Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በፋሲል ከነማ ላይ የድል ግቧን ሳስቆጥር ከድካም የተነሳ ደስታዬን በምፈልገው መልኩ አልገለፅኩም” “እኛን አሳምኖ ያሸነፈን ቡድን ማንም የለም፤ ሊጉን መምራት ነበረብን”     ወንድማገኝ ሀይሉ  /ሐዋሳ ከተማ/

 

ሐዋሳ ከተማ የአምናውን ሻምፒዮና ፋሲል ከነማን ማሸነፉ የሳምንቱ መነጋገሪያ ዜና ሆኗል፤  ቡድናቸውን በአብዛኛው በወጣት ተጨዋቾች የገነቡት የሁለት ጊዜ ሻምፒዮኖቹ  ያገኙትን የስኬት ድል ተንተርሶ ወደ መሪዎቹ ቡድኖችም በነጥብ ተቃርበዋል፡፡

በአሰልጣኝ ዘርዓይ  ሙሉ የሚመሩት ሐዋሳ ከተማዎች አሁን ላይ  አበረታች ውጤትን እያስመዘገቡ ሲሆን ቡድኑ ከእዚህ በላይም ሊጓዝ እንደሚችልና ለሻምፒዮናነትም እንደሚጫወቱ ፋሲል ከነማን ባሸነፉበት ጨዋታ ወሳኟን የድል ግብ ወደ መጨረሻዎቹ ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው  የአምናው የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተስፈኛው ከከብ ተጨዋች ወንድማገኝ ሀይሉ ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

ለሐዋሳ ከተማ በጥሩ ብቃቱ  በአማካይ ስፍራ ላይ የሚጫወተው ወንድማገኝ ሀይሉ ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ  ጋዜጠኛ  መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር  ስለ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የቡድናቸው ተሳትፎ፣ ስለ ራሱ የኳስ ህይወትና  በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ አናግረነው ተከታዩን ምላሽ ሰጥቶናል፤ ቃለ-ምልልሱም በሚከተለው መልኩ ቀርቧል፤ መልካም ንባብ።

የአምናውን ሻምፒዮና ስላሸነፉበት ጨዋታ

“ከፋሲል ከነማ  ጋር ያደረግነው ጨዋታ በጣም ከባድ ነበር፤ ግጥሚያውን ስላሸነፍንና እኔም የድሉን ግብ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች አካባቢ ስላስቆጠርኩ በጣም ደስ ብሎኛል”።

ለአሸናፊነት ስላበቃቸው  ሚስጥር

“ለማሸነፋችን ምንም የተደበቀ ነገር የለውም፤ በአንድነትና በህብረት ሆነን  ከመጀመሪያው ሰዓት አንስቶ እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ እያጠቃንም እየተከላከልንም ስለተጫወትን ነው ባለድል የሆንነው”፡፡

ፋሲል ከነማን  ከጨዋታው በፊት እናሸንፈዋለን ብለው አስበው እንደነበር

“ይሄ እኮ ኳስ ነው፤ ሁሌ ወደሜዳ የምትገባውም ለማሸነፍ ነው።  አሁን ላይ በሊጉ የሚገኙት ክለቦች በትንሽ ነጥብ ነው የሚበላለጡት፤ ቡድኖች ከበድ እያሉም ስለመጡ እኛ ለማሸነፍ ተጫውተን ድሉን አሳክተነዋል”።

በቤትኪንግ ፕሪምየር  ሊጉ  ቡድናቸው ስላለው ጠንካራ ጎንና ክፍተቱ

“ሁላችንም በህብረት መጫወት መቻላችንና አንዱ ሲያጠፋ አይዞህ የምንባባልበት መንገድ ጥሩ ነው፤ ከዛ ውጪ  ግጥሚያዎችን ለማሸነፍ ያለው ቁርጠኝነትም በመልካም ጎኑ የሚጠቀስልን ነው። በክፍተት ደረጃ ላነሳ የምፈልገው ደግሞ የእኛ ቡድን ደካማ ከሚባሉት አንድ አንድ ቡድኖች ጋር ሲጫወት የመዘናጋት  ሁኔታ ይታይበታል፤ ያም በመሆኑ  ለሁሉም ትልቅም ትንሽም ለሆኑት ቡድኖች እኩል እና አንድ አይነት ግምትን ሰጥተን ወደሜዳ የምንገባ ከሆነ  ቡድናችን ከእዚህም በላይ ከፍ ማለት ይችላል”።

