Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በዓምናው ውጤት ተቆጭተናል፤ ዘንድሮ ከ1-3 መውጣትን አልመናል”  ሰለሞን ወዴሳ /ባህርዳር ከተማ/

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ለባህርዳር ከተማ በመጫወት ላይ ይገኛል፤ ወጣት ነው፤ በተከላካይ ስፍራው ላይ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን እያሳየ ይገኛል፤ በሊጉ ባሳየው አቋምም ለኢትዮጵያ እድሜያቸው ከ23 ዓመት በታች ለሆናቸው ብሔራዊ ቡድን ተመርጦ መጫወቱም ይታወሳል፤ የባህርዳር ከተማውን ሰለሞን ወዴሳን የዘንድሮ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ከመጀመሩ በፊት እያደረጉት ስላለው የፕሪ-ሲዝን ዝግጅት፣ ዘንድሮ ምን ውጤትን ለማምጣት እንደተዘጋጁ፤ ስላሳለፍነው የውድድር ዘመንና ሌሎች ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮችን የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ለተጨዋቹ አቅርቦለታል፤ ተከታተሉት፡፡

ሊግ፡- የእስካሁን የፕሪ-ሲዝን ዝግጅታችሁ ምን ይመስላል?

ሰለሞን፡- በጣም ጥሩ የሆነ ልምምድን እየሰራን ነው፤ ሶስት ሳምንትም ሆኖናል፤ በአብዛኛው ከኳስ ጋር በተያያዘም በቡድን ግንባታ ላይ በማተኮር ነው እየተለማመድን የሚገኘው፤ ከእዛ ውጪም የአካል ብቃቱም /ፊትነስ/ ላይ በሚገባ በመስራት የውድድር ዘመኑን መጀመር በመጠባበቅ ላይ ነው የምንገኘው፡፡

ሊግ፡- ባህርዳር ከተማ ለአዲሱ የውድድር ዘመን የያዘውን የተጨዋቾች ስብስብ በሚመለከት ምን ትላለህ? አሰልጣኛችሁስ በምን መልኩ የሚገለፅ ነው?

ሰለሞን፡- አሰልጣኛችንን ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱን በሚመለከት እስካሁን እንደተመለከትኩት ጥሩ ኮች ነው፤ አስተማሪም የሆነ ሰው ነው፤ ከእዛም ውጪ በወጣት ተጨዋቾች ላይ ያለው እምነትና ቡድኑም ጥሩ ኳስ እንዲጫወት እያሰበበት ያለው መንገድ ከወዲሁ እሱን በደንብ እንድረዳው እያደረገኝ ይገኛል፡፡ የተጨዋቾች ስብስባችንን በሚመለከት አሪፍ ስኳድ ነው ያለን፤ ክፍተት በነበሩብን ቦታዎች ላይ ተጨዋቾችን አምጥተናል፤ ከእነሱም ጋር በመሆን ጠንካራውን ክለብ ባህርዳር ከተማን ለመገንባት እየተዘጋጀን ይገኛል፡፡

ሊግ፡- የአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ስም ከአንደበትህ አይጠፋም፤ በእዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ይኖርሃል?

ሰለሞን፡- አዎን፤ ፋሲል ከሱፐር ሊግ አምጥቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሪምየር ሊግ ላይ እንድጫወት ያደረገኝ አሰልጣኜ ብቻ ሳይሆን እንደ ሁለተኛ አባቴም የምመለከተው አሰልጣኝ ነው፤ አቅሜን እንደተመለከተም ነበር በቋሚነት አሰልፎ ሊያጫውተኝ የቻለው፤ እሱ ከዛ ውጪም እንደ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱም ሌላው መምሬም ነውና በወጣት ተጨዋቾች ላይ ካለው እምነት በመነሳት ጥሩ አሰልጣኝነቱን ልናገርለት እፈልጋለው፡፡

ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ባህርዳር ከተማ በ2014 ምን እልምን ሰንቋል?

ሰለሞን፡- በሊጉ ተሳትፎአችን ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነን መገኘትና ከ1-3 ባለው ደረጃ ውስጥ ሆነን ማጠናቀቅ የእኛ ዋንኛው እልም ነው፤ ከተሰራ የማይቻል ነገር የለም፤ ፈጣሪም ይረዳናል እናሳካዋለን፡፡

ሊግ፡- በዓምናው ባስመዘገባችሁት ውጤት ተቆጭታችኋል?

