test
Google search engine

አፈወርቅ ኃይሉ /ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ/


መሸሻ ወልዴ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን
ለቻን አፍሪካ ዋንጫ ከመረጣቸው
ተጨዋቾች መካከል አንዱ ለወልዋሎ
አዲግራት ቡድን በመጫወት
ላይ የሚገኘው አፈወርቅ ኃይሉ
ነው፤ ይሄ ተጨዋች ዘንድሮ ጥሩ
የውድድር ዓመታትን ያሳለፈ ሲሆን
ይሄን ተጨዋች በኳስ ህይወቱና
ሌሎች ጉዳዮችን በማንሳት ጥያቄን
አቅርበንለት ምላሹን ሰጥቷል፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ጅማሬህና
ውልደትህ የት ነው?
አፈወርቅ፡- የእግር ኳስን መጫወት
የጀመርኩት ተወልጄ ባደግኩበት የተ/
ሃይማኖት ከረዩ አካባቢ እንደዚሁም
ደግሞ በጨፌ እና በብሪሞ ሜዳ ላይ
ነው፤ እዛም ከህፃንነቴ እድሜዬ አንስቶ
ከእኩያ ጓደኞቼ ጋር በመጫወት
አሳልፌያለው፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን ልጅ ሆነህ
ስትጫወት ለየት ለየት ቡድኖች
ተጫውተህ አሳለፍክ?
አፈወርቅ፡- የልጅነት ዕድሜዬ ላይ
በሰፈር ደረጃ ያኔ የተጫወትኩባቸው
ክለቦች ይበቃል፣ አንለያይም፣ ወንዳታ
ንጉሴ እና ሶዶርታ ይባላሉ፤ በእነዚህ
ቡድኖች ውስጥም ሆኜ ነው በጨፌ
ሜዳ ላይና በብሪሞ ሜዳ ላይ ስጫወት
የነበረው፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን ስትጫወት
እነማንን በማድነቅ ነው ያደግከው?
አፈወርቅ፡- በእግር ኳስ
ተጨዋችነት ዘመኔ እኔ የማደንቃቸው
ተጨዋቾች ከሀገር ውስጥ ሙሉዓለም
ረጋሳን፤ መስፍን ዳምጠው /ሚጣን/ በረከት
ተሰማንና ቢኒያም ተፋራን ሲሆን ከባህር
ማዶ ተጨዋቾች ደግሞ ስቴቨን ጄራርድንና
ዚነዲን ዚዳንን ነው አድንቄ ያደግኩት፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን መጫወት
ስትጀምር በየቱ ስፍራ ላይ ሆነህ ነው፤
በረኛ፣ ተከላካይ፣ አማካይ ወይንስ
አጥቂ….?
አፈወርቅ፡- የልጅነት እድሜዬ ላይ
ኳስን መጫወት ስጀምር በረኛ ነበርኩ፤
ያን ጊዜ እንደውም በሰፈር ደረጃ በተዘጋጀ
ውድድር ለሁለት እና ለሶስት ጊዜያት
ከጓደኞቼ ከእነ ሚሊዮንና ሌሎች ጥሩ
ችሎታ የነበራቸው ተጨዋቾች ጋር
ስጫወት ኮከብ ግብ ጠባቂ ተብዬም ተሸልሜ
ነበርና መጫወት የጀመርኩት በበረኝነት
ነው፤ ሆኖም ግን ያን ጊዜ ላይ ከግብ
ጠባቂ ይልቅ ለሜዳላይ ስፍራ ተጨዋቾች
በተደጋጋሚ ጊዜ ከፍተኛ አድናቆት ይሰጥ
ስለነበር እኔም በረኝነቱን ትቼ ወደ ኳስ
ተጨዋችነቱ ሙያ ላይ ልገባ ቻልኩ፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን በክለብ ደረጃ የት
የት ተጫወትክ?
