Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

በፋሲሎች መቼም ቢሆን የምረሳ አይነት ተጨዋች አይደለሁም፤ ወደ ቀድሞ ስምና ዝናዬ ዳግም እመለሳለሁ” አብዱራህማን ሙባረክ /ግሪዳው/


በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/

የእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኑን በፕሪምየር ሊግ ደረጃ የመጀመሪያ ክለቡ ለነበረው ኢትዮጵያ ቡና በመቀጠል ደግሞ የከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪ ለነበረው ለአዲስ አበባ ከተማ ክለቦች በመጫወት አሳልፏል፤ ለብሔራዊ ቡድንም የመመረጥ እድልን አግኝቶ በቻን የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ላይም ተሰልፎ ተጫውቷል፤ ዘንድሮ ደግሞ በጉዳት ከቡድኑ ጋር በሜዳ ላይ ባይታይም የፋሲል ከነማ ክለብ ተወዳጅ ተጨዋችም ነው፤ ይሄ ተጨዋች አብዱራህማን ሙባረክ ሲባል ፋሲል ከነማን ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲሸጋገር በማድረጉ በኩል የተዋጣለት ተጨዋች እንደነበርም ይታወቃል፤ ከእዚህ ተጨዋች ጋር ሊግ ስፖርት በጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አማካኝነት ይሄን ተጨዋች በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ አናግራው ምላሹን ሰጥቷታል፡፡
ሊግ፡- የአንተ የትውልድ እና የእድገት ስፍራ አዲስ ከተማ ነው፤ ሰፈርህን እንዴት ትገልፀዋለህ?
አብዱራህማን፡- የአዲስ ከተማ ሰባተኛ አካባቢን እኔ የምገልፀው ብዙ ነገሮችን ያወቅኩበት እና ነገሮችንም በፍጥነት የተረዳሁበት ከዛም በተጨማሪ ደግሞ ለብዙ ነገሮችም ቅርብ የሆንክበት እና ምንም ነገር ቢፈጠር ሁኔታዎች ሁሉ አዲስ የማይሆንብህ ምርጥ ሰፈር ነው፤ በዛ ላይ ለመርካቶም አካባቢው ቅርብ ስለሆነም ስለንግድ እንቅስቃሴም ሆነ ስለሌሎች ማንኛውም ነገሮች በቅርብ ሁሉንም ነገርም ታውቅበታለክና የእዛ አካባቢ ተወላጅ እና ልጅ በመሆኔ ሁሌም ቢሆን ደስተኛ እንድሆንም ነው ያደረገኝ፡፡
ሊግ፡- ከመርካቶ አዲስ ከተማ የሚወጡ ሰዎች ብዙዎቹ ወደ ንግዱ ሙያ ላይ ነው የሚያመሩት፤ አንተ ግን በፍጥነት ወደ ኳሱ አመራ፤ ለእዚህ የተለየ ምክንያት አለ?
አብዱራህማን፡- ያን ያህል እንኳን የተለየ የሚባል ምክንያት የለኝም፤ ይሄ የሆነውም በአጋጣሚ ነው፤ የእኔ ቤተሰቦችም ሆኑ የአካባቢያችን ተወላጆች በንግድ ስራው ላይ የተሰማሩ ቢሆንም እኔ ግን ለኳስ ያለኝ ጥልቅ ፍቅር ነው ሙሉ ትኩረቴን እዛ ላይ እንዳደረግ አስችሎኝ የእግር ኳስ ተጨዋች የሆንኩት፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ዘመንህ ሲያበቃ ወደንግዱ ሙያ የምታመራ ይመስልሃል?
አብዱራህማን፡- አይቀርም፤ በእርግጠኝነት እንደ ቤተሰቦቼ ነጋዴ እሆናለው፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ተጨዋች እሆናለው ብለህ ነው ኳስን የጀመርከው?
አብዱራህማን፡- አዎን፤ የእግር ኳስን ለስሜት መጫወት ከጀመርኩ በኋላ ወዲያው ነው በፍጥነት ወይ ለኢትዮጵያ ቡና አለያም ደግሞ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ገብቼ እጫወታለው የሚል ስሜትን አሳድሬ ኳስን ስጫወት የነበርኩት፤ በኋላ ላይ ምኞቴና ፍላጎቴ አልቀረም ወደ ኢትዮጵያ ቡና ተተኪና የዋናው ቡድን ውስጥ ገብቼ ልጫወት ቻልኩ፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን መጫወት የጀመርክበት ሂደቶች ምንድን ነው የሚመስሉት?
