Google search engine

“በዝምባቡዌ ላይ የተቀዳጀነው ድል ብዙ ነገሮችን  ለአገራችን  ይዞልን ይመጣል” ፋሲል ገ/ሚካኤል

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን  /ዋልያዎቹ/ ግብ ጠባቂ  ፋሲል ገ/ሚካኤል

በዓለም ዋንጫው ማጣሪያ የዚምባብዌ አቻችንን ድል ስላደረግንበት ጨዋታና በቡድኑ አባላቶች ዘንድ ስለተፈጠረው ስሜት

“ይህን ጨዋታ ያደረግነው ጥሩ እንቅስቃሴን አሳይተንበት ከነበረውና ቢያንስ ደግሞ አንድ ነጥብ ያስፈልገን ከነበረው የጋናው ጨዋታ ሽንፈት  የቀናት ልዩነት /ማግስታት/ በኋላ ያደረግነው ስለነበር የግድ ሶስት ነጥብ እንደሚያስፈልገን እርግጠኛ ሆነን ነበር ወደ ሜዳ የገባነው፤ ከዛም ባሻገር የአዲስ ዓመትም በኋል ነው መደሰት ይኖርብናል። ሌላው ሀገራችን ዛሬ ላይ ሰላምም አይደለችምና የጨዋታው ግጥሚያ ሊጠናቀቅ ከጫፍ በደረሰበት ሰዓት  ያገኘነውን የፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረን ያገኘነው  የድል ውጤት  ብዙ ነገሮችንም ይዞልን ይመጣልና  በውጤቱ በጣም ተደስተናል”።

በመጀመሪያው እና በሁለተኛው አጋማሽ ስለነበረው የጨዋታ እንቅስቃሴ

“በእንቅስቃሴም ሆነ ጫና በመፍጠሩ በኩል  በሁለተኛው አጋማሽ ላይ የበለጠ  ጥሩ ለመጫወት ብንሞክርም ቡድናችን ከመጀመሪያው አጋማሽ ጀምሮ መልካም የሚባል ጨዋታን ነው ሲያሳይ የነበረው።  እኛ ኳስን ይዘን ስንጫወት እነሱ  ከራሳቸው የሜዳ ክልል  በሀይ ፕሬስ ከተከላካይ ጀርባ በሚጣል ኳስ ነበር ለመጠቀም ሲሞክሩ የነበሩት። በዚህ ጊዜም አሰልጣኛችን ከሰጠን የጨዋታ ታክቲክ ውስጥ ኳሱን እርጋታ በተሞላበት መልኩ ፖሰስ አድርጋችሁ ተጫወቱ አትቻኮሉ ስላለን በያዘው እንቅስቃሴ ከዚህ ጨዋታ አንድ ነጥብ ይዞ ሊመለስ የተዘጋጀውን ዝምባዋብዌን አሸንፈን ልንወጣ ችለናል”።

ስለ ተጋጣሚያቸው አቋም

“እነሱ  ሀይ ቦል አጨዋወትን ነበር ሲጠቀሙ የነበሩት፤  በረኛቸውም ተከላካዮቻቸውም የሚያገኟቸውን ኳሶች ከእኛ ተከላካይ ጀርባ በመጣል ግብ ለማስቆጠርም ነበር ሲጥሩ የነበሩት። ከዛ ውጪ  ፈጣኖችም  ናቸው። ይህን ከጨዋታ በፊት በአሰልጣኛችን ስለተነገረንና ሜዳ ላይም ስላየነው ይህን አውቄ እኔም ኳሶቹን እየወጣው ስቀበላቸውም ነበርና በአጠቃላይ የተሰጠንን ታክቲክ መተግበር ስለቻልን ነው ጨዋታውን ማሸነፍም የቻልነው”።

የድል ውጤቱ ይገባቸው እንደሆነ

” አዎን ይገባናል፤ ምክንያቱም በኳስ ቁጥጥሩም ሆነ የግብ ዕድልን በመፍጠሩ በኩል ተሽለንም ተገኝተናልና”።

ዋልያዎቹን በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ በምን መልኩ እየተመለከታቸው እንደሆነ

“በአሁን ሰዓት ይሄ ቡድን  በተጋጣሚዎቹ ላይ የኳስ ብልጫን እየወሰደ  ያለና ከጨዋታ  ወደ ጨዋታም በጣም እየተሻሻለ የመጣ ቡድን ነው።  የአፍሪካ  እግር ኳስ ትልቅ ሀገር በሆነችው  ጋና  ላይ ያሳየው ጨዋታም ጥሩ ነበርና እኛ ከማንም እንደማናንስም ነው ያሳየነው። የተሻለ ነገርም አለን። ወደፊት ደግሞ ከዚ የበለጠ ብዙ ነገርንም  እናሳያለን”።

በዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታው  ይህ ቡድን የት ድረስ ይጓዝ እንደሆነ

“ውድድሩ ከመጀመሩ አንስቶ የእኛ  ዋንኛው እቅድ ምድቡን አንደኛ ሆነን በመጨረስ 10ሩ ምርጥ ቡድኖች የሚገቡበት ውስጥ መገኘት መቻል ነው። ያን ለማሳካትም ለእያንዳንዱ ጨዋታዎቻችን በቂ ትኩረትን ሰጥተን  ከፍተኛ ጥረትንም  እናደርጋለን”።

በወጣትነት ዕድሜው ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተሰልፎ ስለመጫወቱ

“ይሄን ዕድል እንዲሁ በፍጥነት አገኛለሁ ብዬ አልጠበቅኩም ነበር። የጋናው ጨዋታ ላይ ግን ተክለማርያም ሻንቆን /ጎሜዝን/  እረፍት ላይ ቀይሬው ስገባ አሰልጣኝ ውበቱ  ለእኔ በራስ መተማመኑ ላይ  ከፍተኛ  ኮንፊደንስ ሰጠኝ። አሁን ወደ ሜዳ የምትገባው በልምምድ ሰዓት ላይ የሰራነውን የታክቲክ ስራን መስራት ነው ብሎም ስለነገረኝ ያን በማድመጥና ደግሞም ሀላፊነቱንም ለመወጣት ራሴንም ዝግጁ ያደረግኩበት ሁኔታም ስለነበር  ደስ ብሎኝ በመጫወት የመጀመሪያ ግጥሚያዬን በጥሩ መልኩ ልወጣ ችያለሁ”።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this: