Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

የሊጉ ምርጥ ቡድኖች ቅ/ጊዮርጊሶች እና እኛ ነን” “በቅ/ጊዮርጊስ በ10 ነጥብ መበለጣችን ከዋንጫው ፉክክር አያስወጣንም” በቃሉ ገነነ /ሐዋሳ ከተማ/

 

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የዘንድሮ የውድድር ዘመን ተሳትፎው ጠንካራ  ተፎካካሪ ሆኖ ቀርቧል፤ ቡድኑ በአብዛኛው በወጣት ተጨዋቾች መገንባቱና  አበረታች የሚባል ውጤትን ማስመዝገቡም በብዙዎቹ ዘንድ አድናቆትን እንዲያሰጠውም አድርጎታል።  የአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ  ቡድን ሐዋሳ ከተማ  በሊጉ መሪውን ቅ/ጊዮርጊስ በመከተል በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በ21ኛው እና በአዳማው ሳይንስና ፋኩሊቲ ሜዳ ላይ  በሚደረገው የዛሬው ጨዋታም ቅ/ጊዮርጊስን ለመፋለሞ ተዘጋጅቷል።

የሐዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የውድድር  ታሪክ  ለሁለት ጊዜያት ያህል ዋንጫውን ከፍ አድርጎ ለማንሳት  ቢችልም፤  በመሪው  ቅ/ጊዮርጊስ  ቡድን  በ10 ነጥብ ለመበለጥ ቢችልም እስከ መጨረሻው ግጥሚያ ድረስ  ተስፋ  ሳይቆርጡ  በመጫወት ከቻሉ ሻምፒዮና ለመሆን ካልቻሉ ደግሞ  ሁለተኛ ወጥተው ወደ ኢንተርናሽናል የውድድር መድረክ ለመመለስ እንደሚጫወቱ የቡድኑ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች በቃሉ ገነነ  ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ  /G.BOYS/  አስተያየቱን ሰጥቷል።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የ20ኛው ሳምንት ጨዋታ በሀዲያ ሆሳዕና ሽንፈትን አስተናግዳችኋል? ከግጥሚያው በኋላ  የተመዘገበው ውጤት ምን ስሜትን  ፈጠረብህ?

በቃሉ፦  ሽንፈት  ሲመጣብህ  በየትኛውም  አጋጣሚና ነገር  ደስ አይልም፤ ያጋጥማልም።  የህይወት  አንዱ አካልም  ስለሆነ   ሁሌ ማሸነፍም    የለም። ስለዚህ ለቀጣይ ላለብህ  ጨዋታ አንድ አንድ ነገሮችን እያስተካከልክና ጠንክረ እየሰራ  በመሄድ  ወደ አሸናፊነት መምጣት  የግድ ይልሃልና  የሁለቱንም ጣህሞች ልታውቅ  ይገባል። በመሸነፋችን ደስታ ባይሰጠኝም  ልቀበለው ግን ችያለሁ።

ሊግ፦ በሀድያ ሆሳዕና ለደረሰባችሁ ሽንፈት በምክንያትነት የምትጠቀሰው ነገር ምንድን ነው? የሊጉን ውድድርስ እንዴት ተመለከትከው?

በቃሉ፦ ሊጉን  እንዳየከው  ሁሉም ቡድን በየጨዋታው የየራሱን ስራ እየሰራ ነው  የሚመጣው። የውድድሩ ይዘትም   አሁን ላይ እንደ በፊቱም አይደለም። በጣም  እየጠነከረም  ነው የመጣው። ምክንያቱም ዲ ኤስ ቲቪም ስላለ እና  እያንዳንዱ እንቅስቃሴም  እየታየ በመሆኑም  በአንተ ወቅታዊ አቋምና  ብቃት ላይ እየተሰራብህ ስለሚመጣብህም በእዛን ዕለት ጨዋታ ባሰብነውና ባቀድነው እንደዚሁም ደግሞ በተነጋገርነው መልኩም ባለመሄዳችን  የሽንፈታችን አንዱ ምክንያት ያ ይመስለኛል።

ሊግ፦  አሁን ላይ  ከዋንጫው ፉክክር ወጥታችኋል ማለት ይቻላል?

በቃሉ፦  በፍፁም፤  አይቻልም። ገና እኮ የ10 ሳምንት ጨዋታ አለን።

ሊግ፦ በመሪው ክለብ  ቅ/ጊዮርጊስ  የምትበለጡበት የነጥብ  ልዩነት እኮ 10 ነው?