አብዱራህማን፡- ኳስን ስጀምር መጀመሪያ ላይ በሰፈራችን አካባቢ ያሰለጥነን በነበረው የተሻለ ምንዳዬ የፕሮጀክት ቡድን ውስጥ ነው መሰልጠንና መጫወት የጀመርኩት፤ በመቀጠል ደግሞ በአሰልጣኝ አፈወርቅ ጉርሙ ይሰለጥን በነበረው እና ባለቤትነቱም አሁን ላይ የእግር ኳስ ፌዴሬሽናችን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በሆኑት የአቶ ዮሴፍ ተስፋዬ ቡድን በሆነው የቢኒ ትሬዲንግ ክለብ ውስጥ ነው ለአንድ ዓመት ያህል የሰራሁት፤ ከዛም ኢትዮጵያ ቡና ለተተኪው ቡድን በአሰልጣኝ ገዛኸኝ ከተማ አማካኝነት ምርጫ ያደርግ ነበርና የልጅነት አሰልጣኜ ተሻለ ወዳዛ ስለወሰደኝ ምርጫውን አልፍኩና ለቡድኑ ልያዝ ቻልኩ፡፡


ሊግ፡- የቢኒ ትሬዲንግ ፕሮጀክት ብዙ ተጨዋቾችን በማፍራት ለተለያዩ ክለቦች እንዲበቁ የሚያደርግ ነበር፤ ሌሎች ለጥሩ ደረጃ መድረስም የሚችሉ ተጨዋቾች ነበሩ ማለት ነው?
አብዱራህማን፡- አዎን፤ በፕሮጀክቱ ለብዙ ጊዜያቶች ባልቆይም በወንዶቹም በሴቶቹም ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾች ከዛ ፕሮጀክት ወጥተዋል፤ ለምሳሌ እኔን ጨምሮ ሀይደር ሸረፋ፣ ሰናይት ቦጋለን የመሳሰሉ ተጨዋቾችንም መጥቀስ ይቻላል፤ ያኔ እኔ በነበርኩበት ሰዓት ከ17 ዓመት በታች ለሆኑት ነበር ኳስን የምጫወተው፤ የቡናን እድልም ሳገኝ ወደዛም አመራው፤ ቢኒ ትሬዲንግ ሌሎች ኳስን የሚችሉ ሌሎች ተጨዋቾችም ነበሩበትና ያ ቡድን ቀጥሎ ቢሆን ኖሮ በርካታ ተጨዋቾችንም ለማፍራት ይችልም ነበር፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ቡና እስከዋናው ቡድን በማደግ ተጫውተሃል፤ በክለቡ ውስጥ የነበረ ቆይታህ በምትፈልገው አይነት ነበር?
አብዱራህማን፡- በፍፁም፤ በቡና የነበረኝ ቆይታ እንዳሰብኩት አይደለም የሆነልኝ፤ ለዛም የራሴ የሆኑም አንድአንድ ስህተቶችም ጭምር ነበሩብኝና ያ በክለቡ ውስጥ ብዙ ዘልቄ እንዳልጫወት እና ያሳደገኝንም ክለብ በደንብ ጠቅሜው እንዳልጫወትም ነው ያደረገኝ፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ቡና በነበረህ ቆይታ በትምህርት ሰጪነቱ አግኝቼዋለው የምትለው ጥሩ ነገር ምን ነበር?
አብዱራህማን፡- ያኔ ከስር አድጌ በነበርኩበት ሰዓት ላይ በዋናው ቡድን ውስጥ እንደ እነ ታፈሰ ተስፋዬ፣ መስዑድ መሐመድ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ፣ መድሃኔ ታደሰ፣ ሲሳይ ደምሴን የመሳሰሉ ተጨዋቾች ነበሩና ከእነሱ የተማርኳቸው ጥሩ ጥሩ ነገሮች ነበሩ፤ እነዛንም ከክለቡ ከለቀቀኩ በኋላም ነው ያወቅኳቸውና ቡና እያለው ብዙ ነገሮች እንዳመለጡኝም ጭምር ነው የተረዳሁት፡፡
ሊግ፡- ከኢትዮጵያ ቡና ለመልቀቅህ በዋናነት የምትገልፀው ምክንያት ምን ነበር?
