Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ተስፋ የማይቆርጥ ቡድን ስላለን ለኢንተርናሽናል ጨዋታ ማለፋችን አይቀሬ ነው” “የሳላህዲን ሰይድ ወደ ቡድናችን መምጣት የሲዳማ ቡናን የዋንጫ ተፎካካሪነት ይበልጥ ከፍ  አድርጎታል” ሙሉዓለም መስፍን /ሲዳማ ቡና/

“ተስፋ የማይቆርጥ ቡድን ስላለን ለኢንተርናሽናል ጨዋታ ማለፋችን አይቀሬ ነው”

“የሳላህዲን ሰይድ ወደ ቡድናችን መምጣት የሲዳማ ቡናን የዋንጫ ተፎካካሪነት ይበልጥ ከፍ  አድርጎታል”

ሙሉዓለም መስፍን /ሲዳማ ቡና/

የሲዳማ ክልል  ተወካዩ ሲዳማ ቡና  በኢትዮጵያ  ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ  የዘንድሮ  ሻምፒዮና የራሱን አቋም ከጨዋታ ወደ ጨዋታ በማሻሻል  ጠንካራ  የሊጉ ተፎካካሪነቱን  እያሳየ ይገኛል።

ሲዳማ ቡና በእዚህም  የውድድር ዘመን  ምንም እንኳን  በሊጉ መሪ ቅ/ጊዮርጊስ  በሰፊ ነጥብ በመበለጥ በ ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ከእዚህ በኋላ በሚደረጉት  የሊጉ ጨዋታዎች ላይም  ከተቻለ  እስከ መጨረሻዎቹ ጨዋታዎች ድረስ  ዋንጫውን ለማንሳትና ያ ካልተሳካ ደግሞ ሁለተኛ በመውጣት በአፍሪካ ክለቦች ደረጃ ለመሳተፍ  እንደሚጫወትም  ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ ከአዘጋጁ ጋዜጠኛ መሸሻ  ወልዴ  /G .BOYS/ ጋር  በነበረው ቆይታ ገልጿል።

ሲዳማ ቡና በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ  ተሳትፎው ዛሬ የሊጉን መሪ ቅ/ጊዮርጊስን  የሚገጥም ሲሆን ይህን ጨዋታን በተመለከተና በቡድኑ አጠቃላይ አቋም ዙሪያ የቡድኑ ተጨዋች የሆነው ሙሉዓለም መስፍን /ዴኮ/ ከጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ጋር  ቆይታን አድርጎ የሰጠው ምላሽ በሚከተለው መልኩ ቀርቧል፤ ተከታተሉት።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሰበታ ከተማን ድል ስላደረጉበት ጨዋታ

“በመጀመሪያው አጋማሽ እነሱ ከፍተኛ የኳስ ቁጥጥር  ብልጫን  ወስደውብን ነበር፤  ምንአልባትም  ያን ሊያሳኩት እና ተግባራዊ ሊያደርጉት  የቻሉትም አስቀድመን ጎል  ስላስቆጠርንባቸው በእዛ ተነሳስተው ሊጫወቱ ስለቻሉና  እኛም ባገባነው ጎል ለመረጋጋት ስላልቻልንም  የመጀመሪያው  አጋማሽ በእዚሁ መልኩ ተጠናቋል።

ከእረፍት በኋላ በነበረው ጨዋታ ላይ  ደግሞ  የእኛ ቡድን በተከታታይ  ግጥሚያች ላይ  ጥሩ እና አበረታች  ውጤትን ከማስመዝገቡ ባሻገር  እያንዳንዱን ግጥሚያዎች  እንረታለን በሚል በጥሩ  የአሸናፊነት መንፈስ ላይ ስለነበርንና የስነ-ልቦና የበላይነቱንም በእነሱ ላይ ስለወሰድን   ከእዛም  ውጪ   ሁለተኛዋን  ግብ ስናስቆጥርም  ግጥሚያውን በተወሰነ መልኩ እንድንቆጣጠር  ስላደረገንና   የተጨዋቾች ቅያሪው ላይም እነሱ በመጀመሪያው አጋማሽ እንዳደረጉት በሁለት ስኪመር የመጫወትን ሁኔታም  እኛም ስለተጠቀምንበትና ወደፊት በመጫወትም ሶስተኛዋን ግብ እንድናስቆጥርም ስላደረገን አጠቃላይ  የጨዋታው እንቅስቃሴ ይሄን ነበር የሚመስለው”።

