Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“አሁን ወደመግባባቱና መቀናጀቱ ስለመጣን ጥሩ ውጤት ይኖረናል” የአብስራ ሙሉጌታ /ቤቤቶ/ /ጅማ አባጅፋር/

“አሁን ወደመግባባቱና መቀናጀቱ ስለመጣን ጥሩ ውጤት ይኖረናል”
የአብስራ ሙሉጌታ /ቤቤቶ/ /ጅማ አባጅፋር/
በቅ/ጊዮርጊስ የተተኪው ቡድን ውስጥ ነው ኳስን መጫወት የጀመረው፤ ልጅ ሳለም ደግሞ ተወልዶ ባደገበት እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው የመስቀል አደባባይ ሜዳ ላይ ኳሱን በማንከባለል ጀምሮ በዛሬው ዕለት ለሚገኝበት የኳስ ተጨዋችነት ህይወት ሊበቃ ችሏል፤ ተጨዋቹ የአብስራ ሙሉጌታ ይባላል፤ ብዙዎቹ ሲጠሩት ደግሞ “ቤቤቶ” ይሉታል፤ ከእዚህ ወጣት እና በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ምንም እንኳን ቡድናቸው በጥሩ ውጤት ላይ ባይገኝም እሱ በግሉ ለቡድኑ መልካም የሚባልን ጥሩ እንቅስቃሴ እያሳየ ስለሚገኝ የሊጉ ስፖርት ጋዜጣ በጋዜጠኛው መሸሻ ወልዴ አማካኝነት በኳስ ህይወቱ ዙሪያና ሌሎችንም ጥያቄዎችን አካቶለት ተጨዋቹ የሰጠው ምላሽ በሚከተለው መልኩ ቀርቧል፡፡
ሊግ፡- በቅድሚያ ብዙዎቹ ከሚጠሩህ የቅፅል ስምህ ልነሳ “ቤቤቶ” ለምን ተባልክ…ማንስ ነው ስሙን ያወጣልህ?
የአብስራ፡- “ቤቤቶ” የተባልኩት በሕፃንነት ዕድሜዬ ወላጅ አባቴ እግር ኳስን በጣም ይከታተል ስለነበርና ብራዚላዊውን ተጨዋችም እንደምመስል ይነግረኝ ስለነበር እሱ ራሱ ስያሜውን ያወጣልኝ፡፡
ሊግ፡- ወደ እግር ኳስ ተጨዋችነት ህይወቱ እንዴትና በምን መልኩ ለማምራት ቻልክ?
የአብስራ፡- በሕፃንነት ዕድሜዬ ነው በጣም የምወደውን እግር ኳስን መስቀል አደባባይ በሚገኘው ሜዳ ላይ በመጫወት የጀመርኩት፤ ትንሽ ከፍ ካልኩ በኋላም በፕሮጀክት ደረጃ ተጫውቼ በመምጣት ወደ ክለብ ልሸጋገር ቻልኩ፡፡
ሊግ፡- በልጅነት ዕድሜህ እንደ አሁኑ ተከላካይ ሆነህ ነው ኳስን መጫወት የጀመርከው?
የአብስራ፡- አዎን፤ ከዛ ውጪም ግብ ጠባቂና በተለያዩ ቦታዎች ላይም የተጫወትኩበት ሁኔታም ነበር፡፡
ሊግ፡- በቤተሰባችሁ ውስጥ ስፖርተኛው አንተ ብቻ ነህ? ስንት ወንድምና እህትስ አለ?
የአብስራ፡- ወንድምና እህት የለኝም፤ ለቤተሰባችንም ብቸኛው ልጅ ነኝ፤ ስፖርተኛውም እኔ ብቻ ነኝ፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን መጫወት ስትጀምር እንደ አርአያ ወይንም ደግሞ እንደ ሞዴል በመመልከት አድንቀህ ያደግከው ተጨዋች ማን ነው?
የአብስራ፡- ጎረቤቴ ስለሆነ ሳይሆን አጨዋወቱ በጣም ደስ ይለኝ ስለነበር ዳዊት እስጢፋኖስን በማድነቅ ነው ያደግኩት፤ ለእሱ ክብርም አለኝ፡፡
ሊግ፡- ከባህርማዶ ክለቦች የማን ደጋፊ ነህ? የምታደንቀው ተጨዋችስ?