አብዱራህማን፡- የእውነት ለመናገር ከክለቡ የወጣሁበትና እንድለቅም የተደረግኩበትን መንገድ አሁንም ድረስ ፈፅሞ አላውቀውም፤ በአጋጣሚም ነው ከዝግጅት እንደመጣን በቢሮ ውስጥ ሳልጠራና ምንም ነገርንም ሳያናግሩኝ ወደ ቡድኑ እንዳልመለስ እና ይሄም የአሰልጣኙ ጥላሁን መንገሻ ውሳኔም ነው ተብዬ ከክለቡ እንድለቅ የተደረግኩት፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡናን እንደለቀቅህ በአዲስ አበባ ከተማም ሆነ በፋሲል ከነማ ክለቦች ውስጥ ጣፋጭ የሚባል ጊዜያቶችን አሳለፍክ ልበል?
አብዱራህማን፡- በትክክል፤ መጀመሪያ ከቡና ስለቅ ጊዜው በጣም የረፈደ ስለነበር ወደ አዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ነው ያመራሁት፤ እዛም በነበረኝ የአንድ ዓመት ቆይታዬ ብዙ ጎሎችን ከማስቆጠር ጀምሮ ጥሩና ምርጥ የሚባል ጊዜን አሳለፍኩ፤ ቆይታዬም ለብሔራዊ ቡድን እስከመመረጥ ደረጃም አደረሰኝ፤ ፋሲል ከነማ ስገባ ደግሞ የበለጠ ነው የተሳካልኝ፤ በጊዜው ቡድኑን ማለትም 2008 ላይ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንዲገባም ትልቁን አስተዋፅኦም አበርክቻለው፤ ያ የፋሲል ከነማ ክለብ በጣም ጠንካራ ነበር፤ ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾችም በስኳዱ ውስጥ ነበሩ፤ እኔም በክለቡ ውስጥ ባለኝ ቆይታ በርካታ ግቦችን ከማስቆጠር ባሻገር የከፍተኛው ሊግ ኮከብ ተጨዋች ተብዬ የተሸለምኩበት ወቅትም ስለነበር ያ ጊዜ ፈፅሞም አይረሳኝም፡፡
ሊግ፡- በፋሲል ከነማ ባለህ የተጨዋችነት ቆይታህ ስምህ በአንድ ወቅት በተደጋጋሚና በቀዳሚነት የሚጠራ ሆኖ አልፏል፤ አሁን አሁን ግን በሜዳ ላይ ብዙ ስለማትታይ ያ ጉልህ ስምህ አልተረሳም…..?
አብዱራህማን፡- እኔንጃ፤ ተረስቷል ብዬ በፍፁም አላስብም፤ ፋሲሎችን በደንብ አድርጌና ጠንቅቄም ነው የማውቃቸው፤ በፋሲሎች መቼም ቢሆን የምረሳ አይነት ተጨዋችም አይደለሁም፤ ስለዚህም አሁን ላይ ካጋጠሙኝ አንድ አንድ ችግሮችና ጉዳቶችም ነፃ በመሆን በመልካም ሁኔታ ላይ ያለው ተጨዋች ስለሆንኩ በቀጣይ ጊዜው የኳስ ህይወቴ ወደ ቀድሞ ስምና ዝናዬ ዳግም መመለሴ የማይቀር ነው፡፡
ሊግ፡- ለፋሲል ከነማ በመጫወት ሜዳ ላይ ከታየህ ብዙ ጊዜያቶችን አስቆጠርክ፤ ለቡድኑ ላለመጫወትህ ምንድን ነበር ያጋጠመህ? ወደ ሜዳ መመለሱስ ላይ ያለህ ናፍቆት ምን ይመስላል?
