡፡
ስለ ኮሮና ቫይረስ አገራችን መግባት እና ይሄንንም ወረርሽኝ ለመከላከል እያደረገ ስላለው የበጎ አድራጎት ተግባራት
“በቅድሚያ ይሄ በሽታ በጣም አስከፊ የሆነ በሽታ ነው፤ ከዛም ባሻገር ሁላችንም እንደምናውቀው ለዓለም ብቻ ሳይሆን ወደ ኢትዮጵያም ጭምር መጥቶ ብዙ ነገሮችንምአስቸጋሪ እያደረገብንም ይገኛል ይሄ በመሆኑም በጣም ነው ያዘንኩት ጥሩ ያልሆኑ ስሜቶችም ተሰምቶኛል፤ ወረርሽኙን ለመከላከል እየተደረገ ባለው ጥረት ውስጥ አዎን እኔም የእግር ኳስን ከሚጫወቱ ጓደኞቼ እና ከአንድ አንድ አካላቶች ጋር በመሆን ባለን እና በምንችለው አቅም ማለትም በፋይናንሺያል፣ በጉልበት እና እንደዚሁም ደግሞ ህብረተሰቡ ቫይረሱን በምን መልኩ መከላከል እንዳለበትም የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላቶች ጋር በመሆን ሰጥተናል፤ ከዛ ውጪም አሁን ደግሞ እኔ በምኖርበት የዲላ ከተማ ላይ ተመሳሳይ የሆኑ ነገሮችንም እዛ ካሉ አካላቶችና ተጨዋቾች ጋር ለመስራትም ፕሮግራምን ይዘናልና በእዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው ከህዝቡ ጎን ሆኜ እየሰራውየምገኘው፤ ስለዚህም በቀጣይነትም ሁላችንም ይሄን የመጣብንን ችግር የምንወጣው በጋራ ስንሰራ በመሆኑ አሁን እያደረግን እንዳለው የበጎ አድራጎት ተግባራት ከህዝባችን ጎን ሆነን ሁሉንም ነገር በጋራ ልንሰራው ይገባናል”፡፡
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከእግር ኳስ ጨዋታ መራቅ መቻል ስለፈጠረብህ ስሜት

“ከእግር ኳስ መራቅ ስሜቱ በጣም አስቸጋሪ ነው፤ ይሄ ደግሞ እኔ ላይ ብቻ ሳይሆን በሁላችንም ላይ እየተፈጠረም ነው፤ ያምቢሆን ከጤና እና ከሕይወት የሚበልጥ ነገር የለምና ሁላችንም ለጤናችን ሰግተን፤ ህይወት ሲኖረንም ነው ኳስንም የምንጫወተውና ከቤተሰብ ጋር መዋሉና ከኳሱ መራቁ የግድ ነው የሚለን፤ ስለዚህም ከኳስ መራቅያውም ለእዚህን ያህል ጊዜ ምንም እንኳን ከባድ ነገር ቢሆንም ይሄን ጊዜ ግን ከቫይረሱ አስቸጋሪነት አኳያ በመመካከር እና በመተጋገዝ እንደዚሁም ደግሞ ቤት በመሆንም ጭምር ማሳለፋችን በጥሩ ጎኑ የሚጠቀስ ነው”፡፡
የአዲስ አበባ ስታድየምና ደጋፊዎቻችሁ ናፍቀውካል
“ያ ናፍቆትማ በውስጥህ ይኖራል፤ በተለይ ደግሞ የቡድንህ ጓደኞች፣ ደጋፊዎቻችን እና እነሱ የሚያሳዩት ድባብ በዋናነት ይጠቀሳል፤ የእኛ ደጋፊ ደግሞ በተለይ በአዲስ አበባ ስታድየም ብቻ ሳይሆን ጨዋታው የትም ቢሆንም ለእኛ እንደ 12ኛ ተጨዋችም ስለሚሆኑን በእነሱ ፊት መጫወት በጣሙን አምሮኛል፤ ስለዚህም ፈጣሪ ደጉን ጊዜ ያምጣልን እና ወደዛ ጊዜ እናመራለን ብዬም አስባለው”፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ጥሬ ስጋ አትብሉ ተብሏል፤ በተለይ እናንተ የደቡብ ክልል ነዋሪዎች ጋር ግን ይህ ህግ እንደተጣሰ ይነገራልና ከዚህ ጋር በተያያዘ የምትለው ነገር ካለ…