የድሉ ውጤት ለእነሱ  ይገባቸው እንደሆነ

“አዎን፤ የአሸናፊነቱ  ውጤት  ለእኛ  ስለሚገባን ነው  ባለድል  የሆንነው። በእግር ኳስ አንዳንዴ ጥሩ ሆነህም አታሸንፍም። በነጥብ እታች የሆነ  ቡድንም ሊያስቸግርህም ይችላል። ሰበታ ከተማን አሁን ካየከው በእንቅስቃሴው ጥሩ ነው፤ ከማንም የማይተናነስ ቡድንም ነው። እነሱን የኳስ ባህሪው ሆኖ ነጥብ አሳጣቸው እንጂ መጥፎ የሚባሉም አልነበሩምና እኛ በሁለተኛው አጋማሽ  ላይ  የተለየ ሆነን ስለቀረብን ነው ያሸነፍነው”።

በተከታታይ ጨዋታዎች ግጥሚያዎችን እያሸነፉ ስለመሆናቸው

“በዋናነት አሰልጣኛችን የሚሰጠንን   ጥሩ ልምምድ  በአግባቡ ስለምንሰራ   ነው  የእሱ እገዛ አስፈልጎን  ባለ ድል የሆንነው።   የእሱ አሰልጣኛችንምጰ  የተቃራኒ ቡድን አቋምን ጠንቅቆቆ ማወቁና ከእዛም ባለፈ  ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾች ቡድኑ  ስላሉትና ሳላህዲን ሰይድን ለማምጣት መቻላችንም ነው የአጥቂው  ክፍልን በጎል ማግባቱ ላይ እያገዘው በመሆኑና የተከላካይ ክፍሉም ላይ  ጠንካራና  ጥሩ በመሆኑ  የሳላህዲን ሰይድ መምጣትም  የቡድኑን ለዋንጫው ፉክክር የመጫወት መጠኑንም  ይበልጥ ከፍ ስላደረገልንሞ እነዚህ ሁኔታዎች ስለተደማመሩም ነው ለድሉ ልንበቃ የቻልነው”።

ሲዳማ ቡና  እንደ አንድ ቡድን ምን ይጎድለዋል

“አሁን ላይ እንኳን ቡድኑ በሁሉም መልኩ የተሟለ ሁኔታዎች ላይ ስለሚገኝ  የጎደለው ነገር ምንም  የለም፤ ቀደም ሲል ግን የአጥቂው ክፍል ላይ ይገዙ ቦጋለን በልምድም ሆነ በሌላ ነገር የሚያግዘው ተጨዋች ስላልነበርና  በአንድ አንድ ጨዋታዎች ላይም በተደራራቢ ግጥሚያዎች  ከድካም የተነሳ የጎል ዕድሎችን እያገኘን የምንስትባቸው  አጋጣሚዎችም ስላሉ ያ ነበር ጉድለታችን። አሁን ግን ወደተሟላ ብቃት ላይ ነው የምንገኘው”።

ሳላህዲን ሰይድ ወደ እናንተ ቡድን ሲያመራ ይሄንን ያህል ይጠቅመናል ብላችሁ አስባችሁ ነበር?

“አዎ፤ ካለው ችሎታና የተካበተ ልምዱ አኳያ  እንደዚሁም ደግሞ በቅ/ጊዮርጊስም አብረን የመጫወት አጋጣሚውን ስላገኘንና ስለ እሱ ችሎታም  አድርጌ ጠንቅቄ ስለማውቅ   ወደ  እኛ ቡድን እሱ  ሲመጣ  ምንም ጥያቄ የለውም  በደንብ  አድርጎ እንደሚጠቅመን  እናውቅ ነበር። ሳላ ጉዳት ካላጋጠመው በስተቀር በጣም ምርጥ አጥቂ ነው፤ ጉዳት ላይ ሆኖ ሲጫወት ራሱ ይጠቅምሃል።ጎል ላይ ምህረት የለሽ ነው። የእሱ መምጣት የተቃራኒ ቡድን ተጨዋቾችን ያስጨንቃል፤  ለሌሎች ተጨዋቾችም ክፍተት በመፍጠር እገዛን ያበረክታል። እሱ ጎል በማስቆጠሩ ላይ እንደሚጠቅመን እኛ ብቻ ሳንሆን አሰልጣኙና የቡድኑ አመራሮችም አስቀድመው የሚያውቁት ነገርም ስለነበር ነው ሊያመጡት የቻሉትና የእሱ  መምጣቱን በደስታ ነው የተቀበልነው፤ ጠቃሚ ተጨዋችነቱንም ይኸው በሜዳ ላይ እያስመለከተንም  ይገኛል”።

ሳላህዲን ሰይድ ከሰበታ ከተማ ጋር በነበራችሁ ጨዋታ ሀትሪክ ሰርቶ  ጎል ካስቆጠረ  በኋላ  ያላችሁ ነገር ነበር?

