ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት እጩ የሆኑት አቶ መላኩ ፈንታ በርካታ መገናኛ ብዙሀን በተገኙበት የምረጡኝ ቅስቀሳ አካል የሆነ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
የራሳቸውን የትምህርት ዝግጅት እና ተቋም የመምራት ብቃት በማስተዋወቅ ለእግር ኳሱ ተቋማዊ ለውጥ በመስራት፣ ዓለም አቀፍ ተሰሚነቱ ከፍ ያለ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መገንባት እንደሚፈለጉ እጩ ተወዳዳሪው ፍላጎታቸውን አሳውቀዋል።
ስለ ስፖርቱ እውቀታቸው፣ የመምራት ልምድ፣ የፖለቲካ ጉዳይ የታሰሩበት የቀደመው ጉዳይን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎችን የመለሱት አቶ መላኩ፣ በጠቅላላ ጉባኤ የቦታ ለውጥ ጉዳይ አቋማቸውን ተጠይቀዋል።
”የቦታው ጉዳይ ሳይሆን በጠቅቅላላ ጉባኤ የተወሰነ ቦታን ለመቀየር የተሄደበት ርቀት ተቀባይነት የለውም፡፡ ግን የፈለገው ቦታ ቢሆን የኢትዮጵያ ቦታ እስከሆነ ድረስ እወዳደራለሁ ” ብለዋል።
“ፍትሃዊ ምርጫ እንጠብቃለን፤ እንደምመረጥ አምናለው እንደሚወራው በገንዘብ ምረጡኝ ድምፅ ለመቀየር እንደሚሰራ መረጃ ሰብስበናል ፍትሀዊ ከሆነ እንቀበላለን ውጤቱን ካልሆነ ግን እናጋልጣለን” ብለዋል።
በቀጣይ ቀሪ ሁለቱ እጩ ፕሬዝዳንቶች ራሳቸውን እንደሚያስተዋውቁ ይጠበቃል።