Google search engine

“አዳማ ከነማ የሁለተኛው ዙር ላይ ይበልጥ ይሻሻላል፤ የሊጉ ክስተት ቡድን የምለው ማንም የለም” /አዲስ ህንፃ/

 

የአዳማ ከነማ የመሃል ሜዳው ስፍራ ተጨዋች አዲስ ህንፃ ክለባቸው በሁለተኛው ዙር በሚኖረው የውድድር ተሳትፎው የመጀመሪያው ዙር
ላይ ከነበራቸው አቋም ጥሩ ለውጥን እና መሻሻልን እንደሚያሳዩ ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
የአዳማ ከነማ እግር ኳስ ክለብ በሊጉ ውድድር በአሁን ሰአት በ- ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ ውጤትና ደረጃም እንደሚሻሻል ተጨዋቹ
ያምናል፡፡
የአዳማ ከነማን የሊግ ተሳትፎ እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ አዲስ ህንፃን አናግረነው የሰጠን ምላሽ እንደሚከተለው ይቀርባል፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙርን በምን መልኩ እንዳጠናቀቁ
“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙርን በ6ኛ ደረጃ ለማጠናቀቅ ብንችልም የቡድናችን አቋም ያንን ያህል ምርጥ ነው ለማለት
አልችልም፤ ምርጥ ለመሆንም ብዙ ነገሮችን መስራት አለብን፤ ቡድኑንም ውጤታማም ማድረግ አለብን፤”
የአዳማ ከነማ የመጀመሪያ ዙር ጥንካሬው እና ድክመቱ
“አዳማ ከነማ በመጀመሪያው ዙር የነበረው ጠንካራ ጎን በሜዳው ሲጫወት ጎሎችን ማስቆጠር መቻሉ ሲሆን ድክመቱ ደግሞ በመከላከል
ላይ ባለው እንቅስቀሴ ያለጥንቃቄ ስለሚጫወት ጎሎች በቀላሉ የሚቆጠርበት መንገድ ነው፤ ይሄ በፍጥነት ሊሻሻል ይገባል፡፡”
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ፉክክርን በራሱ እይታ ሲመለከተው
“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን የመጀመሪያው ዙር ፉክክር እንደራሴ እይታ ስመለከተው ያንን ያህል ጥሩ የሚባል አይደለም፤ ጨዋታዎቹ
ጥንቃቄ እና የአቻ ውጤቶች ይበዙበታል፤ ብዙም አጥቅቶ የሚጫወት ቡድን አይታይምና ሊጉ ጠንካራ ፉክክር ተደርጎበታል ብዬ አላምንም፡፡
የሁለተኛው ዙር ላይ ግን ለውጦች የሚኖሩ ይመስለኛል፡፡”
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአዳማ ከነማ እቅዱ ምንድነው
“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ሲጀመር የክለባችን ዋንኛ እቅድ የነበረው እንደማንኛውም ቡድን የሊጉን ዋንጫ እናነሳለን ብለን ነው፤
አሁንም ተሻሽለን በመቅረብ ያን ነው የምንጠብቀው”፡፡
የአዳማ ከነማ የተጨዋቾች ስብስብ በአንተ አንደበት ሲገለፅ