“እሱ በጨዋታው  ላይ  ለእኛ  ይለን  የነበረው  ሌላም ጎል እናስቆጥራለን ኳሱን ወደፊት አድርገን እንጫወት ነው”።

በሲዳማ ቡና ክለብ ውስጥ ደጋግመህ ከመጫወትህ አንፃር ለአንተ ምርጡ የጨዋታ  ጊዜ /ሲዝን/ የነበረው የትኛው ነው?

“ለእኔ  ምርጡ  የጨዋታ  ጊዜዬ  የነበረውን  ይሄ   ነው ብዬ ለመናገር ቢከብደኝም ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ከማምራቴ በፊት በ2007 ላይ  ሲዳማ ቡና በጣም ጠንካራ ነበርና በእዛ ቡድን ውስጥ የነበረኝን  ቆይታ  ነው  በጣም  ምርጡ የምለው”።

በ2007 ሲዳማ ቡና የሊጉን ዋንጫ ሊያነሳ ወደሚችልበት ሁኔታ ተቃርቦ ነበር። ግን በቅ/ጊዮርጊስ የተሸነፋችሁበት ጨዋታ  ያን ዕድል እንድታጡ አንዱ ምክንያት ሆኗችኋል። ያኔ አንተ ለሲዳማ ሳላህዲን ደግሞ ለቅ/ጊዮርጊስ ነበር የምትጫወቱት አሁን ላይ በአንድ ቡድን ውስጥ ከመገናኘታችሁ አኳያ ጨዋታውን ያነሳችሁበት ሁኔታ አለ

“ስለ እሱ ጨዋታ በተደጋጋሚ ጊዜ  በሌላም ወቅት ላይ  አውርተናል። ግጥሚያውን 0-0 አጠናቀን ብንመለስ ኖሮ ለዋንጫው ዕድሉ ይኖረን ነበር። ግን እነሱ በሳላ አማካኝነት ያስቆጠሩት ግብ ባለድል አድርጓቸው የዋንጫው ባለቤት ለመሆን ያ ግጥሚያ ምክንያት ሆኖ አግዟችኋል”።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ አሁን ላይ ምን ነገርን ሰርታችሁ በመምጣታችሁ ነው ወደ ለውጥ ልትመጡ የቻላችሁት?

“ከሁሉም በላይ ለውጥ ያመጣነው በኮቺንግ ስታፉ እና የክለቡ ማኔጅመንት አካባቢ  አንዱን ተጨዋች ከሌላው ማበላለጥ ሳይኖር ሁሉንም ተጨዋች  እኩል በሆነ መንገድ በማየት ተጨዋቹን አንድ የማድረግ የማኔጅመንት ስራ ስለተሰራ ነው ይሄ የውጤት ለውጥ ሊመጣ የቻለው። ከዛ  ውጪም  በተጨዋቾች  መካከልም መከፋፈል  እንዳይኖርም ስለተደረገ  እና የአንድ አሰልጣኝ ቡድንን የሚመራበት መንገድም ትልቅ ዋጋ  ስላለው በእዚህ በኩል ደግሞ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌ በሚሰጠው ስልጠናና የማኔጅመንት ብቃቱም ምርጥ አሰልጣኝ ስለሆነም በዋናነት የእሱ ስራም ነው ትልቅ ዋጋ  ኖሮት  ለለውጣችን በምክንያትነት የሚጠቀሰው”።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ከመሪው ክለብ ቅ/ጊዮርጊስ በነጥቦች ተበልጣችሁ ከመራቃችሁ አንፃር የሊጉን ዋንጫ የማንሳት ዕድሉ ይኖራችኋል….?