አፈወርቅ፡- መጀመሪያ ለኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ የታዳጊ ቡድን ነው
የተጫወትኩት፤ እዛም የሁለተኛው ዙር
ላይ ነው ክለቡን ለማጠናከር በሚል
በአሰልጣኝ ፈለቀ እና በአሰልጣኝ አለባቸው
አማካኝነት በአሰልጣኝ ጋሻው አረዳ
ለሚሰለጥነው ለባልቻ አባነፍሶ ትምህርት
ቤት ካፒቴን ሆኜ በምጫወትበት ሰዓት
ለክለቡ ተመልምዬ በመምጣት ለአራት
ወር ያህል እንድጫወት የተደረግኩት
በኋላ ላይ ግን ወደዋናው ቡድን ለማደግ
በተሰጠው የሙከራ እድል ከሲ ቡድን እኔ
ከቢ ቡድን ደግሞ 11 የሚደርሱ ተጨዋቾች
ከኃይኮፍ ጋር በተደረገ የወዳጅነት ግጥሚያ
ላይ በአሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻና ሲሳይ
ከበደ አማካይነት በመመረጥ ሶስት
የምንደርስ ተጨዋቾች ማለትም ከቢ ቡድን
ዋለልኝ ገብሬና ወንድወሰን ከሲ ቡድን
ደግሞ እኔ እንድናድግ ተደርገን የዋናውን
ቡድን ልቀላቀል ቻልኩ፤ በኋላ ላይ ግን
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ወደ ቡድኑ ሲመጣ
እኔ ልጅ ነበርኩና አንተ ህፃን ነህ በሚል
እንድጠነክር በሚል ወደ ተስፋ ቡድን
ሲመልሰኝ ከክለቡ ጋር ሳልቀጥል ቀረሁና
በአሰልጣኝ ባንቲ ወደሚመራው የየካ ክፍለ
ከተማ ቡድን አመራሁ እዛም ጥሩ ቆይታ
ኖሮኝ ቡድኑን ሐዋሳ ላይ በተደረገ ጨዋታ
ውጤታማ በማድረግ ወደ ብሄራዊ ሊግ
እንዲገባ አደረግን፤ ከዛም በኋላ ለድሬዳዋ
ፖሊስ ለሁለት ዓመት ያህል ተጫወትኩና
ወልዋሎን ተቀላቀልኩ፡፡
ሊግ፡- የወልዋሎ አዲግራት ክለብ
ውስጥ የነበረህን የውድድር ዘመን ቆይታህን
በምን መልኩ ትገልፀዋለህ? የቡድኑን
ውጤት በተመለከተስ ምን ትላለህ?
አፈወርቅ፡- የወልዋሎ አዲግራት
ዩኒቨርሲቲ ክለብ ውስጥ ያለኝ የእስካሁን
የተጨዋችነት ቆይታ በጣም ጥሩ
የሚባል ሲሆን በዚህ በምስረታው ከቅዱስ
ጊዮርጊስ ክለብ ቀጥሎ የብዙ ዓመታትን
ባስቆጠረው ክለብ ውስጥ ተጫውቼ ማለፌ
የተለየ የደስታ ስሜት ነው የሚሰማኝ፤
የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እግር
ኳስ ክለብ በውድድር ዘመኑ ላይ
ያስመዘገበው ውጤት በአቻነቱ ወደር
የማይገኝለት ነው፤ ይህንን ስልም
ያለምክንያት አይደለም፡፡ ወልዋሎ
በፕሪምየር ሊጉ የዚህ አመት ተሳትፎው
አጠቃላይ ግጥሚያውን ያደረገው ከሜዳው
ውጪ ነው ማለት ይቻላል፤ ከመቐለ 70
እንደርታ ክለብ ባለው ከኳስ ውጪ ልዩነት
አንፃር የመቐለ ደጋፊዎች ከቡድናችን
ይልቅ ከእኛ ጋርበተቃራኒነት ለሚጫወቱ
ሁሉም ቡድኖች ድጋፍን የሚሰጡበትና
በጫና ውስጥ ሆነንም የምንጫወትበትን
ሁኔታም ስለሚፈጥሩበሜዳችን ማግኘት
የነበረብንን ውጤት እንድናጣ የተደረገበት
ሁኔታ ቢኖርም የሜዳችን ውጪ
ጨዋታዎች ላይ ከሜዳችን በተሻለ ውጤት
ስለነበረን በአጠቃላይ ያስመዘገብነው
ውጤት ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ሊግ፡- የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ
ደጋፊዎችን በሚመለከት ምን ትላለህ?