አብዱራህማን፡- ወደ ሜዳ ተመልሼ ለፋሲል ከነማ መጫወት በጣም ነው የናፈቀኝ፤ ከሜዳ ለመራቄ ደግሞ ምክንያት የሆኑኝ ነገሮች የመጀመሪያው አንድ አንዴ በኳስ ህይወትህ ውስጥ ከኳስ ጀርባው የሚያጋጥሙህ ብዙ ነገሮች አሉና እነዛን በአህምሮ ተቀብሎ ለመጓዝ ሊያስቸግሩህና ሊጎዳህም ይችላልና ያ እንዳልጫወት አድርጎኛል፤ ይሄን ችግር ደግሞ በአጠገቤ ያሉ አንድአንድ አካላቶች ተረድተውልኝ ካስተካከልኩ በኋላ ደግሞ ጉዳት ገጥሞኝም ነበርና ያ ተደራራቢ ችግርም ሊሆንብኝም ችለዋልና እነዚህ ናቸው ከሜዳ ያራቁኝ፤ ሆኖም ግን በጊዜው ከአጠገቤ ብዙ ሰዎች ቢኖሩ ኖሮ ብዙ ነገሮችን ማለፍ ይቻልም ነበር፤ አሁን ላይ ግን አላምዲሊላ ሁሉም ነገር ተስተካክሎ ወደ ጥሩ ጤንነቴ ተመልሻለው፤ በኮቪድ 19 የሊግ ውድድሩ ስለተቋረጠ እንጂ በአንድ ሁለት ግጥሚያዎች ላይ ከጉዳቴ ስለዳንኩ በ18 ስብስቡ ውስጥ ተካትቼም ነበር፡፡
ሊግ፡- በእግርህ ላይ የደረሰብህ ጉዳት ከባድ ነበር ማለት ይቻላል?
አብዱራህማን፡- አሁን መጨረሻ ላይ አስተናግጄ የነበርኩት ጉዳት የእውነት ለመናገር ከሌላው ጊዜ ትንሽ ለየት ይል ነበር፤ ግን ፈጣሪዬ ዓላ ይመስገን ጉዳቱን ባደረግኩት ጥሩ ህክምናና በቤተሰቦቼም በኩል ጥሩ የሆነ እንክብካቤና ባህላዊ የሆኑ ነገሮችንም እንድጠቀም ስላደረጉኝ ዶክተሮቼ እረፍት አድርግበት ካሉኝ ጊዜ አስቀድሜ በመዳን አሁን ላይ ሊጉ በመጪው ዓመት ሲጀመር ወደ ሜዳ ለመመለስ ሙሉ ጤነኛም ሆኛለው፡፡
ሊግ፡- በፋሲል ከነማ ተጫውተህ ከፍተኛ ስምና ዝናን አትርፈሃል፤ ፋሲል ማለት ለአንተ ምን ማለት ነው?
አብዱራህማን፡- ፋሲል ከነማ ለእኔ ትልቅ የምለውን ደስታ ያገኘሁበት እና በጣም የምወደውም ክለቤ ነው፤ ምርጥ የጨዋታ ጊዜንም አሳልፌበታለው፤ እንደዛም ሆኖ አስቸጋሪ ጊዜያትንም አሳልፌበታለው፡፡
ሊግ፡- አስቸጋሪ ጊዜያቶቹ ምን ነበሩ?
አብዱራህማን፡- ከቤተሰብ ርቀህ ነው እዛ ሄደ የምትጫወተው፤ ጥሩ የጨዋታ ጊዜን እንዳሳልፍኩ ሁሉ ከሜዳ ስትጠፋ እና በሜዳ ላይም አንድአንድ ነገሮች አልሳካ ሲሉ መቼም ቢሆን ደስተኛ አትሆንምና እነዛ ናቸው አስቸጋሪ ጊዜያቶቹ ፤ ያን ደስታ ዳግም ለማግኘት ትህግስተኛ እና ጠንካራ መሆን ይኖርብሃል፤ እንዳዛም ሆኖ ደግሞ አንድአንድ ነገሮች አልሳካ ሲሉህም የዛን ክለብ ሁሉንም ቆይታ እንድታስታውስም ያደርግሃልና በፋሲል ከነማ ሁለቱንም ነገሮች ለማየት ችያለው፡፡
ሊግ፡- በኮቪድ 19 የእግር ኳስ ውድድሮች ተቋርጠዋል፤ እንደ አንድ እግር ኳስ ተጨዋች በአሁን ሰዓት ምን በመስራት ላይ ትገኛለህ?
አብዱራህማን፡- አብዛኛው ስፖርተኛ በቤቱ ውስጥ ነው የሚያሳልፈው እና እኔም ኪሎዬ እንዳይጨምር እና የተስተካከለ የሰውነት አቋምም እንዲኖረኝ የተለያዩ ስፖርቶችን በመስራት ነው ከቤተሰቦቼ ጋር የማሳልፈው፤ ከዛ ውጪም አልፎ አልፎ ወጣ ብዬም በአካባቢዬ ለትንፋሽ የሚሆኑ እንቅስቃሴዎችንም አደርጋለው፤ ፕሌይስቴሽንም እጫወታለው፡፡
ሊግ፡- ኮቪድ 19 ጠፍቶ ወደ እግር ኳሱ ዳግም ስለመመለስስ ምን ትላለህ?
አብዱራህማን፡- ኢንሽ ዓላ፤ ይሄ ክፉ ወረርሽኝ ጠፍቶ ዳግም ወደ ኳሱ የምንመለስበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን እርግጠኛ ነኝ፤ እስከዛው ግን አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረግን በመቆየት ያን ጊዜ እንጠብቅ፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ የምንጊዜም ምርጡ ተጨዋቾች ለአንተ እነማን ናቸው?
አብዱራህማን፡- ከባህር ማዶ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሲሆን ከሀገር ውስጥ ደግሞ ሳላህዲን ሰይድ ናቸው፡፡
ሊግ፡- እስከዛሬ ካስቆጠርካቸው ግቦች ውስጥ በቀዳሚነት ደረጃ ላይ የምታስቀምጣት?
አብዱራህማን፡- እሷ ግብ መቼም ቢሆን አትረሳኝም፤ ግብ ካስቆጠርኩ ከስምንት ወራት በኋላም ያገባዋት ነበረች፤ ዓምና 2011 ላይም ነበር ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በአዲስ አበባ ስታድየም በተጫወትንበት እና 1ለ1 በተለያየንበት ሰዓት ያስቆጠርኳት እና ጥሩ እና የወደድኳትም ግብ ነበረች፡፡


ሊግ፡- በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመንህ የሚያስቅህ እና የሚያዝናና ተጨዋች ማን ነው?
አብዱራህማን፡- በእግር ኳሱ ውስጥ ስትኖር ምንአልባት ያ ተጨዋች ከአጠገብህ ላይኖር ይችል እንደሆነ እንጂ የማያስቅህ ተጨዋችማ የለም፤ ሁሉም አስቂኞች ናቸው፤ እንደዛም ሆኖ ግን እንደ መሐመድ ናስርን የመሳሰሉ ተጨዋቾች ደግሞ በፋሲል ከነማ ቡድን ውስጥ አብረን ነበርንና የእሱ በአንተም ጉዳይ ላይ ይሁን በራሱ ጉዳይ ላይ ተንተርሶ ከአፉ የሚወጡት እና የሚያወራቸው ወሬዎች ቀጥ ያሉ ግልፅ የሆኑና እንደዚሁም ደግሞ የሚያስቁም ስለሆኑ እሱ አዝናኙ ተጨዋች ነው፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመንህ ለአንተ በጣም የቅርብ ጓደኛህ የሆነው ሰው ማን ነው?
