ከመስከረም 2013 ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በዋና አሰልጣኝነት የመሩት ውበቱ አባተ ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥያቄ አቅርበው የነበረ ሲሆን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ የአሰልጣኙን መልቀቂያ በመቀበሉ በጋራ ስምምነት ተለያይተዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለነበራቸው ቆይታ ምስጋናውን እያቀረበ በቀጣይ የሥራ ሕይወታቸው መልካም የሥራ ጊዜ እንዲገጥማቸው ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል።