Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በፉከራ፣ በድሮ ስምና ዝና ብቻ ማንንም የሀገር ውስጥ አሰልጣኝ አንቀጥርም”“ሚቾ በምክትል አሰልጣኝነት ለማገልገል ከፈለገ መምጣት ይችላል”አቶ አብነት ገ/መስቀል (የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የቦርድ ሰብሳቢ)

በተለይ ለሊግ ስፖርት

በአለምሰገድ ሰይፉ

ፈረሰኞቹ አምርረዋል፡፡ በተለያዩ የውድድር ዓመታት የሊጉን የድል አክሊል ደጋግሞ በመድፋት ደጋፊዎቻቸውን ከልብ ማስፈንጠዝ የቻሉት ቅ/ጊዮርጊሶች ከቅርብ ዓመታት በኋላ ከዋንጫ ስኬት ጋር የተራራቁቢሆንም በክለቡየገዘፈ ክብርና ዝና ላይ ግን ምንም አይነት ድርድር የለም የሚል አቋም ይዘዋል፡፡

ለዚህም ነው በሀገሪቱ የእግር ኳስ ታሪክ ጣራ የነካ ስምና ዝና ያላቸውን ተጨዋቾች የዲስፕሊን ጥሰት ፈፅመው በመገኘታቸው ያለ ርህራሄ የታላቁን ክለብ መለያ አውልቀው እንዲሰናበቱ የተደረጉት፡፡ አንዳንዶች “ቅ/ጊዮርጊስ አሁን አሁን አንቀላፍቷል” የሚል እሳቤ ቢኖራቸውም የክለቡ የምንጊዜም የቁርጥ ቀን ልጅ የሆኑት አቶ አብነት ገ/መስቀል ግን ከዚህ የተለየ ሃሳብ አላቸው፡፡ እጅግ ከተጣበበ ጊዜያቸው ላይ የተወሰኑ ደቂቃዎችን መሰዋዕት በማድረግ ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ከሆነው ከጋዜጠኛ አለምሰገድ ሰይፉ ጋር ያደረጉት ቆይታየሚከተለውን ይመስላል፡፡

ሊግ፡– የ2014 የውድድር ዘመን የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ቅድመ ዝግጅት ምን ይመስላል?

አቶ አብነት፡- እንደሚታወቀው የ2014 የውድድርዘመን ቅድመ ዝግጅትን በ2013 አጋማሽ ላይ ነው የጀመርነው፡፡ ዋናው መለኪያችን ደግሞ የእግር ኳስ ክለባችን አቋም አጥጋቢ ሆኖ ስላላገኘነው በዚህ ረገድ ክፍተት ያለበትን ቀዳዳ ለመድፈን መስራት ከጀመርን 6 ወራትን አስቆጥረናል፡፡

ሊግ፡– በእነዚህ ወራቶች የተከናወኑትን ተግባራት ማወቅ ይቻለኛል?

አቶ አብነት፡- በሚገባ! ሰፊ የሆነ ጥናት በማድረግ ጥሩ ሊባል የሚችል ቅድመ ዝግጅት ነው፡፡ ተጨዋቾችን በተመለከተ ትኩረት ያደረግነው በወጣት ዕድሜ ክልል ላይ ያሉና በተለይ  በተለይ ደግሞ ክለቡ የሚያወጣውን የዲስፒሊን መመሪያ መተግበር በሚችሉት ላይ ነው፡፡ ሌላው እናንተም እንደምታውቁትና ተደጋግሞ እንደሚነገረው ወደ ክለባችን የሚመጣው የውጭ ሀገር አሰልጣኝ ሌሎች  ክለቦች ዝግጅት ጀምረው ውድድሩ ሊጀመር አካባቢ ነበር ሙያተኛው የሚመጣው፡፡ አሁን ግን ይህ ስህተት እንዳይደገም  በማሰብ ከአንድ ወር በፊት ቅ/ጊዮርጊስን የሚመጥን አሰልጣኝ ከብዙ ድካምና ልፋት በኋላ ከብዙ ተፎካካሪዎች እኛ ልቀን በመገኘት የአፍሪካ ክለቦችን በማሰልጠን ልምድ ያለውና የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን በሚገባ የሚያውቅ አሰልጣኝ አግኝተናል፡፡