ወደ ድሬዳዋ ከተማ  ከማምራታቸው በፊት  ሐዋሳ ላይ ስለነበራቸው የሊጉ ቆይታ

“በሐዋሳ  ከተማ  የነበረን የጨዋታ  ቆይታ  በውጤት ደረጃ  ካሰብነው የወረደ ቢሆንም በነጥብ ደረጃ ከመሪዎቹ ቡድኖች በሁለት እና ሶስት ነጥቦች ብቻ ርቀንበት ስለነበር  ጉዞአችን የሚከፋ አልነበረም”።

አሁን ላይ በድሬዳዋስ

“ወደ  እዚህ የሐዋሳውን  አለአግባብ የጣልናቸውን ነጥቦች ለማስተካከል ነው የመጣነው፤  እስካሁን ሶስት ጨዋታዎችን ስላሸነፍን ጅማሬያችንም ጥሩ ነው። በአጠቃላይ አምስት ጨዋታን ለማሸነፍም ነው የመጣነው፤ ቀሪዎቹን ሁለቱንም እናሸንፋለን ብለን እናስባለን”።

በቤትኪንጉ  ዘንድሮ ስለፈተናቸው ቡድን

“ብዙ ከባድ ጌሞችን አድርገናል፤ በተለይ ትላልቅ ከሚባሉት የአማራ ክልል ቡድኖች ጋር ማለትም ከባህርዳር ከተማና ከፋሲል ከነማ ጋር የተጫወትናቸው ለእኛ በጣም ፈታኝ ነበሩ”።

በእዚህ ዓመት ካደረጋችሁት ግጥሚያ  በጣም ያስቆጨህ

“አሰልጣኛችንን ዘርዓይ ሙሉን ጨምሮ  ሁሉንም የቡድኑን አባላት ባሳመነ መልኩ  እኛን  ዘንድሮ ያስቆጨን ግጥሚያ  የተሸነፍናቸውን በሙሉ ነው፤  በሁሉም  ነጥብ  በጣልንባቸው  ጨዋታዎች  አሳማኝ በሆነ ሁኔታ አይደለም ነጥቦችን የጣልነው፤ ውጤቶቹ ሁሉ ለእኛ  የሚገቡና በአንደኛ ደረጃም ላይ የሚያስቀምጠንም ነበር”።

ስለ ዘንድሮው ሐዋሳ ከተማ

“የእኛ ቡድን በታዳጊ ወጣቶች የተገነባና ክለቡም በእዚሁ የሚያምን ነው፤ ካሉት ልጆች ውስጥ እኔ ሲኒየር ነኝ፤ ጁኒየርም ነኝ በሚል የመበላለጥ ነገርም የሌለበት ክለብ ስለሆነም በዛ ደስተኛ ነኝ፤ በአንድነት እና በህብረት የሚያምን ቡድንም ነው ያለን”።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ዘንድሮ ጎላ ብሎ የተመለከትከው ተጨዋች

“ውድድሩ ገና ቢሆንም እንደ እኔ እይታ  አብሮኝ ከጎኔ የሚጫወተው መስፍን ታፈሰ /ጩንቄ/ አበረታች እንቅስቃሴ እያሳየ ይገኛልና የእኔ ምርጫ እሱ ነው”፡፡

ሐዋሳ ከተማ የሁለት ጊዜ የሊጉ ሻምፒዮና ነው፤ በዘንድሮ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ከእናንተ ምንን እንጠብቅ፡…..?

