Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“አሁንም በድጋሚ ዋንጫው ከፋሲል ከነማ አይወጣም” ፍቃዱ ዓለሙ /ፋሲል ከነማ/

 

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታው  ፋሲል ከነማ ሀዲያ ሆሳህናን 3-1 በማሸነፍ ውድድሩን በድል ጀምሯል፤ የፋሲል ከነማን የአሸናፊነት ግቦችንም አጥቂው ፍቃዱ ዓለሙ በማስቆጠር የመጀመሪያውን ሀትሪክ ሊሰራም ችሏል፤ የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማና የመከላከያ እንደዚሁም ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች  በመሆን ያሳለፈው ፍቃዱ በዘንድሮው የሊጉ ውድድር ላይም ቡድናቸው እንደ ዓምናው ሁሉ ባለድል እንደሚሆንም ይናገራል፤ ከዚህ ተጨዋች ጋር ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ሀድያ ሆሳህናን ካሸነፉበት ጨዋታ በኋላ ስለ እለቱ ድላቸው፣ ሀትሪክ ስለመስራቱ፣ ስለ ዘንድሮ እቅዳቸውና ሌሎችንም ጥያቄ አቅርበንለት ተጨዋቹ ምላሽ ሰጥቶናል፤ ተከታተሉት፡፡

ሊግ፡– በሀድያ ሆሳህና ላይ ሀትሪክ መስራት ችለሃል፤ በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመንህ  በአንድ ጨዋታ ላይ ሶስት ግቦችን ስታስቆጥር የአሁኑ የመጀመሪያ ነው?

ፍቃዱ፡- አይደለም፤ ከዚህ ቀደም ለአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በከፍተኛው ሊግ ስጫወት

በደቡብ ፖሊስ ቡድን ላይ ሶስት ግቦችን አስቆጥሬ ነበር፤ ያኔም ሆነ አሁን ግቦቹን ሳስቆጥር አሰልጣኙ በተመሳሳይ ስዩም ከበደም ነበርና ይህ ግጥምጥሞሹም ሊገርመኝም ችሏልና የአሁኑ የሀትሪክ ግቤ ለሁለተኛ ጊዜ ያስቆጠርኩትም ነው፡፡

ሊግ፡- ለፋሲል ከነማ  ባስቆጠርኳቸው 3 የድል ግቦች የተሰማህ ስሜት ምን ይመስላል?

ፍቃዱ፡-  በጣም ነው ደስተኛ የሆንኩት፤ ምክንያቱም እነዚህ ግቦቼ በፕሪምየር ሊግ ደረጃ  ያስቆጠርኳቸው የመጀመሪያ ሀትሪክ ግቤ ስለሆኑና ከሁሉም ባሻገር ደግሞ ለቡድኔ በመጀመሪያው ጨዋታችን ሶስት ነጥብ ያስገኘችም በመሆኗም ነውና የተለየ የደስታ ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማ ሀድያ ሆሳህናን ድል ባደረገበት ጨዋታ ለአሸናፊነት እንዲበቃ ያደረገው ዋናው ምክንያት ምን ነበር?

ፍቃዱ፡- በጨዋታው የእኛ ቡድን ይዞት የገባው እንቅስቃሴ በመልሶ ማጥቃት ላይ  /ካውንተር/ ያተኮረ እንቅስቃሴ ነበርና በእዛ ውስጥ ተጉዞ ነው ያገኛቸውን የግብ ማስቆጠር እድሎችን ሊጠቀም በመቻሉ ግጥሚያውን አሸንፎ ሊወጣ የቻለው፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማ ሀድያ ሆሳህናን ሲያሸንፍ ምርጥ ነበር ለማለት ይቻላል?

ፍቃዱ፡- በፍፁም፤ እንደ መጀመሪያ ጨዋታችን ጥሩ አልነበረንም፤ ያም ሆኖ ግን የዋንጫ ቡድን አንድ አንድ ጊዜ  በሜዳ ላይ እንቅስቃሴው የተመልካችን ስሜት የማይስብበት ጊዜ ሊኖር ስለሚችል፤ እኛም በፈለግነው መልኩ ጥሩ ባንጫወትም ግጥሚያውን ግን ለማሸነፍ ችለናል፤ ይሄ ሊሆን በመቻሉም በጣም ተደስተናል፡፡

ሊግ፡- ሀድያ ሆሳህናን ለማሸነፍ ስትችሉ የእነሱን አቋም እንዴት አገኘኸው?

ፍቃዱ፡- በጣም ጠንካራ ናቸው፤ የአየር ላይ ኳስ ላይም ኳስን  በጭንቅላት ለመግጨት ሲዘሉም ይገርማሉ፡፡ በዛ ላይ ደግሞ የጨዋታ እንቅስቃሴያቸውም ይከብዳል፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ትክክለኛ ዋንጫውን ሀድያ ሆሳህናን ካሸነፈበት የረቡዕ እለት ግጥሚያ በፊት ተቀብሏል፤ በእሱ ዙሪያ ምን አልክ?