“ዋንጫ የማንሳት ዕድላችን  በርካታ ጨዋታዎች ከመቅረታቸው አኳያ አልተሟጠጠም። ዕድሉ የለም አክትሟል ብሎ ለመደምደምም በጭራሽ አይቻልም። ያንን ዕድሉን ለመጠቀም  ግን ከእኛ በርትቶ መስራትና ለእያንዳንዱም ቀሪ ጨዋታዎች  ከፍተኛ ትኩረትም መስጠት ይገባናልና ዋንጫ የማንሳት ዕድሉ በሚገባ  ነው ያለን”።

ዛሬ ቅዳሜ የቀድሞ ቡድንህን በተቃራኒነት ልትገጥም ነው፤ ምን ነገርን ከጨዋታው ትጠብቃለህ?

“ቅ/ጊዮርጊስ ዘንድሮ እንደሚታየው  በጠንካራ አቋሙ ላይ ነው ያለው። የሊጉን ጨዋታዎችም እስካሁን አልተሸነፈም።  ከተከላካዩ  አንስቶ እስከ አጥቂው ክፍል ድረስም  የተሟላም  ነውና  ከእነሱ ጋር የሚኖረን ጨዋታ በጣም ጠንካራ ነው የሚሆነው። ከእነሱ ጋር ስለሚኖረን ጨዋታም ሁሉም ቡድን ለእነሱ ክብር ሰጥቶ እንደሚገባው ሁሉ እኛም ክብርን ሰጥተናቸው ነው ወደ ሜዳ የምንገባው። የእኛም ቡድን በጣም ጠንካራ ስለሆነም ከእነሱ ጋር በሚኖረን ጨዋታ  በነጥብ  ያለብንን ልዩነት ለማጥበብ እንጫወታለን”።

ግጥሚያውን ማን ያሸንፋል ሲዳማ ቡና ወይንስ ቅ/ጊዮርጊስ

“እሱን እንኳን አሁን ላይ ሆኜ  ማን እንደሚያሸንፍ አላውቅም። ውጤቱን ከጨዋታው በኋላም አብረነው የምናየው ይሆናል”።

የሚያሸንፈውን  ቡድን  ካላወቅክ  ጨዋታው በአቻ ውጤትስ ያልቃል ማለት ነው?

“አቻ ያልቃልም አልልም፤  ሁለታችንም ለማሸነፍ ስለምንጫወት ዛሬ ውጤቱን በተመለከተ ከላይ እንደገለፅኩት  ሁሉንም ነገር አብረን የምናየው ይሆናል”።

ብዙ ተጨዋቾች የቀድሞ ቡድናቸውን በተቃራኒነት በሚገጥሙበት ጨዋታ ላይ  ከሌላው ጊዜ በበለጠ

እሳት ጎርሰው  ነው ወደ ሜዳ የሚገቡት አንተስ?

“ከቅ/ጊዮርጊስ  ጋር በሚኖር ጨዋታ የእውነት ለመናገር የእነሱ የቀድሞ ተጨዋች ሆነህ የለቀክ ሆንክም   ለእነሱ ቡድን ያልተጫወትክ የሌላ ቡድን ተጨዋች   ሁሉም ሜዳ  የሚገባው ራሱን ለማሳየት ነው። ይህን በብዙ መልኩም አይቻለው። ለእኔም አሰልጣኙ በሰጠኝ ታክቲክ እኔም  በሰራሁበትና በተዘጋጀሁበት ሁኔታም ነው ወደ ሜዳ ገብቼ የቀድሞ ቡድኔን እንደ ማንኛውም  ግጥሚያ ሆኜ  እንጂ ተጋጣሚያችን ቅ/ጊዮርጊስ ስለሆነ ብቻ በተለየ መልኩ ወደ ሜዳ አልገባም”።

ከወቅታዊ አቋምህ በመነሳት አሁን ላይ መሻሻሎችን እያሳየው ነው ትላለህ?