ይሄን ማድረግ የቻልነው እንዲሁ በቀላሉ እንዳይመስልህ ከፍተኛና አድካሚ የሚባል ድርድር ነው ያደረግነው፡፡ ምክንያቱም አብዛኛዎቹ የውጭ ሀገር አሰልጣኞች ኢትዮጵያ ውስጥ መጥቶ የመስራት ፍላጎት የላቸውም፡፡ ምክንያቱም የሀገሪቱ ሊግ እጅግ ደካማ በመሆኑ ወደፊት የተሻለ ክለብ ለማግኘት የሚታዩበትን ዕድል ስለማይፈጥርላቸው ቀደም ብዬ እንደገለፅኩልህ እዚህ መጥቶ የመስራት ፍላጎታቸው አነስተኛ ነው፡፡ አሁን ግን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዲ.ኤስ.ቲቪ እየታየ በመሆኑ ምናልባት እዛ ሄደን አንዱን ክለብ ብናነሳ ተፈላጊነታችን ሊጨምር ይችላል ብለው በማሰባቸው ሂደቱ ስኬታማ መሆን ችሎ ኮንትራታችንን ጨርሰናል፡፡

ሊግ፡– አሁን እናንተ እያመጣችኋቸው ያሉትን ተጨዋቾች ማንነት አሰልጣኙ ያውቃል?

አቶ አብነት፡- አዎ፤ በተቻለ አቅም እንዲያውቅ እየተደረገ ነው፡፡ ስምምነታችንን ከጨረስን በኋላ አጠቃላይ የክለቡን ሂደት በቅርበት እየተከታተለ ነው፡፡ የተጨዋቾቹን ማንነት እንዲያውቅ በቪዲዮ የተደገፈ ዶክመንት እየመገብነው እንገኛለን፡፡ ከዚህ በተረፈ ያለው ነገር የእርሱ ስራ ነው፡፡ የሀገር ውስጥ ተጨዋቾችን በተመለከተ ከኮንትራት ውጪ የሆኑትንና ጊዮርጊስን ይመጥናሉ ብለን ያሰብናቸውን ለይተን ጨርሰናል፡፡ አሁን የሚቀረን ከውጭ ሀገር የምናስመጣቸው ተጨዋቾች ላይ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ላይ አሰልጣኙ ሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርግ እድሉን ስለሰጠነው በቅርበት እየተነጋገርን እየሰራንበት ነው፡፡ ከሁለቱ የአንዱ ተጨዋች ጉዳይ ጨርሰናል፡፡ ከዚህ በኋላ ከውጭ የምናስመጣው የሚቀረን ተጨዋች አንድ ብቻ  ይሆናል፡፡

ሊግ፡– እንደሚታወቀው የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ተደጋጋሚ የሻምፒዮንነት ክብርን በመጎናፀፍ ነው ተለይቶ የሚታወቀው፤ አሁን ግን ላለፉት አራት ዓመታት ከለመደው ታሪክ ወደኋላ እያፈገፈገ ነው፡፡ ከቅድመ ዝግጅቱ ባሻገር የዚህን ችግር መንስኤስ ቦርዱ በሚገባ መርምሯል?

አቶ አብነት፡- አዎ! በሚገባ መርምረናል፡፡ በዚህ የግምግማ ሂደት የውስጥና የውጭ ችግሮች እንዳሉ ነው የተገነዘብነው፡፡ ፌዴሬሽኑ ዋንጫው በየቦታው መዞርና መዳረስ አለበት የሚል አቋም ያለው ይመስላል፡፡ አንድ ጊዜ ለዚህ ቡድን፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ ለሌላ ክልል እያለ ስልጣኑን ለማራዘምና በየክልሎች ድጋፉን ለማብዛት በማሰብ ከእግር ኳሳዊ ይዘት ውጭ የሆኑ ችግሮች ተፈጥሮ ዋንጫ ያጣንበት ሁኔታም ተፈጥሮ እንደነበር እናውቃለን፡፡

በሌላ አንፃር ካየኸው በጥሩ ሁኔታ እንደዘንድሮ በነበረው ፉክክር በንፁህ መንገድ እንደፋሲል ከነማ አይነት ቡድን ተገቢውን የሻምፒዮንነት ክብር ማግኘቱ የሚገባው ነው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ እኛ ከሌሎች ክለቦች በተሻለ ሁኔታ ጥሩ ስብስብ ይዘን ውጤታማ መሆን አልቻልንም፡፡ እናም ከሻምፒዮኑ ለመራቃችን ሚስጥሩ ሃምሳ ሃምሳ ፐርሰንት ተካፍለን ኃላፊነቱን እንወስዳለን፡፡ ሁላችሁም እንደምታውቁት ዘንድሮ የሊግ ኮሚቴው ከመምጣቱ በፊት ፌዴሬሽኑ በችርቻሮ መልክ ዋንጫውን ሰጥቷል፡፡ ይህ የማንደባበቀው ሀቅ ነው፡፡ ይህን እውነታ በመረዳትም የራሳችን የሆነ የውድድር አካል ሊኖረን ይገባል በማለት ፍላጎታችን ተግባራዊ ሆኖ ዘንድሮ ጥሩ ፉክክር ታይቷል፡፡ እንደመጀመሪያው መቶ ፐርሰንት የተዋጣለት ነው ማለት ባይቻልም ከ86 ፐርሰንት በላይ አጥጋቢ ነገር ማየት ተችሏል፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን የታዩትንክፍተቶች በቀጣዩ ዓመት ያስተካክላሉ ብለን እናስባለን፡፡ በተለይ ዳኝነት አመዳደብ ላይ፤ አራት ተከታታይ ጨዋታዎችን ተመሳሳይ ዳኞች ሲመሩ የታየበትም ሁኔታ አለ፡፡ እናም ቀደም ብለህ ላነሳኸው ጥያቄ ማጠቃለያ ምላሽ ስሰጥህ ባለፉት ዓመታቶች ቅ/ጊዮርጊስ ከዋንጫ ጋር የተራራቀበት ምክንያት የእኛ ችግር ብቻ ሳይሆን የሌሎችም አስተዋፅኦ ተጨምሮበት እንደሆነ ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡

ሊግ፡– ሰሞኑን የወሰዳችሁትን ጠንካራ የዲስፒሊን ርምጃ ተከትሎ ሁለት አይነት አስተያየቶች ይደመጣሉ፡፡ አንዳንዶች የቦርዱን ውሳኔ ቁርጠኛ በማለት ሲያወድሱት አንዳንዶች ደግሞ በአንድ ጊዜ የክለቡን ቁልፍ ተጨዋቾች ማሰናበት ተፎካካሪ ክለቦችን በማጠናከር በአንፃሩ ጊዮርጊስን የበለጠ ማዳከም ነው ይላሉ፡፡ እርስዎ በዚህ ዙሪያ ምን ይላሉ?