አብዱራህማን፡- የእግር ኳስን ስጫወት ጀምሮም ሆነ ጉዳትን አስተናግጄ እስከነበርኩበት ጊዜ ድረስ ከእኔ ጎን ባለመጥፋት በሁሉም መልኩ አሁንም ድረስ ብርታት የሆነኝ ጓደኛ ቢኖር የእግር ኳስ ተጨዋቹ መሐመድ ከድሬ ወንድም የሆነው አብዱ ነው፤ እሱ በብዙ መልኩ ለእኔ ጥሩ የሆነም ሰው ነው፤ ከእሱ በተጨማሪም ሌላ ምርጥ የሆነ የእግር ኳስ ተጨዋች ጓደኛም አለኝ፤ ይስሀቅ መኩሪያ ይባላል፤ ይስሀቅ የሰፈሬ ልጅ እና አብሮ አደግ ነን፤ እንደ ወንድም ነው የምንተያየው፤ የቤተሰብ ያህልም ነው የምንቀራረበው፤ የእግር ኳስን በተለይ ደግሞ በፋሲል ከነማ ክለብ ውስጥ አብረንም ልንጫወት ችለናልና ሁለቱ ጓደኞቼ በኳሱ ብቻ ሳይሆን ስለ ህይወትም ብዙ ነገሮችን የሚነግሩኝና የሚያማክሩኝም ናቸውና ሁለቱ ለእኔ የተለዩ ናቸው፤ አመሰግናቸዋለውም፡፡
ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተመርጠህ የተጫወትክበት ጊዜ ነበር፤ ያኔ የነበረህ ስሜት በምን ደረጃ ይገለፃል?
አብዱራህማን፡- ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን አፍሪካ ዋንጫ ተመርጬ በተጫወትኩበት ጊዜ በውስጤ ተፈጥሮብኝ የነበረው የደስታ ስሜት በጣም ከፍ ያለ ነበር፤ ከሱዳን ጋር ተደርጎ በነበረው ጨዋታም ላይ ጎል እስከማስቆጠር ደረጃም ላይ ልደርስ ችያለውና ደስታዬ እጥፍ ድርብ ሊሆንልኝም ችሏል፡፡
ሊግ፡- በቀጣይነትስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዳግም ተመርጦ ስለመጫወትስ ምንድን ነው የምታስበው?
አብዱራህማን፡- ከዚህ በኋላ እንደዚህ አይነት እድሎችን በድጋሚ ለማግኘት ምንም ጥያቄ የለውም ለብሔራዊ ቡድን ለመጫወት የተሻለ ተስፋን ይዤም ነው የምንቀሳቀሰው፤ ይህን ተስፋ ጉዳት ከሜዳ አርቆኝ ስለነበር እንጂ ባለፈው ዓመት ላይ ጥሩ እየተጫወትኩና ጎሎችንም አስቆጥር በነበርኩበት ሰዓት ላይ እያለው አስቀድሜም ነበር ያቀድኩት፤ ስለዚህም ከዚህ በኋላ ዓላ ፈቅዶ እግር ኳሱ ይጀመር እንጂ ከእዚህ በፊት ከነበረኝ አቋም በብዙ መልኩ ተስተካክዬም ሀገሬን የማገለግልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡
ሊግ፡- ወደ ቤተሰብህ እናምራ ስለ እነሱ ምን ማለት ይቻላል?
አብዱራህማን፡- ቤተሰብ መስርቼ ከሶስት ዓመት በፊት በፍቅር ከምወዳት ባለቤቴ አንድ ልጅን አግኝቻለው፤ የልጅ አባትም ስለሆንኩ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡
ሊግ፡- ወደ እዚህ ምድር እንድትመጣ ያስቻሉህን ቤተሰቦችህንስ በምን መልኩ ትገልፃቸዋለህ? ወላጅ አባትህም በብስክሌት /ሳይክል/ ተወዳዳሪነት ስፖርተኛ እንደነበሩም ሰማን፤ ልክ ነው?
አብዱራህማን፡- አዎን፤ አባቴ የብስክሌት ስፖርት ተወዳዳሪ ነበር፤ ይሄን በታሪክም ነው ለማወቅ የቻልኩት፤ ለስፖርትም ልዩ ፍቅር ነበረው፤ ይሄን ተንተርሶም ሌሎች ሶስት ታላላቅ ወንድሞቻችንን ወደተለያዩ ስፖርቶች ማለትም ወደ ካራቴ፣ ውሹ እና የቦክስ ስፖርትም ላይ አሰማርቷቸውም ነበር፤ ከእነሱ ውስጥ እኔ ብቻ ነኝ በኳስ ተጨዋችነቱ ልጓዝም የቻልኩት፤ በአጠቃላይ የእኛ ቤተሰብ ስፖርትን የሚወድ እና የሚረዳዳም ነበርና ወደዚህ ምድር እንድመጣ ያደረጉኝን ወላጆቼን በእዚሁ አጋጣሚ በጣሙን ላመሰግናቸው እፈልጋለው፡፡
ሊግ፡- በቤተሰባችሁ ውስጥ ስንት ወንድም እና እህት አለ? የቤቱ ቀልደኛ እና አስቸጋሪውስ? በልዩ ባህሪያቱ የሚታወቀውስ ?