“የጥሬ ስጋን በተመለከተ በዛ ደረጃ ምግቡን አትብሉ ተብሎ መመሪያ ቢወጣም እዛ ያሉ አንድ አንድ ነዋሪዎች ግን ጥሬ ስጋንይበላሉ፤ ጥሬ ስጋን ባለመብላት የሚጠነቀቁም አሉ፤ የሚበሉትን ተንተርሶ እነሱን አትብሉ ከማለት ህይወታቸውን ቢሰጡ ይመርጣሉና ነገሮች በጣም አስቸጋሪ የሆነበት ሁኔታ ነው ያለው፤ ስለዚህም ጥሬ ስጋ ለሚበሉ ሰዎች ከመንግስት አካላት ጋር በመሆን ይሄን ጊዜ ብቻ የምናሳልፍበትን የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን እንሰጣቸዋለን፤ በእዚህም ብዙ ነገሮችም ይስተካከላሉም ብዬ አስባለው”፡፡

በኮሮና ቫይረስ ቤት ውስጥሲውል ምን እንደሚሰራ
“በአገራችን በቤት ውስጥ የሚሰሩ የተለያዩ ልምምዶች አሉ፤ እነዛንም ትሬሊንጎች በሚገባ እየሰራውም ነው የምገኘው፤ በሶሻል ሚዲያዎች ላይም ለቅቂያቸለው፤ ከዛ ውጪም ከቤተሰቦቼ ጋርም እጫወታለው ፊልሞችንም አያለው፤ ሌላው የማደርገው ነገር ደግሞ የቡድን ጓደኞቼም ይናፍቁኛልና በስልክም እንደዋወላለን”፡፡
በእግር ኳስ ዘመኑ ምርጡ ስለሚለው ጨዋታው
“ብዙ አሉ፤ በዋናነት የምጠቅሰው ግን በክለብ ደረጃ በሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ምንተስኖት አዳነ በቀይ ካርድ ኮንጎ ላይ የወጣበት ግጥሚያ ለእኔ ምርጡና ጥሩ ብቃቴንም ያሳየሁበት ስለነበር ቅድሚያን የምሰጠው ጨዋታ ነው፤ በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ደግሞ በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ባህርዳር ላይ ኮትዲቯርን ያሸነፍንበት ጨዋታ ተመራጩ ነው”
የእግር ኳስን መጫወት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በየስፍራው የእሱ ምርጥ ተጨዋቾች እነማን እንደሆኑና ስለ ብቃታቸው
“የእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኔ ላይ ስጫወትም ሆነ በሚገባ ከተመለከትኳቸው ተጨዋቾች ውስጥ ለእኔ በየቦታው ምርጥ ናቸው ብዬ የማስቀምጣቸው ተጨዋች በግብ ጠባቂነት ሮበርት ኦዶንካራን ነው፤ ሮበርት እኔ ቅዱስ ጊዮርጊስ በገባሁበት ዓመት ላይ እሱ በሜዳ ላይ ሲኖር ለእኛ ተከላካዮች ብቻ ሳይሆን ቡድኑም በራስ መተማመን መንፈስ እንዲጫወት ያደርገዋል፤ ወደ አንተ ቡድን የሚሞከሩ ኳሶችንም አቅልሎም ይይዛል፤ ግብህም እንዳይደፈርም ያደርጋልና እሱ ምርጫዬ ነው፡፡ ወደ ተከላካዮች ስናመራ ደግሞ ለእኔ ቀዳሚው ምርጫዬ ደጉ ደበበ ነው፤ እሱ ምርጫዬ ብቻ ሳይሆን በእግር ኳሱ አርአያዬ የሆነም ተከላካይ ነው፤ ስለ ደጉ ብቃት ማለት የምፈልገው ደግሞ ደጉ በችሎታው ጥሩ አቅምና የተካበተም የጨዋታ ልምድ ያለው ተጨዋች ከመሆኑ ባሻገር በጣም ጠንቃቃና ብልጥም የሆነ ተጨዋች ነው፤ ከእሱ ሁላችንም ተጨዋቾች በተለይ ደግሞ ተከላካዮች ብዙ ነገሮችን ልንማርም ይገባናልና በዚህ ነው ተመራጬ ያደረግኩት፡፡ ወደ አማካይ ስፍራ ተጨዋቾች ሳመራ ደግሞ የእኔ ምርጫ ታደለ መንገሻ ነው፤ ከታደለ ጋር ከደደቢት ጀምሮ አብረን ተጫውተናል፤ በደንብም አውቀዋለው፤ ታዱ ምርጥና ድንቅ ተጨዋች ነው፤በተለይ ደግሞ አንድ አጥቂን ከግብ ጋር የሚያገናኝበት መንገድ ይለያል፤ ከዚህ በፊት በብሄራዊ ቡድን ደረጃ እንኳን ከአልጄሪያ ጋር ስንጫወት ለጌታነህ ያቀበለበትን ነገር ስትመለከት እሱ ተመራጭህ ተጨዋች ይሆናል፡፡ ወደ አጥቂዎች ጎራ ሳመራ ደግሞ በተደጋጋሚ ጊዜም ተናግሬያለው፤ ለእኔ የመጀመሪያ ምርጫዬ ጌታነህ ከበደ ነው፤ ጌታነህ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት አጥቂዎችምቁጥር አንዱም ነው፤ ጌታነህን ምርጫዬ ለማድረግ የቻልኩበትም ዋናው ነገር የሚያገኛቸውን የግብ ኳሶች የማይምርና ቡድንህንም በተደጋጋሚ ጊዜም ውጤታማም የሚያደርግ ተጨዋች ስለሆነ ከዛ ባሻገር የ16 ከ50 ክልል ውስጥ ያለው አጨዋወቱም የሚማርክ ስለሆነ በዛ ደረጃ ልወደው እና በጣምም ላደንቀው ችያለው”፡፡

በቅርብ ስለተቋቋመው ስለ አዲሱ የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር
“ኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ ቀደም ለተጨዋቾች የሚከራከር አካል አንድም አልነበረም፤ በእዚህም ብዙ ተጨዋቾች ተጎድተዋል፤ የነበሩት ሁኔታዎችም በጣም አስቸጋሪዎች ነበሩ፤ አሁን ግን ለእኛ የቆመልን አዲስ እና ጠንካራ የፕሮፌሽናል ተጨዋቾች ማህበር ተመስርቷልና በእዚህ ደስተኛ ነኝ፤ ጠንካራ እየተቃቃመነው የሚገኘው በማህበራዊ ስራ እየተሳተፈ ነው ከዚህ ማህበር ጋር ልንሰራ ይገባል በማህበሩ እንደ ግልም እንደ ክለንም የግል ችግራችነምን በግል በማሳውቅ ማወቅ መቻል አለብንና ከማህበሩ ቀረው መስራት ይጠበቅብናል
የመጨረሻ መልዕክትህ
“ኮቪድ 19 አስቸጋሪ በሽታ ነው፤ ህዝባችን ግን አንድ ሰሞን ለዚህ ክፉ ወረርሽኝ መጠንቀቅ ጀመረና አሁን ላይ ደግሞ 50 ሰዎች አገገሙ የሚያዙትም ቢያንስ አንድ እና ሁለት ሰዎች ናቸው ሲባል ጊዜም መልሶ እየተዘናጋ ነው የሚገኘውና ከዚህ መዘናጋት ሊቆጠብ እና እንደበፊቱ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ፤ ከዛ ውጪም የበዓሉ ሰሞንም በዓሉን ምክንያት በማድረግ አዲስ አበባ ካሉ ሰዎች ጋርም እንደዋወልም ነበርና አንድ በግ ለመግዛት ሰው ሲወጣ ያለው ግርግር ጥሩ አልነበረምና ይሄም ሁኔታ ታሳቢ ሊደረግ ይገባል፤ በጉን የምትበላው ህይወት ሲኖርህ ነው፤ ስለዚህም ሁላችንም ከኮሮና ቫይረስ ራሳችንን ለመከላከል በመንግስትና በጤና ጥበቃ ደረጃ የወጡትን መመሪያዎች በማክበር እንደዚሁም ደግሞ እንደ እምነታችን ፀሎት በማድረግና በቤታችን ውስጥ ሆነን በማሳለፍ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል፡፡ ሌላው መልዕክቴ ይሄ ከፍተኛ ስጋት የሆነብንን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጊዜን አሳልፈን እኛ ስፖርተኞች ብቻ ሳንሆን ሌላው ማህበረሰብም ወደምንወደው ስራችን እንድንመለስ ፈጣሪ ይርዳን መልካምና ጥሩሁንም ነገር ያምጣልን ነው የምለው”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P