ፍቃዱ፡- ዓምና በጣም ለፍተንና ተግተን ነበር ይህን ዋንጫ ለማንሳት ስንጫወት የነበርነው፤ በጊዜው ዋንጫው ደርሶ0 በእጃችን ላይ ባይገባም አሁን ይኸው ትክክለኛ ዋንጫው ተሰጦን ልንጨፍርበት ችለናልና በጣም ደስ ብሎናል፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማን ከዚህ በኋላ በሚኖረው ጨዋታው በምን መልኩ እንጠብቀው? የዘንድሮ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ እልሙና ግቡስ እስከምን ድረስ ነው?

ፍቃዱ፡- የመጀመሪያ የሀዲያ ሆሳህና ጨዋታችን ላይ ምንም እንኳን ግጥሚያውን እናሸንፍ እንጂ ብቃታችን እንደ አምና አልነበረም፤ በዛ ዕለት ጨዋታም ግጥሚያውን ለማሸነፍ እንድንችል ግብ ማስቆጠሩ ላይ ብቻም ነበር ትኩረት ሰጥተንም የነበርነው፡፡ ያም ተሳክቶልናል፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ቡድናችን ከጨዋታ ወደ ጨዋታ እየተስተካከለ በመምጣት የዓምናውን ጥንካሬያችንን ዘንድሮም በተሻለ መልኩ ሜዳ ላይ እናሳያለን፡፡ የእዚህ ዓመት ግባችንን በተመለከተ ፋሲል ከነማ የአምናው ሻምፒዮና ነው፤ ባክ ቱ ባክ ዘንድሮም ይህን ድል ይደግመዋል፤ ከዛም በተጨማሪ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉንም ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የሚያነሳም የመጀመሪያው ቡድንም ይሆናል፡፡

ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታህ ሀትሪክ ስትሰራ ሶስተኛ ግብህ የተቆጠረው በፍፁም ቅጣት ምት ነበር፤ የክለቡ የመጀመሪያ መቺ አንተ ነበርክ?

ፍቃዱ፡- አይደለውም፤ የመጀመሪያው የፍፁም ቅጣት ምት መቺያችን ካፒቴናችን ያሬድ ባየህ ነው፤ ልክ የፍፁም ቅጣት ምቱን እንዳገኘን እሱ ነው ሀትሪክ እንደሰራ በመፈለጉ ለእኔ ለቆልኝ ምታ ያለኝ፤ ያኔም ደስ አለኝና መትቼ ግቧን በጥሩ ሁኔታ አስቆጠርኩ፤ በእዚህ አጋጣሚ ያሬድ በእኔ ላይ እምነቱን ጥሎ እንድመታ ስለፈቀደልኝ ከልብ ላመሰግነው እፈልጋለውኝ፡፡

ሊግ፡- የፍፁም ቅጣት ምቱን ልትመታ ስትል አንድአንዶች ሊስት ይችላል በሚል ስጋት ያደረባቸው ነበሩ፤ የፍፁም ቅጣት ምት ስተህ ታውቃለህ እንዴ?

ፍቃዱ፡- ኸረ ስቼ አላውቅም፤ በእርግጥ ወደ ፋሲል ከነማ ስመጣ ሰዎች ስለ እኔ የፍፁም ቅጣት ምት አመታት ላያውቁ ስለሚችሉ ሊሰጉ ይችሉ ይሆናል፤ እኔ ግን ከዚህ ቀደም ለአዲስ አበባ ከተማ ቡድን በምጫወትበት ሰዓት የመጀመሪያ መቺ ነበርኩ፤ የማገኛቸውን ምቶችንም አስቆጥር ነበርና ምንም ግር ሳይለኝም ነው ፋሲል ከነማ ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ላስቆጥር የቻልኩት፡፡

ሊግ፡- በቤትኪንጉ ሀትሪክ ሰርተህ ኳሷን ወሰድክ፤ እነማን ፊርማቸውን አኖሩባት?

ፍቃዱ፡- የመጀመሪያውን ፊርማ አኑረው ኳሷን የሰጡኝ አልቢትሮቹ ናቸው፤ ወዳረፍንበት ሆቴል ካመራን በኋላ ደግሞ የተወሰኑ የቡድናችን ተጨዋቾች ናቸው ፊርማቸውን አኑረው ሊሰጡኝ የቻሉት፡፡

ሊግ፡- በቤትኪንግ ሀትሪክ የሰራክበትን ኳስ የት ልታስቀምጣት አሰብክ?

ፍቃዱ፡- ይህቺ ሀትሪክ የሰራሁባት ኳስ ለእኔ ልዩ ታሪኬና የሁልጊዜም ማስታወሻዬ ናት፤ በክብርም ቤቴም ነው የማስቀምጣት፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማ ድል ባደረገበት ጨዋታ ሀትሪክ ስትሰራ በአንተ ስኬት በመደሰት የመጀመሪያውን የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክት ማን ላከልህ?