አብዱራህማን፡- በቤታችን አራት ወንድሞች እና ሁለት እህቶች ናቸው ያሉኝ፤ የቤቱ ቀልደኛና አስቸጋሪው ልጅም ታናሼ እስማሄል ነው፤ ሌላው ደግሞ በልዩ ባህሪያቱ የሚታወቀው እና ሁላችንንም የሚቆጣጠረው ደግሞ አሁን አግብቶ ከመውጣቱ በፊት በቤታችን ውስጥ የነበረው ከድር ሙባረክ /ጅንደላው/ ነው፡፡ እሱ ታላቄ ሲሆን እኛን በደንብ ለመቆጣጠር ከመፈለግ አኳያም በጣም እለኸኛ እና ትቢተኛም ነበር፡፡ ሲቆጣጠረንም ልክ እንደ ወላጅ አባታችንም ነበር፡፡


ሊግ፡- በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመንህ ከተመለከትካቸው ውስጥ መቼም ቢሆን የማትረሳው እና የሚያስገርምህ ነገር?
አብዱራህማን፡- ዓምና ለፋሲል ከነማ በምንጫወትበት ሰዓት ነው፤ ያኔ እኔና ጀማል ጣሰውን የመሳሰልን ተጨዋቾችም በተጠባባቂ ወንበር ላይ ነበርን፤ ከጨዋታው በፊት ጀማል ጣሰው የቡድናችን ድንቅ አማካይ ለነበረው ኤፍሬም ዓለሙ /ፍፁም ዓለሙ/ አሁን ላይ ለባህር ዳር ከተማ እየተጫወተ ይገኛል፤ አይዞሽ ዛሬ ጎል ታገቢያለሽ፤ እንዲህ እንዲህም አድርጊ ጎል አግብተሽም ወደ እኔም ትመጪያለሽ ብሎ አበረታታት እና ሜዳ ከገባች በኋላ ልክ ጎል እንዳስቆጠረች በቀጥታ እኛ ወደነበርንበት የተጠባባቂ ወንበር ነው የመጣችው ጀማልም ደስታውን በመግለፅ እጁን እንደዘረጋ ኤፍሬምም ከስር እግሩ ስር ገብታ ስታቅፈው እና ወደላይም አንስታው ልትጨፍር ስትልና ስታነሳው አልተጠባበቁም ነበርና ጀማል የወደቀው አደገኛ እና የሚያሳቅቅ አይነት አወዳደቅ መቼም ቢሆን አይረሳኝም፤ ጀማል ወደ ታች በጭንቅላቱም ነበር የወደቀው፤ ሙሉ ስታድየሙም ነው የደነገጠው፤ እኛም ኤፍሬምን ልናቅፈው ብለን ሄደን ጀማል ሲወድቅ ደንግጠንም በመሳቀቅ ነበር ወደ ወንበራችንም ተመልሰን የሄድነው፡፡
ሊግ፡- ጀማል በቀልደኛ ተጨዋችነቱ ሁሌም ይታወቃል፤ በእናንተ ክለብ ውስጥስ?
አብዱራህማን፡- አዎን፤ እኛም ጋር በጣም ቀልደኛ ነው፤ ምን እሱ ብቻ በብዙ ነገርም የሚገርም እና ልትወደው የምትችለው አይነትም ተጨዋች ነው፤ በተለይ ደግሞ ቀልዱ ላይ አንድ ነገር ስትለው እሱ የሚሰጥህ ምላሽ አንተ ከምትጠብቀው እና ከምትገምተው አይነትም በላይ ተቃራኒ በሆነ መልኩም ነው ወዲያው በፍጥነት በሚያዝናና መልኩም ምላሽም የሚሰጥህና በዛ ደረጃ እሱን አትጠብቀውም፡፡ ከዛ ባሻገር እሱ ብዙ ነገሮች ላይ ይሳተፋል፤ ባህሪውም ለስለስ ያለ እና አስቸጋሪ ያልሆነ ሰውም ነው፤ ቶሎም ሰዎች ውስጥ የመግባት አቅምም አለው፤ ፋሲል ከነማ ውስጥ ውጤት እንዲኖር የእሱ አስተዋፅኦም የሚጠቀስ ነው፤ ከዛ ውጪም ከእኔም ጋር ጥሩ ግንኙነት ያለው ተጨዋች ስለሆነም ለእሱ ከፍተኛ አክብሮትም አለኝ፡፡
ሊግ፡- በአንድ ወቅት ከፋሲል ከነማ በመውጣት ወደሌሎች ክለቦች ልታመራ ስትዘጋጅ አንድ ሰው የሆነ ነገር አለህ ፤ ስለ እሱም ብዙ ብለናል፤ ያን ሁኔታ እስኪ ከራስህ አንደበት ብንሰማው?