ሰለሞን፡- እንዴት አንቆጭም! ምክንያቱም ጥሩና ጠንካራ ቡድን ነበረን፤ ቢያንስ የደረጃ ተፎካካሪ ሆነን ማጠናቀቅም ነበረብን፤ ከዛም በተጨማሪ ውጤት ያመጣሉ ከተባሉት ውስጥም የእኛ ክለብ አንዱም ተጠቃሽ ነበርና ያን ስላላሳካን ነው የተቆጨነው፡፡

ሊግ፡- ባህርዳርን በቤትኪንጉ ምን ውጤት አሳጣው? ከስህተቱ ተምሮ ለመምጣትስ ምን ተጨማሪ ነገሮችን አስቧል?

ሰለሞን፡- እግር ኳስ የብዙ ስህተቶች የድምር ውጤት ነው፤ በዓምናው ተሳትፎአችን ጎሎችን የማስቆጠር ችግር ነበረብን፤ በቀላሉ ግብም ይቆጠርብን ነበር፤ ሌሎች ተያያዥ ችግሮቻችንም ነበሩ ውጤቶችን ያሳጡንና ዘንድሮ ከእነዛ ሁሉ ክፍተቶች ተምረን በመምጣት ነው ለአዲሱ የውድድር ዘመን ተሳትፎ በጥንካሬያችን የምንቀርበው፡፡

ሊግ፡- እንደ ባህርዳር ከተማ ክለብ ተጨዋችነትህ ራስህን በምን አቋም ላይ አገኘኸው?

ሰለሞን፡- አሁን ለሶስተኛ ዓመት ለመጫወት ዝግጁ ነኝ፤ በእስካሁኑም የክለቡ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታዬም በራሴ ላይ ከዓመት ወደ ዓመት ለውጦችን እየተመለከትኩ ነው፤ በኳሱ ገና ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያልደረስኩ ቢሆንም ብዙ ለውጦች አሉኝ፤ በዘንድሮ የውድድር ዘመን ተሳትፎዬ ደግሞ ያሉብኝን ክፍተት ጎኖች በማረም ለክለቤ ጥሩ ነገር ለመስራትና ለብሄራዊ ቡድንም ዳግም ለመመረጥ ጥረትን አደርጋለው፤ በተለይም ደግሞ….

ሊግ፡- በተለይ ምን?

ሰለሞን፡- ለአፍሪካ ዋንጫ ላለፈው ቡድን ሀገሬን ወክዬ ብጫወት በጣም ነው ደስ የሚለኝ፤ ያ ባይሳካ እንኳን ለሌሎች ለምሳሌ በዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ላይና ወይንም ደግሞ በቀጣይነት ለሚደረጉትም የኢንተርናሽናል በርካታ ግጥሚያዎች ላይ መሳተፍ እፈልጋለው፡፡

ሊግ፡- ወደ ባህርዳር ከተማ አዳዲስ ተጨዋቾችም መጥተዋል፤ እነሱን በማላመድ ዙሪያ የሰራችሁት ስራ አለ?

ሰለሞን፡- በመሰረቱ ስፖርተኛ ለመተዋወቅ ብዙም ችግር የለበትም፤ የተለያዩ ክለብ ተጨዋቾችም ሆነን እንተዋወቃለን፤ የመጡት ተጨዋቾች ከእኛ ጋር እርስበርስ ለመላመድ ምንም አይነት ችግር አልነበረባቸውም፤ እንደውም ለምደውን ነው የመጡት፡፡

ሊግ፡- አንተ ተጨዋች ወይንስ ዝምተኛ?

ሰለሞን፡- ዝምተኛ ነኝ፤ እንደውም ሼመኛ፤ ብዙ ጊዜም ስፖርተኞች ቁጭ ባሉበት ቦታ ላይ ቀልድና ጨዋታዎች ሲኖሩም ለእኔ ስላለመድኩት ይከብደኛልና በዛ ደረጃ የምገለፅ ነኝ፤ በቀጣይነት ግን እኔም ተጨዋች ብሆን ደስ ይለኛል፡፡

ሊግ፡- በመጨረሻ…..?

ሰለሞን፡- ሁሉም ነገር የሚኖረው ሀገር ሰላም ስትሆን ነው፤ በመጀመሪያ ፈጣሪ አገራችንን ሰላም ያድርግልን፤ ይህን ካልኩ በዘንድሮ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎአችን ክለባችንን ውጤታማ አድርገን ደጋፊውን ለማስደሰት ተዘጋጅተናልና ለእዛ ያብቃን ነው የምለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P