በቃሉ፦ አዎን፤  ግን ካለው የጨዋታ ብዛት ውስጥ  የነጥቦቹን ልዩነቶች  ስንመለከታቸው እንደዛ ብሎ መደምደም አይቻልም።  እነሱም በቀሪዎቹ ጨዋታዎች ምን እንደሚያጋጥማቸውም አይታወቅምና ከዋንጫው ፉክክር ወጥተናል ማለት አይቻልም።

ሊግ፦ የዘንድሮ ሐዋሳ ከተማ እንደ ቡድን ምርጥ ነው?

በቃሉ፦ አዎን፤  እንደ ሌሎች  ቡድኖች  ክፍተቶች ቢኖሩብንም  ከዚህ  ቀደም ክለቡ ካሳለፋቸው የውድድር  ዓመታቶች አኳያ  የዘንድሮ ቡድኑ በጣም ጠንካራ እና ምርጡ ቡድን  ነው።

ሊግ፦  የእናንተ  ጠንካራው  እና  ደካማው  ጎናችሁ ምንድን  ነው?

በቃሉ፦ ጠንካራው ጎናችን  ዛሬ ላይ  ጨዋታን  አድርገን በነጋታው ላይ ስለነበረን ወቅታዊ አቋም ከአሰልጣኞቻችን የሚነገረንን ነገር  በመስማት ከስህተታችን ለመማር  ወደ ስራ ውስጥ መግባት መቻላችን ነው።  ሌላው ጠንካራ ጎናችን  ህብረታችንም ነው። በክፍተት ጎንነት ደረጃ የማነሳው ደግሞ በተደጋጋሚ ጊዜ የቆሙ ኳሶች ይገቡብናል።  በጎል እየመራን  ውጤትን የማስጠበቅ ችግርም አለብንና እነዚህ ነገሮች ይጠቀሳሉ።

ሊግ፦  ሐዋሳ ከተማ  ዘንድሮ ካደረጋቸው ግጥሚያዎች ውስጥ  በየቱ  ይቆጫል?

በቃሉ፦  እንደ ራሴ እይታ የምቆጭባቸው ጨዋታዎች በሀድያ ሆሳዕና  እና በሲዳማ ቡና የተሸነፍንባቸውን ነው።

ሊግ፦  በሀድያ የተሸነፋችሁበትን  ግጥሚያ እንዴት አገኘከው?

በቃሉ፦ በጨዋታው እነሱ  በሁሉም ነገር  ማለትም አግሬሲቭ  ሆነው በመጫወትና  ጎልን  በማስቆጠር በልጠውን ነበር።  በጨዋታው ላይ   እነሱ መርተውን  አቻ ልናደርጋቸው ብንችልም የተሻሉ ስለነበሩ  አሸንፈውናል።

ሊግ፦ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን በምን ውጤት ታጠናቅቃላችሁ?

በቃሉ፦  በአዳማ ከተማ ላይ ያለንን ውድድር ጨርሰን ባህርዳ በክፍተት ጎናችን ላይ እየሰራንና እያስተካከልን ቢያንስ ወደ ሻምፒዮንነቱ ደረጃ ለመጠጋትና ያ ካልተሳካም ሊጉን በሁለተኝነት ለማጠናቀቅና  ወደ  ኮንፌዴሬሽን ካፕ ለማለፍ ጥረትን እናደርጋለን።

ሊግ፦  በዘንድሮ  ውድድር  ምርጡ ቡድን ማን ነው?

ሊግ፦ ለእኔ ምርጡ ቡድን በምንም ጨዋታ  ያልተሸነፈውን  ቅ/ጊዮርጊስ እና እኛ ነው የምለው። ቅ/ጊዮርጊስን ምርጡ ያልኩበት ዋናው ምክንያትም በሁሉም ነገር የተሟላም  ስለሆነ  ነው። የእኛን ቡድን ከእነሱ በመቀጠል  ምርጡ ያልኩበት ሁኔታ ደግሞ  ከቡድኑ  የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ አንስቶ በወጣት ተጨዋቾች ተገንብቶ የሚጫወት በመሆኑና  ከዛ ውጪም  እንደ ሌሎቹ ቡድኖችም ብዙ ወጪን ሳያወጣ አበረታች የሚባል ውጤትን እያስመዘገበ  ስላለም ነው።

ሊግ፦ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሲጠናቀቅ በኢንተርናሽናል  የውድድር መድረክ  ኢትዮጵያን በመጪው ዓመት  የሚወክል ሁለት ቡድን ይኖራል፤ አንዱ ተሳታፊ  ቡድን ሐዋሳ ከተማ ይሆናል?

በቃሉ፦ አዎን፤  ለዛም ነው ጠንክረን እየሰራን የምንገኘው።

ሊግ፦ በራሳችሁ ትተማመናላችሁ?

በቃሉ፦ አዎ።

ሊግ፦  በሐዋሳ ከተማ   ባለህ ቆይታህ ያሳለፍከውን የውድድር ጊዜ እንዴት  ትመለከተዋለህ? እንደ ቡድንስ  ስታየው….?

በቃሉ፦ እንደ አጠቃላይ  አሪፍ  ቆይታ ነበረኝ። እንደ ቡድን  ያሳለፍነውን ነገር ስመለከተው ደግሞ  በአዳማ ላይ  ትንሽ ቀዝቀዝ ብለን ነበር። ከዛ በፊት ደግሞ  ጠንክረን ነው ለመምጣት የቻልነው።  በቀጣይነት  ደግሞ  ዛሬ  ላይ ላለብን  ጨዋታና  ባህርዳር ላይም ለሚኖረን  ተሳትፎ  ጠንክረን  ለመቅረብ  እንሞክራለን።

ሊግ፦ ባሳለፍከው የውድድር ጊዜ ድክመቴ ብለህ የምታነሳው ምንድን ነው?

በቃሉ፦ እንደ  አማካይ ስፍራ  ተጨዋችነቴ  ጎል  አልገባውም።  ያንንም  ነው  የምጠቅሰው።

ሊግ፦ ከቅ/ጊዮርጊስ  ጋር  ወሳኝና ተጠባቂውን  ጨዋታ ዛሬ ላይ ታደርጋላችሁ፤  ከግጥሚያው  ምን ውጤትን  ትጠብቃለህ?

በቃሉ፦ ኳስ ጨዋታ የዕለት አቋም /ፐርፎርማንስ/ ነው።  ባለፈው  ጨዋታ  በመሸነፋችን  ነጥብ ጥለን የመጣን  ከመሆኑ  አኳያና  መሪውንም  ቡድን   በነጥብ  መቃረብ ስላለብን  ይህን ግጥሚያ ለማሸነፍ  ነው  ወደሜዳ የምንገባው።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ  የዘንድሮ  ምርጡ  ተጨዋች ማን ነው?

በቃሉ፦  እስካሁን ካየሁት በተለይም ደግሞ ድሬ ላይ የፋሲል ከነማው በረከት ደስታ ልዩ  ተጨዋች  ነበር። በእዚህ በአዳማ ላይ ደግሞ ምርጡ የምለው ተጨዋች እስካሁን  ማንም የለም።

ሊግ፦ አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን እንዴት ትገልፀዋለህ?

በቃሉ፦ እሱ ለሁለት ዓመት እኔን ስላሰራኝ  ስለ እሱ ብዙ  ባወራ  ማጋነን ይሆንብኛል።  ያም ሆኖ ግን

ነገር ስነሳ  በወጣት ተጨዋቾች እና  በመነጋገር  የሚያምን አሰልጣኝ ነው።  በብዙ ነገር ቅድሚያን  ለወጣቶችም ይሰጣል። ለዛም ነው ቡድኑን  በእዛው መልኩም  የገነባው።  ከዛ ውጪም እነዚህን ወጣቶች ከሲኒየሮቹ ጋር በማጣመርም ለቀጣዮቹ ጨዋታዎች  ስህተቱን   እያረመም  ወደፊት የሚጓዝ አሰልጣኝ ነውና  እሱን በእዚህ መልኩ ነው የምገልጸው ።

ሊግ፦  ቆይታችንን እናጠቃል?

በቃሉ፦  በመጨረሻ  የምለው  እኛ ወደፊት ላሉብን ጨዋታዎች ጠንክረን ሰርተን መጥተን  ያጣናቸውን ውጤቶች  ለማስተካከል  እንጥራለን።   ኳስ ጨዋታ ብዙ ውጣ ውረዶች አሉት።  ወጥ የሆነ አቋምን ላታሳይ ትችላለህ።  ከእዚህ  መነሻነት ከጎናችን  ያሉት ደጋፊዎቻችን  አሁንም በተለመደው መልኩ  በምንም ውጤት ሊጉን  እስክናጠናቅቅ  ድረስ ከእኛ  ጋር እንዲሆኑና  ድጋፋቸውን እንዲሰጡን እንጠይቃለን።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P