የአብስራ፡- የማደንቀው ተጨዋች ቴሪ ዳንኤል ሆንሪን ሲሆን የምደግፈው ክለብ ደግሞ አርሰናልን ነው፡፡
ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ቡድናችሁ ውጤት ማምጣቱ ላይ ተቸግሯል፤ ይህን ያሳጣችሁ ምክንያት ምንድን ነው?
የአብስራ፡- በኳስ ህይወት ማሸነፍ፣ መሸነፍና አቻ መውጣት ያጋጥማል፤ ጥሩ ውጤት ይመጣል፤ ይጠፋልም፤ እኛንም የውጤት ማጣት አጋጥሞናል፤ እስካሁንም ካደረግናቸው ጨዋታዎች ውስጥ አንድ ጨዋታን ብቻ ነው አቻ የተለያየነው፤ ለእዚህ ውጤት ልንጋለጥ የበቃነውም አብዛኛዎቹ ተጨዋቾች ለቡድኑ አዲስ ስለሆንና በደንብ ስላልተዋወቅን እንደዚሁም ደግሞ ልንቀናጅም ስላልቻልን ነው፤ አሁን ግን በመግባባቱ ላይ በደንብ ሰርተን ስለምንመጣ ጥሩ ውጤት ይኖረናል፡፡
ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ጥሩ የተጨዋቾች ስብስብ ኖራችሁ ነው ውጤት እያጣችሁ ያለው?
የአብስራ፡- ልክ ነህ፤ ወጣት ተጨዋቾች እና ጥሩ ልምድ ያላቸው ሲኒየር ተጨዋቾችን ይዘን ነው ውጤት ያጣነው፤ ወጣት ተጨዋቾቹ የጌም ልምድ ችግር አለብን፤ ከዛ ውጩ የትኩረት ማጣትም እኛን የጎዳን ቢሆንም ወደ መጨረሻዎቹ የሐዋሳ ከተማ ጨዋታዎቻችን ላይ ግን ጥሩ ነገርም ስለተደረገልን በቡድናችን ላይ መሻሻሎችን ልንመለከት ችለናል፡፡
ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የእስካሁን ጉዞአችሁ የየቱ ጨዋታ ውጤት ያስቆጭሃል?
የአብስራ፡- ከቀድሞ ክለቤ ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ያደረግነው ነዋ! በጨዋታው እኛ ንፁህ ግብ አግብተን ተሽሮብናል፤ እኛ ላይ የገባው ግብ ደግሞ ከጨዋታ ውጪ የሆነ ነው፤ በእዚህ ጨዋታም እኛ እንደነበረን ብቃት ሶስት ነጥብ በደንብ ይገባን ነበር፡፡
ሊግ፡- በቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ነው የኳስ ጅማሬህን ያደረግከው፤ ነገር ግን ብዙም ቆይታን ሳታደርግ ወደ ጅማ አባጅፋር ልታመራ ቻልክ፤ ፈልገከው ነው?
የአብስራ፡- አዎን፤ ምክንያቱም የቀድሞ ክለቤ የመጫወቱን ነገር ለእኔ ብዙም አልሰጠኝም፤ እኔ ደግሞ በእዚህ እድሜዬ መጫወትን እንጂ መቀመጥን ስላልፈለግኩኝ ከእነሱ ጋር በመነጋገርና ለመስማማትም ስለቻልን ነው ወደ አዲሱ ቡድኔ ላመራ የቻልኩት፡፡
ሊግ፡- በቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ቆይታን ብታደርግ በጣም ደስ ይልህ ነበር?
የአብስራ፡- በጣም፤ ያ የሚሆነው ግን ተሰልፌ እየተጫወትኩ ከሆነ ነው፤ ምክንያቱም ቅ/ጊዮርጊስ ትልቅ እና የወደድኩትም ቡድን ስለነበር ነው፤ በጣም እደሰት የነበረው እየተጫወትኩም ቢሆን ነበር፤ ያለበለዚያማ ተቀምጬ ምን አደርጋለው፡፡
ሊግ፡- ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ዳግም የምትመለስ ይመስልሃል?