አቶ አብነት፡- ደጋፊ ደጋፊ ነው፡፡ አንዱ ጭልጥ ብሎ አይኑን ጨፍኖ የሚደግፍ፣ ውጤቱ ላይ ብቻ አተኩሮ የሚደግፍ አለ፡፡ ሌላኛው ደግሞ ስም፣ ዝናና ክብር ጭምር ይዞ የሚደግፍ አለ፡፡ የእኛ አላማ ደግሞ ክብራችንና ማሊያችን እንዳይደፈርና ዲስፒሊን እንዲከበር ነው፡፡ ስማ አንድ እውነት ልንገርህ እኛ በአሁኑ ሰዓት ካለን የዋንጫ ብዛት አንፃር ዋንጫዎቹን የምናስቀምጥበት ቦታ አጥተናል፡፡ በቂ ዋንጫዎች አሉን፣ ታሪክም ሰርተናል፡፡ ስንፈልግ በብዛት፣ ሲያሻን በመደዳ፡፡ አሁንም እዛ ቦታ ላይ መመለስ ቀላል ነው፡፡ ክብራችንንና ዝናችንን ሸጠን እንደዛ ከምንሆን በወጣቶች ብንጫወት የተሻለ ነገር እናመጣለን፡፡ እነዛ ተጨዋቾች ከሁለት ዓመት በኋላ አርጅተው ይወድቃሉ፡፡ እኔ የማዝነው ያን ያክል አቅም ያላቸውና ለብሄራዊ ቡድን የሚጫወቱ ተጨዋቾች ሕይወታቸው ተበላሽቶ ወደፊት ባያደርገው ደስ ይለኛል፡፡ ካደረገው ግን መጥፎ ነው የምለው ሁሉ ነገር አክትሞ መንገድ ላይ እንዳይወድቁ ነው፡፡

ሊግ፡– አሁን ወደ ክለቡ ያመጣችኋቸው ተጨዋቾች የቅ/ጊዮርጊስ ማሊያን መልበስ ይከብዳቸዋል የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ በዚህ ሃሳብ ይስማማሉ?

አቶ አብነት፡- ይሄ አሁን የምትለው ነገር የስነ-ልቦና ዝግጅትን የሚፈልግ ነው፡፡ ራሳችንን በምንፈትሽበት ጊዜ የደረስንበት አንዱ ነገር በትክክልም የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ስብዕናና የማሊያ ፍቅር እንዲኖራቸው ለማስቻል የቀድሞ የክለቡን ተጨዋቾች ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ማስጠጋትና የተለያዩ የስራ ኃላፊነቶችን በመስጠት ወደ ክለቡ የሚመጡ አዳዲስ ተጨዋቾች ማሊያው እንዳይከብዳቸው ማድረግ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ወደ ጊዮርጊስ የሚገቡት እኮ ዕቃ ለመሸከም ሳይሆን ኳስ ለመጫወት ነው፡፡ ኳስ ደግሞ የሚፈልገው ጭንቅላትና ጥበብ ነው፡፡

በሌላ አንፃር ይከብዳል ሲባል አዎ! ከዝናው፣ ከደረጃው፣ ከታሪኩና ከውጤታማነቱ አንፃር እዚህ ክለብውስጥ ገብተህ ለመጀመሪያ ጊዜ ስትጫወት ሊከብድ ይችላል፡፡ ነገር ግን ቀደም ብዬ እንደገለፅኩልህ በስነ-ልቦና ረገድ በደንብ መስራት ከተቻለ ከላይ የተነሳው ፍራቻ ቦታ አይኖረውም፡፡ ከዛ ይልቅ ወደፊትም ቢሆን ቅ/ጊዮርጊስ በዲስፒሊን ረገድ አንዳችም ድርድር እንደማያውቅና ከቅ/ጊዮርጊስ በላይ ማንም ምንም እንዳልሆነ ሁሉም ጠንቅቆ ሊያውቀው ይገባል፡፡

ሊግ፡– ሌላው በእናንተ ላይ የሚነሳው ቅሬታ ቅ/ጊዮርጊስ በነጭ አሰልጣኝ ያመልካል፡፡ ለሀገር ውስጥ ሙያተኞች ዕድል አይሰጥም ትባላላችሁ፡፡ ለምንድነው የሀገር ውስጥ ሙያተኞችን የማትፈልጉት?