“በእዚህ ሰዓት  ምንም  ነገር ለማለት ጊዜው ገና ቢሆንም  እኛ አቅደን  የተነሳነው ከፈጣሪ ጋር ሻምፒዮና ለመሆን ነው፤ ያ ባይሳካ እንኳን ሊጉን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ባለው ደረጃ ላይ ሆነን ማጠናቀቅ እንፈልጋለን፤ ይህን ውጤት ለማሳካትም ከአንደኛው ዙር በኋላም የበለጠ ተጠናክረን እንቀርባለን”፡፡

ከፋሲል ከነማ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ወሳኟን የድል ግብ ስለማስቆጠሩ

“ጎሏን ሳስቆጥር  የማሸነፊያ እና  ግጥሚያውም ወደመጠናቀቁ የተገኘች ስለነበረች  በጣም ነበር ደስ ያለኝ፤  ያም ሆኖ ግን ድካም ላይ ስለነበርኩ ደስታዬን በምፈልገው መልኩ ልገልፀው አልቻልኩም”፡፡

ወደ  እግር ኳስ ተጨዋችነት  ህይወት ስላመራበት መንገድ

“በልጅነት ዕድሜዬ ላይ ነበር  በተወለድኩበትና ባደግኩበት የሐዋሳ ከተማ 03 ቀበሌ አካባቢ  የምወደውን ኳስ መጫወት የጀመርኩት፤  ቤተሰቦቼ ያኔ ትምህርትህን ተማር ቢሉኝም ኳስ መጫወቱንም አይከለክሉኝም ነበር፤  ያን ጊዜ ታዲያ በሰፈር ውስጥ በምጫወትበት ሰዓት አሰልጣኜ የነበረው ሲሳይ ደቦጭ ነበርና እኔ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደምደርስ ይናገር ነበር፤ ጠንክረህ ስራም ይለኝ ነበር፤ በእሱና በቤተሰቦቼ ድጋፍና ምክርም በመታገዝ ዛሬ ላይ ለእዚህ ደረጃ ለመብቃት ችያለውና ለእነሱ  ምስጋና ላቀርብላቸው እፈልጋለው”።

በእግር ኳሱ  ከእነሱ ቤተሰብ  ሌላ ስፖርተኛ እንዳለ

“ሁለት እህቶችና አንድ ወንድም ቢኖረኝም ስፖርተኛው ግን እኔ ብቻ ነኝ”።

ተወልዶ ያደገበት አካባቢ ስላፈራቸው ሌሎች ተጨዋቾች

“አሁን ካሉት ብዙ አሉ፤ ከሚታወቁት መካከልም ለሲዳማ ቡና እየተጫወተ የሚገኘው ቴዎድሮስ ታፈሰ እንደዚሁም ከእኛ ክለብ  ተጨዋቾች ውስጥ ፀጋ እና ሌሎች ደግሞ በሱፐር ሊግ ደረጃ የሚጫወቱ አሉ፡፡ ፍሬው ሰለሞን /ጣቁሩም/ ከእኛ አካባቢ ብዙም የማይርቅ ተጨዋች ነው”፡፡

በልጅነት ዕድሜው  አድንቆት ስላደገው ተጨዋች

“የኢትዮጵያን ኳስ  ያኔ  ወደ ሜዳ ገብቼ  አላይም ነበርና ከሀገር ውስጥ ተጨዋቾች  የማደንቀው ማንም የለም፤ ወደ ባህርማዶ ተጨዋቾች ስትመጣ ግን ያኔ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን እከታተል ነበር፤ የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ እንደመሆኔ ዋይኒ ሩኒን በጣም ነበር የማደንቀው፤  እሱ አርአያዬም ነው። ከሩኒ ሌላ ክርስቲያኖ ሮናልዶንም  አደንቀዋለው። ሁለቱ ተጨዋቾችም ናቸው ኳስን በጣም እንድወድም ያደረጉኝ”።