ፍቃዱ፡- ከጨዋታው በኋላ በደስታ ላይ ስለነበርኩ ብዙ መጨናነቆች ነበሩ፤ መኪና ውስጥ ስለነበርኩም ብዙ ስልኮችም ተደውለውልኝ ነበር፤ ቀድሞ ግን ማን እንደደወለልኝ ፈፅሞ ላውቅ አልቻልኩም፡፡

ሊግ፡- በቤትኪንጉ ለፋሲል ከነማ በመጀመሪያው ጨዋታ ሀትሪክ መስራት ችለሃል፤ ከዛ በመነሳት ዘንድሮ ምን ያህል ግቦችን ለማስቆጠር እቅድን ይዘሃል?

ፍቃዱ፡-  ይሄን ያህል ግብ አስቆጥራለው ብዬ ከወዲሁ አላቀድኩም፤ የእኔ ግብ ባለኝ አቅም ሁሉ ቡድኔን ለውጤት የሚያበቃ ግቦችን ማስቆጠር መቻል ነው፡፡

ሊግ፡- የሙጂብ ቃሲም ወደ አልጄሪያ በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ለመጫወት መሄድ መቻል ለፍቃዱ አለሙ መሰለፍም ሆነ ግቦችን እንዲያስቆጠር እድልን ፈጥሮለታል የሚል ነገር እየተነሳ ይገኛል…?

ፍቃዱ፡- ሙጂብ ጥሩና የማደንቀው ተጨዋች ነው ከእሱ ብዙ ልምዶችንም ወስጃለው፤ እኛ ጋር በነበረበት ሰዓት ብዙ ባይሆንም አብረን የተጫወትንበት አጋጣሚም ነበር እንደ አጋጣሚ ሆኖ እሱ የተሻለ እድል ሲያገኝና ወደ አልጄሪያ ሲጓዝ እኔ ደግሞ አሁን ላይ በቋሚ ተሰላፊነት መጫወት ጀምሬያለውና ያን እድል ልጠቀምበት ተዘጋጅቻለው፤ በፋሲል ከነማ የዘንድሮ ቆይታዬ አሁን ላይ ሙጂብ ባይኖርም ኦኪኪ አፉላቢ አለ፤ ከእሱ ጋር ተቀናጅተንም ፋሲልን ለድል ለማብቃት ዝግጁ ነን፡፡

ሊግ፡- የፋሲል ከነማን ስብስብ በምን መልኩ ትገልፀዋለህ?

ፍቃዱ፡- የእኛ ስብስብ በጣም አሪፍ ነው፤ ብዙዎቻችን አብረንም ቆይተናል፤ ሶስት እና አራት አመት የቆዩም አሉ፤ ከዛ በመነሳት ስብስባችንን ስመለከተው ዘንድሮም ምርጥ የሚባል ነው፡፡

ሊግ፡- የእነ አስቻለው ታመነ ቡድናችሁን መቀላቀል የጨመረላችሁ ነገር አለ?

ፍቃዱ፡- በጣም፤ አስቻለው የሀገሪቱ ምርጥ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ነው፤ እሱ ከእነ ያሬድ ባየህ እና ሌሎች ተጨዋቾች ጋር የሚኖረው ጥምረትም ቡድናችን ላይ የተለየ ጥንካሬን ይጨምርልናልና በእሱ መምጣት ሁላችንም ደስተኞች ሆነናል፡፡

ሊግ፡- ለፋሲል ከነማ ዘንድሮ የትኛው ክለብ የዋንጫ ተፎካካሪው ይሆናል?

ፍቃዱ፡- የእኛን የዋንጫ ተፎካካሪ አሁን ላይ ይሄ ቡድን ነው ለማለት በጣም ይከብደኛል፤ ሊጉ ገናም መጀመሩ ነው፤ ስለዚህ ባልገምት ነው የሚሻለው፡፡

ሊግ፡- በዚህ ዓመት ምን ምን ነገሮችን አቀድክ?

ፍቃዱ፡- የመጀመሪያው እቅዴ ከክለቤ ፋሲል ከነማ ጋር ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ዳግም ማንሳት መቻል ነው፤ ከዛም በማከል ደግሞ በርካታ የድል ግቦችን ለቡድኔ በማስቆጠር ቡድኔን መጥቀምና ውጤታማ ማድረግ እፈልጋለው፤ ሌላው ወደ ብሔራዊ ቡድንም ዳግም በመመረጥ መመለስ እፈልጋለው፤ ለዛም በሚገባ ተዘጋጅቻለው፡፡

ሊግ፡- በመጨረሻ…..?

ፍቃዱ፡- ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ዓምና እንደ ዘንድሮ ብዙ እውቅና አልነበረውም፤ በዚህ ዓመት ላይ ግን ከወዲሁ ሐዋሳ ከተማ ላይ እንደተመለከትኩት የዲ. ኤስ. ቲቪ ማስታወቂያዎችን ብዙ ሰዎች እየተመለከቱት ነው፤ ይህ ለሁሉም ጥሩ ስሜት ይሰጣል፤ የእግር ኳስ ተጨዋቾችን የመጫወት ፍላጎትም ይጨምራልና በዛ ሁላችንም ተጨዋቾች ደስ ብሎናል፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P