“የአዳማ ከነማን የተጨዋቾች ስብስብ ከአምና እና ከካቻምናው አንፃር ስመለከተው ያንን ያህል ምርጥ እና አስገራሚ የሚባል ስብስብ
አለን ብዬ ለመናገር አልደፍርም፤ ያለፉት ጊዜያት ስብስባችን የተሻለ ነበር”፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ውድድርን ስትመለከት ለአንተ ክስተቱ ቡድን ማን ነው?
“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ውድድር ላይ የመቐሌ 70 እንደርታ ክለብ ሊጉን ከመምራቱ አኳያ ከሆነ እንጂ በሌላ
መስፈርት ለእኔ እስካሁን የሊጉ ክስተት ብዬ የምጠራው ቡድን ማንም የለም”፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው ዙር ላይ በምን መልኩ ለመቅረብ ተዘጋጅታችኋል? በአቋም ደረጃስ ከመጀመሪያው ዙር አንፃር
ለውጥስ ይኖራችኋል?
“አዳማ ከነማ የሊጉ የሁለተኛው ዙር ላይ ራሱን ለማጠናከር ሁለት ተጨዋቾችን ማለትም ብሩክ ቃልቦሬን እና አብደላ የተባለን ተጨዋች
ብቻ ያስመጣበት ሁኔታ ቢኖርም ከመጀመሪያው ዙር ተሳትፎአችን አንፃር ለውጥ ይኖረናል የሚል እምነት ነው አለኝ፤ ሁለተኛው ዙር ላይም
ጥሩ ውጤት እናመጣለን”፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው ዙር ግጥሚያችሁን ነገ ከ—–ጋር ታደርጋላችሁ፤ ከጨዋታው ምን ውጤት ትጠብቃለህ?
“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ከ6ኛ ጋር የሚኖረን የነገው ጨዋታ በሁለተኛው ዙር ላይ ለምንጓዝበት መንገድ ወሳኝ ስለሆነ ለጨዋታው
ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተነዋል፤ ግጥሚያውንም በድል አጠናቅቀን ለመመለስም ዝግጁ ነን”፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውስጥ የተለያዩ ክለቦች ውስጥ ገብተህ ተጫውተሃል፤ በእግር ኳስ ህይወትህ ደስተኛ ነህ?
“በአብዛኛው የኳስ ህይወቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፤ እግዚአብሄር ይመስገን ብዬም ነው ስራዬን የምሰራው፤ ያም ሆኖ ግን አልፎ አልፎ በአንዳንድ
ክለቦች ውስጥ ኳስን ስጫወት የተከፋሁባቸው አጋጣሚዎች የሉም ማለት አልችልም፤ እነዚህ ሁኔታዎች ደግሞ የተለያዩ ክለቦች ውስጥ
ስጫወት አሰልጣኞች በሚቀያየሩበት ወቅት ላይ ከአንዳንዳቸው ጋር ሳትስማማ ትቀርና ወደቤትህ የምታመራበት ሁኔታዎች ያጋጥሙካል፡፡ ያ
ከአንተ ጋር ያልተስማማው አሰልጣኝ መልሶ ቡድኑ በሚቸገርበት ሰአት መልሶም ይጠራካልና በመሰለፍና ባለመሰለፍ ሁኔታዎች እንደዚሁም
በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ደስተኛ ያልሆንኩበትም ሁኔታዎች አጋጥመውኛልና እነዚህን አልረሳም”፡፡
የአዳማ ከነማን በቀጣይነት በምን መልኩ ለመጠቀም ዝግጁ ነህ?
“አዳማ ከነማን በጥሩ ሁኔታ ለማገልገል ያለኝ ፍላጎት አሁንም ቢሆን ከፍተኛ ነው፤ በሚቻለኝ አቅም ሁሉ ቡድኑን ለመርዳትና ውጤታማም
ለማድረግ ዝግጁ ነኝ”
በመጨረሻ….
“ለኢትዮጵያ ህዝብ ፈጣሪ ፍቅርን እና ሰላምን እንዲሰጣቸው እመኛለሁ”፡፡
የአዳማ ከነማ ክለብ የመሃል ሜዳ ስፍራው ተጨዋች አዲስ ህንፃ የሁለኛው ዘር ላይ በሚኖራቸው አቋም ከመጀመሪያዬ ዙር ለውጥን እና
መሻሻልን እንደሚያሳዩ ሃሳቡን ገልጿል፡፡
የአዳማ ከነማ ክለብ የሊግ ውድድሩ ላይ በአሁን ሰአት በ- ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ ውጤትና ደረጃም እንደሚሻሻል ተጨዋቹ እምነትን
ጥሏል፡፡ የአዳማ ከነማን የሊግ ተሳትፎ እና ተያያዝ በሆኑጉዳዮች ዙሪያ አዲስ ህንፃን አናግረነዋል ተጨዋቹም ምላሹን እንደሚከተለው
ሰጥቷል፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P