የኢትዮጵያን እግር ኳስ መከታተል ስትጀምርስ ማንን ተጨዋች አደነቅ

“ሳላህዲን ሰይድን በተለይ ለብሄራዊ ቡድን ሲጫወት እንቅስቃሴው ደስ ይለኝ ነበር”።

ከእግር  ኳስ ውጪ  የእረፍት ጊዜውን ስለሚያሳልፍበት በኋላ  ቀን ቀን በመተኛት ነው የማሳልፈው፤ ከዛ ውጪ  ደግሞ መሸትሸት ሲል ሰፈር አካባቢ ቁጭ በማለት ከጓደኞቼ ጋር እጨዋወታለው”።

ከሐዋሳ ከተማ ውጪ  ለሌላ ቡድን ተጫውቶ እንደሆነ

“ኸረ ለማንም ቡድን አልተጫወትኩም፤ ለሐዋሳ ከተማ ራሱ የተጫወትኩት ከቅርብ ጊዜ አንስቶ ነው፤ ለu-17 ለአንድ ዓመት ለu-20  ለአንድ ዓመት ብቻ ከተጫወትኩ በኋላም ነው የዋናውን ቡድንም በመቀላቀል የተጫወትኩትና ይሄን ስመለከት በኳሱ የመጣሁበት መንገድ በጣም ፈጣን ነውም ማለት ይቻላል”፡፡

በቤትኪንጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ስላስቆጠረው ጎልና ስለ መጀመሪያ ጨዋታው

“የመጀመሪያ ጎሌ አምና በፋሲል ከነማ 2-1 ስንሸነፍ  ያስቆጠርኩት ነው፤  በዛ ጨዋታ  የመጀመሪያ ግብ ማስቆጠር ደስ ቢልም ጨዋታውን እየተመራን ያስቆጠርኩት ግብ ስለነበር ደስታዬ ሙሉ አልነበረም፤ ከዛ በመነሳትም ሌላ ጎል  የማስቆጠር ፍላጎትም ነበረኝ።  የመጀመሪያ ጨዋታዬን በተመለከተ ደግሞ  ተቀይሬ በመግባት  ከሰበታ ከተማ ጋር አድርገን 3-1 የተሸነፍንበትን ነው፤  ለመጀመሪያ ጊዜ በመሰለፌ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር፤ በጨዋታው  እየተመራን ስለነበርም  ጥሩ ነገር ለመስራትም  እቅድ ነበረኝ”፡፡

ስለ ወደፊት እቅዱ

“የመጀመሪያው  ከክለቤ ሐዋሳ ከተማ ጋር ሻምፒዮና መሆን ነው፤ ከዛም ባሻገር ዓምና በሊጉ ተስፈኛው ኮከብ ተጨዋች ተብዬ ተሸልሜ ነበርና ዘንድሮ ደግሞ የዓመቱ ኮከብ ተጨዋች የመባል ከፍተኛ ፍላጎቱ አለኝ”።

ስለ ግለ ባህሪው

“ላወቅኩትና ለተግባባሁት ሰው በጣም ተጨዋች እና  ተግባቢ   ነኝ፤  ከዛ ውጪም  ሰው አክባሪ ነኝ”።

ስለ ቅፅል ስሙ

“ፎቼ  ተብዬ ነው የምጠራው፤ ስያሜውም የምግብ መጠሪያ ስም ነው”።

ስለ ቅርብ ጓደኞቹ

“በሰፈር ደረጃ ሀብታሙና ፀጋሀብ ሲሆኑ በክለብ ደረጃ ደግሞ መስፍን ታፈሰና ምንተስኖት ናቸው”።

እናጠቃል

“ከሐዋሳ ከተማ ጋር ዘንድሮ ጥሩ ጊዜን ማሳለፍ እፈልጋለሁ፤  በኳሱም  ዛሬ ላይ ለደረስኩበት ደረጃ እኔን በመምከርም በማሰልጠንም የረዱኝንና ለእዚህ ያበቁኝን  ሰዎች እና  ቅድሚያም ፈጣሪን ለማመስገን እፈልጋለሁ”።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P