ሊግ ስፖርትን ያንብቡ
ተወዳጅ ጋዜጣዎን ሊግ ስፖርት ነገ በጠዋት ለንባብ ይጠብቋት፤ 20ኛ ዓመቷን ለማክበር በመንደርደር ላይ የምትገኘው ይህቺው ጋዜጣዎ ነገ ገበያ ላይ ስትቀርብም በሀገር ውስጥ አምዷ የባህርዳር ከተማው አጥቂ ሀብታሙ ታደሰ “ሻምፒዮና ባንሆን እንኳን ሁለተኛ ሆነን ለኮንፌዴሬሽን ካፑ እናልፋለን” ሲል በዓለም ዋንጫ ዙሪያም “አርጀንቲና የዓለም ዋንጫው አሸናፊ ትሆናለች” ሲል ተናግሯል።
ሊግ ስፖርት በባህርማዶ ዘገባዋ ደግሞ በኳታር አስተናጋጅነት እየተካሄደ ስላለው የዓለም ዋንጫ ሰፊ ዘገባ አላት።
ሊግ ስፖርት በእዚህ የዓለም ዋንጫ ዘገባም እሁድ ፍፃሜ ስለሚያገኘው የአርጀንቲናና የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታም የሚወዱትን ዘገባ ታስነብቦታለች።
በተለይም ስለ አርጀንቲናው ጥበበኛ ሊዮኔል ሜሲ የመጨረሻ ሙከራም የምትሎት ይኖራል።
ሊግ የእርስዎ ናት፤ ያንብቧት፤ ይወዷታል።
የሊግ ስፖርት የነገው የፊት ለፊት ምስልም ይህንን ይመስላል።
@Leaguesport