አፈወርቅ፡- የወልዋሎ አዲግራት
ዩኒቨርሲቲ ደጋፊዎችን በቀላል ቃላቶች
የምትገልፃቸው አይደለም፤ እዛ ያለው ህዝብ
ኳስን በጣም ይወዳል፡፡ ቡድናቸውን ደግሞ
ከምንም ነገር በላይ አስበልጠው ሲደግፉትና
ሲያበረታቱትም ይታይል፤
እነሱ ወልዋሎን የህይወታቸው
መገለጫ አድርገውም ነው
የሚዘምሩለት፤ ብዙ ህዝብም ነው
ጨዋታችንን የሚከታተለው፤ ከዛ
ውጪም ደጋፊውን ስትመለከት
እስከማልቀስም ትደርሳለህ፤ ይሄ
ቡድን ክልል ሄዶ ሲጫወትና
አሸንፎ ሲመጣ እናቶች ሁሉ ናቸው
ከቤታቸው በመውጣት ጭምር
የሚቀበሉትና ይሄን ስትመለከት
ለእዚህ ቡድን መጫወት መቻል
የተለየ የደስታ ስሜት ነው
እንዲሰማህ የሚያደርግህ፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ
ላይ የወደፊት ምኞትህ ምንድነው?
አፈወርቅ፡- የእግር ኳስን
እየተጫወትኩ ባለሁበት የአሁን
ሰአትየእኔ ዋናው ምኞቴ እና
እሳቢዬ እንደ ትልልቅ ተጨዋቾች
ነውና ወደ ባህር ማዶ በመጓዝ
በፕሮፌሽናል ደረጃ መጫወት
ነው፤ ከዛ ውጪም ለብሄራዊ
ቡድንም በመመረጥ መጫወት
እፈልጋለሁ፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ብሄራዊ
ቡድን ውስጥ የመመረጥ እድልን
አግኝተሃል፣ ስሜቱን እንዴት
አገኘኸው?
አፈወርቅ፡- የኢትዮጵያ
ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ተመርጦ
መጫወቱ ላይ ከእዚህ ቀደም
ከአንዴም ሶስቴ የታዳጊ፣የወጣት
ብሎም ደግሞ የኦሎምፒክ ብሄራዊ
ቡድኖች ምርጫ አምልጦኛል፤ ያኔ ለሃገር
መመረጥ አንተ እንደፈለግከው ሳይሆን
አሰልጣኙ እንደፈለገው በመሆኑ ይሄንን
አምኜ ተቀብዬዋለው፤ ይሄንን ለብሔራዊ
ቡድን የመመረጥ እድልን አሁን ላይ
በኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ
አማካኝነት ያገኘው በመሆኑ አሁን ላይ
በጣም ደስ ብሎኛል፡፡
ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን
መመረጥ መቻል እንደ ተጨዋች ስሜቱ
በጣም ይለያያልና ምናልባት በአንተ ዘንድ
የተለየ የሚባል ነገርይኖር ይሆን?
አፈወርቅ፡- አዎን፤ ለሃገር መመረጥ
እና መጫወት መቻል ትልቅ ክብር
እና ኩራትም ነው እኔም የእግር ኳሱን
እየተጫወትኩ እስካለሁበት የቅርብ ጊዜያት
ድረስ ለራሴ የገባሁት አንድ ቃል ነበረኝና
ያንን ነው ተግባራዊ ያደረግኩት፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ
ቡድንማሊያዎችንም ሆነ ብሄራዊ ቡድኑን
የሚገልፁ ቲሸርቶችን ጠንክሬ ሰርቼና

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P