Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

ኢትዮጵያዊያን እንደኮከብ ያበሩበት የአትላንታው ደማቅ ውድድር

“ህዝቦችን ከማቀራረብ ባሻገር ሃገራችንን ማገዝ ቀዳሚ ተግባራችን ነው” አቶ አብይ ኑርልኝ የESFAN ፕሬዘዳንት


በዓለምሰገድ ሰይፉ


የምር ኢትዮጵያዊ በመሆኔ ኮራሁ፡፡ በዛች የሃያላን ሃገራት ቁንጮ በምትባለው አሜሪካን ሃገር ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቼና እህቶቼ እንደዛ እንደኮከብ አብርተው ሳያቸውና የሃገራችን ሰንደቅ አላማ ከጥግ ጥግ ድረስ ተውለብልሶ ሳየው ይሄን ታላቅ አንድነት መፍጠር ለቻለው በሠሜን አሜሪካ የባህል ስፖርት ፌዴሬሽን ESFAN ላቅ ይለ ምስጋና ለማቅረብ ወደድኩ፡፡ ተግባራችሁ አኩሪ ነውና በርቱ ልላችሁ እወዳለሁ፡፡
ከተመሰረተ እነሆ ዘንድሮ 36ኛ አመቱን ያስቆጠረው ESFAN ይህንን ሃሳብ ሲጠነስስ እዚህ ታላቅ ደረጃ ላይ ይደርሳል ብሎ የገመተ ማንም አልነበረም፡፡ ምንም እንኳን ሂደቱ እጅግ አድካሚና ፈታኝ ቢሆንም እውነትና የሃገር ፍቅር በውስጣቸዉ የታተመና በየጊዜው ፌዴሬሽኑን ተፈራርቀው ሃገር ወዳድ ዜጎች እነሆ አሁን ይሄን ፌዴሬሽን በሁለት እግሩ እንዲቆም አስችለውታል፡፡
ይህ ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ ያለውና ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጉጉት የሚጠብቀው አመታዊ ውድድር ህዝቦችን ከማቀራረብና የሃገራችን ውብ ገፅታ ከማስተዋወቅ ባሻገር በጊዜው በስፖርቱና በማህበራዊ ህይወት ለሃገራቸው ውለታ የፈፀሙ ዜጎችን በማስታወስ በክብር እንግድነት በመጋበዝ የላቀ ሚና ተጫውቷል፡፡ ራዕየ ስራው ESFAN በየአመቱ በሚደረገው ፌስቲቫል ህዝቦችን ከማቀራረብ ባሻገር ለሚወዷት ሃገራቸው አንድ ነገር ማበርከት እንደሚፈልጉ ጎልማሳው የፌዴሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ አብይ ኑርልኝ ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡ ርቀን ብንኖርም ሁሌም ሃሳቦችንና ልባችን ከሃገራችን ርቆ አያውቅም፡፡ እናም ለዚህች ለምንወዳት ሃገራችን በህይወት እያለን አንድ ቋሚ ቅርስ ማበርከት ይጠበቅብናል፡፡ ለምሳሌ በየአመቱ ከምናካሂደው ውድድር ለሚገኘው ገቢ በየአመቱ እያሰባሰብን ህዝባችንን በእውቀት ማነፃ የሚያስችል ላይብረሪ ብንከፍት የሚል እቅድ አለን በማለት ፕሬዘዳንቱ አቶ አብይ አውግተውኛል፡፡
ሁሌም ከውስጣቸው የሚንቀለቀል ከፍተኛ የሆነ የሃገር ፍቅር የሚነበብባቸው ፕሬዘዳንት በቀጣይነት ፌዴሬሽኑን አንድ በተግባር የሚፈተሽ አሻራውን በትውልድ ሃገራቸው ላይ የማኖር ራዕይ እንዳላቸው አስረግጠው ነግረውኛል፡፡ ሃሳባችሁ ይሳካ ዘንድ ልባዊ ምኞቴ ነው፡
የዘንድሮው የኢትዮጵያዊኖች የስፖርት የባህል ፌስቲቫል ለ36ኛ ጊዜ የተሰናዳው በአትላንታ ጆርጂያ ሲሆን በዚሁ ውድድር ላይም ፌዴሬሽኑ በላከልኝ ግብዣ ታድሜ ነበር፡፡ ይኸው ደማቅና ስኬታማ ፌስቲቫል እጅግ በተቀጀና በተናበበ ሁኔታ ያንን ሀሉ እንግዳ ያለአንዳች እንከን ማስተናገድ መቻላቸውን ስመለከት ፌዴሬሽኑ ምን ያህል በተጠናና በእቅድ የሚመራ ተቋም መሆኑን ያሳይል፡፡ ለ32 ተሳታፊ ቡድኖችና በውድድሩ ላይ ለሚታመደሙ እንግዶች በአጠቃላይ ደረጃውን የጠበቀ የሆቴል በማሰናዳትና ለሌሎች አርአያ መሆን የሚችል የአንድ ሳምንት የውድድር መርሃ ግብር በአግባቡ መወጣታቸውን ስመለከት የእውነት ይህ ፌዴሬሽን ላቅ ያለ ምስጋና ማግኘቱ የሚበዛበት አይሆንም፡፡
የዘንድሮው የአትላንታው ውድድር ለየት የሚያደርገው ከአሁን በፊት ፌዴሬሽኑ ለሚያዘጋጀው አመታዊ ደማቅ ድግስ የሃገራችን ከፍተኛ አመራሮች እውቅና የነፈጉበት ጊዜ የነበረ ሲሆን ዘንድሮ ግን ሁሉ ነገር ተቀይሮ መንግስት ለፌዴሬሽኑ የላቀ እውቅና በመስጠቱ በውድድሩ መክፈቻና መዝጊያ ፕሮግራም ላይ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አቶ ፍፁም አረጋ በመገኘት ለፌዴሬሽኑ ያላቸውን አጋርነት በይፋ አረጋግጠዋል፡፡ በአሜሪካ የተለያዩ ስቴቶች የሚገኙ ኢትዮጵያኖች በታደሙበት በዚህ ደማቅ አመታዊ ፕሮግራም ላይና ኢትዮጵያዊነት በከፍተኛ ደረጃ የተቀነቀነበትና በስፖርቱም ዘርፍ ነገ ሃገራቸውን በአግባቡ መጥቀም የሚችሉ ምርጥ ክህሎት ያላቸው ታዳጊዎችን ማየት የቻልንበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ይኸው ለትርፋማነት ያልተቋቋመው ዋነኛ አላማና ግቡ በየበታው የተበታተኑ ወገኖችን በየአመቱ በማሰባሰብ ብሄራዊ አንድነት ለመፍጠር የሚተጋው ፌዴሬሽን ከምን በላይ ግልፅና ተጠያቂነት ያለው የፋይናንስ እንቅስቃሴው ምን እንደሚመስል ለሚዲያው ግልፅ በማድረግ በገንዘብም ይሁን በእውቀት ህዝቡን ማገልገል ብቻ እንደሆነ ማስመስከር ችለዋል፡፡ ይህ በገንዘብ ሊተመን የማይችለው በባዕድ ሃገር ኢትዮጵያዊያን እንደ ክዋክብት ለሚያበሩት አመታዊ ውድድር አድማሱ የሠፋ ይሆን ዘንድ መንግስት ለዚህ ፌዴሬሽን በሚችለው አቅም ሀሉ ሁለንተናዊ እገዛ ሊያበረክትለት ይገባል እንላለን፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P