የአብስራ፡- አንድ ቀንማ መመለሴ አይቀርም፤ ይሄ የሚሆነው ግን አሁን ለምጫወትበት ክለብም ሆነ በሌላ ቡድን ውስጥ መልካም የሚባል የጨዋታ እንቅስቃሴን ማሳየት እና ቡድኖቼን በስኬት መጥቀም ከቻልኩኝ ነው፡፡
ሊግ፡- የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ተሳትፎ እንዴት ተመለከትከው፤ የትኞቹ ቡድኖችስ ለአንተ ጠንካራ ናቸው?
የአብስራ፡- አብዛኛዎቹ ክለቦች ተመሳሳይ አቋማቸውን እያሳዩ ቢሆንም ፋሲል ከነማን፣ ቅ/ጊዮርጊስንና ኢትዮጵያ ቡናን በተወሰነ መልኩ ጥሩ ሆነው አግኝቼያቸዋለው፡፡
ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የሐዋሳ ከተማ ቆይታችሁ ብዙዎቻችሁ ተጨዋቾች የጨዋታ ሜዳውን በሰበብ ደረጃ ስታነሱ ተሰምቷል፤ የሊጉ ችግር የእሱ ብቻ ነው?
የአብስራ፡- አይደለም፤ የሜዳው ጥሩ አለመሆን ጥሩ ኳስ እንዳይታይ አድርጓል፤ ነገር ግን ከእሱ ውጪም የተጨዋቾች ዲስፕሊን አለመሆን፣ የዳኝነት ችግር፣ የአየሩ ሁኔታና ተጨዋቾች ላይ ስሜታዊ የመሆን ሁኔታ ሊጉ ላይ በሚገባ ታይቷል፡፡
ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ አንድ ነጥብ ያለውን ክለባችሁን ድሬዳዋ ላይ እንዴት እንጠብቀው?
የአብስራ፡- በሐዋሳ ቆይታችን ወደ መጨረሻ ጨዋታዎቻችን አካባቢ ጥሩ ነበርን፤ መሻሻሎች በቡድናችን ላይ ታይቷል፤ ከእዚህ በመነሳት በድሬዳዋ ከተማ በሚኖረን የውድድር ቆይታ አንደኛው ዙርን ተስፋ ሰጪ በሆነ ውጤት የምናጠናቅቅ ይሆናል፡፡
ሊግ፡- በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ዋልያዎቹን እንዴት አገኘካቸው?
የአብስራ፡- ኳስን ይዘው ይጫወታሉ፤ በቡድናችን ላይ ተስፋ ሰጪ ነገርን ተመልክቼያለው፤ የመዘናጋትና የአካል ብቃት ችግር ግን በቡድናችን ላይ ነበር፤ እሱ ሊሻሻል ይገባል፡፡
ሊግ፡- በአፍሪካ ዋንጫው ለአንተ ምርጡ ብሔራዊ ቡድን ማን ነው?
የአብስራ፡- በአብዛኛው ተመሳሳይ የሆነ አቋም ነው ያላቸው፤ ብዙዎቹ ጥሩ ጨዋታን አላሳዩንም፤ ለእኔ ጥሩ የሆነው ቡድን ኮትዲቯር ሲሆን የእኛም ቡድን ኳስኑ ይዞ ለመጫወት በመሞከር ጥሩ ነበር፡፡
ሊግ፡- እናጠቃል…?
የአብስራ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዛሬ ላይ ለደረስኩበት ደረጃ ብዙ ሰዎች ከጎኔ ሆነው ረድተውኛል፤ ቤተሰቦቼ በተለይም ደግሞ አባቴ ብዙ ዋጋ ሊከፍልልኝ ችሏል፤ ጎረቤቴ ዳዊት እስጢፋኖስን ጨምሮ አሰልጣኝ ደረጄ ተስፋዬ /አንገቴ/፣ አሳምነው ገብረወልድ፣ ዘሪሁን ሸንገታ፣ ታዲዮስ ሀይሉ፣ አሸናፊ በቀለ እና የፕሮጀክት አሰልጣኜን ብሩክ ገብረሃይንና አጠቃላይ ጓደኞቼን ከልብ ማመስገን እፈልጋለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P