“አዎን፤ ብዬ አስባለሁ፤ በተለይ የሁለተኛው ዙር  ጨዋታ ከተጀመረ   ከቡና ጋር  ስንጫወት  ተጎድጄ  ከወጣው በኋላ  በድሬው ጨዋታ ላይ ባርፍም የሐዋሳው  ግጥሚያ ላይ  ሙሉ ለሙሉ ከጉዳቴ ሳላገግም ገብቼ ተጫውቼ  በሰበታው ግጥሚያ ላይ ከፍተኛ የጤና መሻሻልን በማሳየት ጥሩ  ተንቀሳቅሼ  ልጫወት ስለቻልኩ በቀጣይነትም ጥሩ  ብቃቴን አሳይቻለሁ”።

ከቅ/ጊዮርጊስ  የሚኖራቸውን ጨዋታ በበርካታ ደጋፊዎች ታጅበው የሚያደርጉ ስለመሆናቸው

“አሁን እንደምታየው ከቅ/ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ጀምሮ  የሌላ ክለብም  ደጋፊዎች  ወደ ሜዳ በብዛት መግባት  ውድድሩን እያደመቀው እንደሆነ እየተመለከትን ነው።  ያ መሆን መቻሉም  ለእግር ኳሱ ከፍተኛ መነሳሳትም ይፈጥራል። በዲ ኤስ ቲቪም  ጨዋታውን ለሚመለከት ሰው ድምቀትም ነውና ለእግር ኳሱ መነሳሳትን ይፈጥራል”።

ሲዳማ ቡና ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊጉን በምን ውጤት እንደሚያጠናቅቅ

“ባለፈውም እንደነገርኩህ አንድ ቡድን ውድድር ሲጀመር ብዙ ነገሮችን  ያስባል። የአቅሙን ሰርቶም ዕቅዱን ለማሳካትም ይጥራል። የእኛ ቡድንም የእዚህ ዓመቱን ውድድር ሲጀመር  የተለያዩ ቡድኖችን በማሰልጠን  በውጤታማነቱ  የሚታወቀውን አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌን  አስቀድሞ ወደ ቡድኑ በማምጣት እና ብቁ ተጨዋቾችንም በማሰባሰብ ከተቻለ የሊጉን ዋንጫ ያ ካልተስካ ደግሞ ክለቡ ሁለተኛ ወጥቶ በአፍሪካ  ደረጃ በኢንተርናሽናል ጨዋታ የሚሳተፍበትን ውጤት ለማግኘት እየሰራን ነው የሚገኘው። ከሁለቱ በአንዱም የአፍሪካ ውድድር ላይ ተሳታፊም እንሆናለን”።

ሲዳማ ቡና ከእዚህ ቀደም በነበሩት አንድ አንድ ዓመታቶች ላይ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት  እየተፎካከረ እና በነጥብም እየተቃረበ ወደ መጨረሻዎቹ ጨዋታዎች አካባቢ ወገቤን ሲል ይታያል። ይሄ ቡድን በእዚህ ደረጃ ከመጓዙ አኳያ የሊጉ ዋንጫ ይገባዋል ወይንስ አይገባውም?

“በደንብ ነው እንጂ የሚገባው።  እኔ በነበርኩበት የውድድር ጊዜ ከፋይናንስ አንስቶ በእያንዳንዱ ጨዋታዎች ላይ ግጥሚያን ስናሸንፍ የሚሰጠንም ኢንሴንቲቭ ነበር። በተደጋጋሚ ጊዜም ሻምፒዮና

 

የሲዳማ ቡናን ደጋፊዎች  ስትመለከት እንዴት ይገለፃሉ

“ከሐዋሳ ከተማ ተሳትፎአችን ጀምሮ ነው ያን ኪሎ ሜትር አቋርጠው በመምጣት የሚደግፉን። በጣም ነው የሚያበረታቱን። ሊከበሩና ሊመሰገኑ ይገባል”።

የፋሲካ በዓል ነገ እሁድ ከመከበሩ አኳያ ጊዜውን እንዴት እንደሚያሳልፍ

“ፋሲካን በብዛት  በጨዋታ ላይ ሆኜ  ነው የማሳልፈው። በጨዋታ ላይ በማልኖርበት እና በእረፍት ላይ በምሆንበት  ወቅት ላይ ደግሞ  ቤተሰብ ጋር ሄጄ  ነው  ከእነሱ  ጋር የማሳልፈው  አሁን ደግሞ የራሴን ጎጆ ከባለቤቴ ጋር  ስለቀለስኩ ከእሷ ጋር የማሳልፍበት ሁኔታ ቢኖርም ውድድር ላይ በመሆናችን አልተሳካም”።

ለእነ ማን እንኳን አደረሳችሁ ማለትን ትፈልጋለህ

“ለቤተሰቦቼ ለባለቤቴ እና ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ነው እንኳን አደረሳችሁ የምለው”።

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P