አብዱራህማን፡- ለፋሲል ከነማ በምጫወትበት ጊዜ ጥሩ ጊዜን ነበር ያሳለፍኩት፤ ቡድኑን ወደ ፕሪምየር ሊግ ከማሳለፌም ባሻገር በርካታ ግቦችንም ለቡድኑ አስቆጥር ነበር፤ ይሄ ደግሞ ከፍተኛ ተወዳጅነትን በክለቡ ደጋፊዎች ዘንድ አትርፎልኝ ስለነበር የብዙ ክለቦችንም ቀልብ መሳብ ቻልኩ፤ ያኔም ቡድኖቹ እኔን ፈልገው ሊወስዱኝ ፍላጎትን ባሳደሩበት እና ስሜም ከአንድአንድ ክለቦች ጋር በሚነሳበት ሰዓት የፋሲል ከነማው አንዱ ደጋፊ ወደ እኔ መጥቶ “አንተማ ወደሌላ ክለብ ከምትሄድ፤ ብርም ከሆነ የምትፈልገው ፤ አንጥፌ ለምኜም ቢሆን በክለቡ ውስጥ አስቀርሃለው” ነበር ያለኝና ይሄን ፈፅሞ አልረሳውም፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ…..?
አብዱራህማን፡- ከሁሉ በፊት በጣም ማመስገን የምፈልገው አንድአንዴ ይመስልህና ውጪ ውጪ ያለውን ብቻ ነው የምታየው፤ ስለ ሰዎች ሁሉንም ነገር የምታውቀው ግን በችግርህ ጊዜ ነውና ያኔም ብዙ ነገሮችንም ትረዳለህ፡፡ ስለዚህም ለእኔ ከፈጣሪ በታች ቀድሜ ልጠራቸው እና ላመሰግናቸው የምፈልጋቸው ሰዎች ቤተሰቦቼን ነው፤ ቤተሰቦቼ ለእኔ በህይወቴ ትልቁን ውለታ የፈፀሙልኝ ናቸው፤ በችግር ባሳለፍኩባቸው ያለፉት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥም ከጎኔ በመሆን እንደ ቤተሰቤ ቅድሚያውን የሚወስድም ማንም የለም፤ በተለይ ደግሞ በጉዳት ላይ በነበርኩበት ሰዓት እህቴ ሸምሲያ ሙባረክ ታምሜ ሆስፒታል በተኛሁበት ሰዓት ብዙ ነገሮችን ታደርግልኝም ነበር፤ መላው ቤተሰቦቼ እኔን ከመደገፍ ውጪ በጣም መጨነቅ መቻላቸው በራሱ ትልቅ ዋጋም ነበረውና ያን ጭንቃታቸውን መቼም ቢሆን የምረሳው አይደለሁም፤ ሌላው በፋሲል ከነማ በነበርኩበት ሰዓት ከክለቡ ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ ነበርና ብዙ ስህተቶች እንዳይኖሩ፤ ከዛ ውጪም ክለቡም እኔም እንዳንጎዳ ሚዛናዊ በሆነ የአካሄድ ሁኔታ ነገሮችን በማስተካከል ሁለታችን እንድንስማማ ያደረገውን የቡድኑን ቁልፍ ሰው ሀብታሙ ዘዋለምንም እንደ ቤተሰቦቼ ሁሉ በጣሙን ማመስገንም እፈልጋለውኝ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P