አቶ አብነት፡- ከአሁን በፊትም ተናግሬያለሁ፡፡ አብዛኛዎቹ የሀገራችን አሰልጣኞች ለሙያ ማሻሻያ ኮርስ ወደ ውጭ ሀገር የሄዱት የበርሊን ግንብ ሳይፈርስ ነው፡፡ ታዲያ እንዴት ነው ከእነዚህ ጋር ወደ ኋላ ሄደህ የሳይንሳዊ ስልጠና ምንነትን የምታመጣው? እኔ ከዛ ይልቅ የሚመስለኝ ወጣት አሰልጣኞቻችን በክረምት ወራት ወደ ውጭ ሀገር እየሄዱ ሙያቸውን የሚያሻሽሉበትና ኮርስ የሚወስዱበት ሁኔታ ቢፈጠር፤ ከዛ በተረፈ የካፍ፣ የፊፋና የአውሮፓ የፕሮ-ላይሰንስ የሚያገኙበት መንገድ ቢመቻች መልካም ነው፡፡ ኤ-ዋን እንኳን ባይደፍሩ ሲ-ውን ለመሞከር እየሄዱ ቢመጡ ጥሩ ነው፡፡ ለዛም ነው ቅ/ጊዮርጊስን ለኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች ለመስጠት የማንደፍረው፡፡ ከዚህ በፊትም ሞክረን አይተነዋል፡፡ ከማስተዳደሩ የበለጠ ሽምግልና መቀመጡ ነው የሚከብደው፡፡

ይሄን ለማድረግ ደግሞ ጊዜ የለንም፡፡ አንተም እንደምታውቀው በአሁኑ ጊዜ ስፖርቱም ልቆ ሄዷል፡፡ ሰዎቹ ደግሞ ቆመዋል፡፡ ለእዚህ ነው እንጂ በኢትዮጵያዊነታቸው ብቃት ያለው አሰልጣኝ ሆነው ቢመጡ በጣም ደስ ብሎኝ የምቀበለው ነገር ነው፡፡

ሊግ፡– ስለዚህ ቅ/ጊዮርጊስ መቼም ቢሆን ፊቱን ወደ ሀገር ውስጥ አሰልጣኝ አያዞርም እያሉኝ ነው?

አቶ አብነት፡- ለዘላለም ይሟጠጣል የሚባል ነገር የለም፡፡ ነገ ውጭ ሀገር ሄዶ በሚገባ ተምሮና ላይሰንሱን ይዞ በመምጣት ውጤት ማምጣት የሚችል አሰልጣኝ ካገኘን እሰይ ብዬና እጄን ዘርግቼ ነው የምቀበለው፡፡ ምክንያቱም በኢትዮጵያዊነቱ እኛንም ያኮራናልና፤ ነገር ግን ዝም ብሎ በፉከራ፣ በድሮ ስምና ዝና ማንንም የሀገር ውስጥ አሰልጣኝ አንቀጥርም፡፡

ሊግ፡– የሚቾ የዛምቢያን ቡድን መልቀቅና የናንተ ዝምታ ሲገጣጠም ብዙሀኖች ቅ/ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሚቾን መልሶ ሊያመጣው ነው ብለው አስበው ነበር፡፡ እውነት አስባችሁ ነበር? አሊያስ አባባሉ ስህተት ነው?

አቶ አብነት፡- ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ብዙ ነገር ይባላል፡፡ ነገር ግን የተወራውን ሁሉ እውነት ነው ብሎ መቀበል አስቸጋሪ ነው፡፡ አየህ እኛ ክለብ ውስጥ ሁሉን ነገር በጥንቃቄ ነው የምንሰራው፡፡ የተጀመሩ ነገሮች ፍፃሜ ካላገኙ በቀር መረጃዎች ስለማይወጡ ሁሉም በፈለገው መንገድ የመሰለውን ይላል፡፡ አሰልጣኝ ሚቾን በዚህ የውድድር ዘመን ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ለማምጣት ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደረግንም፡፡ ለአሰልጣኝ ሚቾ አቅምና ችሎታ ክብር አለን፡፡ ከእኛ ጋር በጋራ በሰራንበት ጊዜ መልካም የሚባል ለውጥና ውጤታማነትን ስላስገኘልን እናመሰግናለን፡፡ በተረፈ አሁን የእኛ ዋና አሰልጣኝ ሌላ ነው፡፡ ሚቾ በምክትል አሰልጣኝነት ለማገልገል ከፈለገ መምጣት ይችላል፡፡ በተረፈ አንተ ከላይ እየተባለ ነው ያልከው ነገር ሁሉ አሉባልታ እንጂ የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡

ሊግ፡– የቅ/ጊዮርጊስ አይነት ታላላቅ ክለቦችን በኃላፊነት ቦታ ላይ መምራት ትንሽ ይከብዳል፡፡ ከዚህ አንፃር አንዳንዴ ፈታኝ የሆኑ ችግሮች ሲደራረቡ ምነው ይህ ኃላፊነት ቢቀርብኝ ብለው ተማረው ያውቃሉ?

አቶ አብነት፡- ሲጀመር ተስፋ ብቆርጥ ኖሮ መሪም አልሆንም ነበር፡፡ በቁርጠኝነት ገብተህ መሪ ስትሆን ተስፋ መቁረጥ የሚባል ነገር የለም፡፡ እውነት ነው በስራ ሂደት የማይመጣ ፈተናና ችግር የለም፡፡ ከውጭ ይመጣል፣ ከውስጥህና ከጎንህ፣ አንዳንዴ ደግሞ ከብብትህ ስር ይወጣሉ፡፡ በአጠቃላይ አንተን ለማደናቀፍ የሚያርፍ ሰው የለም፡፡ በዛ ላይ የሀገሪቷ የፖለቲካ ትኩሳት በብዙ መልኩ ሊነካህ ይችላል፡፡ ያንን ሁሉ መቋቋምና ማለፍ በጣም ከባድ ነው፡፡ ወደዚህ ቦታ ደጋፊው መርጦኝ ስመጣ እንድሰራለት ነው፡፡ ያንን ለማድረግ ደግሞ ከፊቴ የሚጋረጡትን መሰናክልና ፈተናዎችን በማለፍ የተሰጠኝን ኃላፊነት በተገቢው ሁኔታ መፈፀም መቻሌን ማሳየት ይጠበቅብኛል፡፡

ሊግ፡– ባለፈው ዓመት የውድድር ዘመን የቻምፒየንስ ሊጉን ተሳትፎ ማሳካት ባትችሉ እንኳን ሁለተኛ ደረጃን ማጣታችሁ ቁጭት ውስጥ አልከተታችሁም?

አቶ አብነት፡- እውነት ነው በባለፈው ዓመት የውድድር ዘመን ሌላው ቢቀር በትንሹ ሁለተኛ ሆነን መጨረስ ይገባን ነበር፡፡ በራሳችን ጥፋትና በልጆቻችን የዲስፒሊን ግድፈት ምክንያት የጣልናቸው ነጥቦች የተፈለገውን ውጤት ስላላስገኘልን ቁጭቱ የበለጠ ለቀጣዩ ዓመት በእልህ እንድንሰራ አድርጎናል፡፡

በአጠቃላይ ግን አሁን ምንም በሌለበት ሁኔታ ዝም ብሎ ከማውራት ጊዜውን ጠብቆ ሁሉን ነገር ማየት ይሻላል፡፡ ከዚህ በተረፈ አሰልጣኙ ምን አይነት ውጤት እንደሚያመጣ አብረን የምናየው ይሆናል፡፡ ሌላው የሚመጡት አሰልጣኞች ከደጋፊውም ጋር ሆነ ከሚዲያው ጋር አንዳንዴ መስመራቸውን የሚስቱበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡

ከሚዲያው የሚጠበቀው ሀቁንና እውነቱን ለደጋፊውና ለስፖርት ቤተሰቡ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ ምክንያቱም ሁላችንም የምንማረው ከሚዲያው ነው፡፡ መገናኛ ብዙሃን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ድክመታችንን አጉልቶ በማሳየት የምንማርበት ተቋም በመሆኑ ይሄን እውነታ ከሚዲያው እንጠብቃለን፡፡ በአጠቃላይ ሚዲያው የሀገሪቱን ስፖርት ለማሳደግም ሆነ ለማቀጨጭ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ በእኛ በኩልም ስራችንን በአግባቡእንስራ ስህተትም ካለ በአግባቡ ይገለፅልን፡፡

ሊግ፡– የውጭ ሀገር ተጨዋቾች ግዢ ገደብን እንዴት ይመለከቱታል?

አቶ አብነት፡- ይህ ውሳኔ በጣም የሚገርምና የሚደንቅ ነው፡፡ ከመሬት ተነስቶ ከ5 ወደ 3 ዝቅ እንዲል የተደረገበት ውሳኔ ለምን እንደሆነ አልገባኝም፡፡ እንኳን ካለው ኮታ ተቀንሶ ይቅርና ከአሁን በፊት 5 የውጭ ሀገር ተጨዋች ኖሮን እንኳን ኳሊፋይ መሆን አልቻልንም፡፡ እነ ቲፒ ማዜንቤ 17 ተጨዋች አላቸው፡፡ የተቀሩት ደግሞ ስድስት፣ ሰባትና ስምንት ተጨዋቾች አሏቸው፡፡ ቁልቁል መውረድ ተፈልጎ ከሆነ በርህን ዘግተህ መቀመጥ አሊያም ያለነዳጅ ቁልቁል የቸርቸር ጎዳናን መጓዝ ነው፡፡ ለእኔ እስከሚገባኝ በአሁኑ ሰዓት ፌዴሬሽኑ እያደረገ ያለው ነገር ይህንኑ ነው፡፡

ነገ ማንም ቡድን ይሁን ፋሲል ከነማ፣ ኢትዮጵያ ቡና አሊያም ቅ/ጊዮርጊስ አፍሪካ ላይ የምንሄደው ኢትዮጵያን ወክለን ነው፡፡ እዚህ ያለውን የውስጥ ችግራችንን ለመፍታት ሲባል የሚወሰነው ውሳኔ ነገና ከነገ ወዲያ አፍሪካ ላይ ስንሄድ በተጓዝንበት አውሮፕላን ነው በጊዜ የምንመለሰው፡፡ እንደዚህ አይነቱ ውሳኔ በግብታዊነት ሳይሆን በሰል ባለ ሁኔታ ቁጭ ብለው ተሰብስበውና ጥናት ተደርጎ መሆን አለበት፡፡ አንተም እንደምታውቀው በየዓመቱ ከክለብ ወደ ክለብ የሚሽከረከሩት ተጨዋቾች አንድ አይነት ናቸው፡፡ አዲስ ተጨዋች የለም፡፡ ዛሬ የአንዱን ክለብ ማሊያ ለብሶ ነገ ደግሞ የሌላውን ይቀይራል፡፡ ኳሳችን ገና አላደገም፡፡ እናም ያንን ማሳደግ ሲገባን፣ ሁለተኛ የውጭ ሀገር ተጨዋች ባበዛህ ቁጥር ክለቡ ውስጥ ለመሰለፍ የሚኖረውን ፉክክር ማሳደግ ነው፡፡ እናም እዚህ አገር ውስጥ ልምድ ሳታገኝ ሄደህ ልምድ ካላቸው ጋር መጫወት ማለት አንድ አቅም የሌለው ቦክሰኛ ያለአቅሙ ገብቶ በአንድ ቡጢ ተዘርሮ ፎጣ ሲወረወርበት እንደማየት ነው፡፡

ሊግ፡– ለነበረን ቆይታ በሊግ ስፖርት ጋዜጣ አንባቢያን ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

አቶ አብነት፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P