Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ኢትዮጵያ ቡናን ማሸነፋችን ፈፅሞ አያስኮፍሰንም” “አሁን ላይ ይሄ  ቡድን  ዋንጫውን  ያነሳል ብሎ መገመት ከባድ ይመስለኛል” ስንታየሁ መንግስቱ /ወላይታ ድቻ/

 

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ ቡናን በስንታየሁ መንግስቱ /አቡሽ/ ሁለት ግቦችና በቃልኪዳን ዘላለም ቀሪ ግብ 3-1 በማሸነፍ  የውድድሩ  መሪው ክለብን ፋሲል ከነማን በነጥብ ተስተካክሏል፤ ለኢትዮጵያ ቡና ከባዶ ከመሸነፍ የዳኑበትን ጎል ደግሞ ታፈሰ ሰለሞን አስቆጥሯል፤ ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ ቡናን በእርስ በርስ ግንኙነት በማሸነፍ አሁንም የበላይነትን የያዘ ሲሆን በማክሰኞው ዕለቱም የአራተኛ ሳምንት ግጥሚያ በከፍተኛ ፍላጎት በመጫወት ተሽለው ታይተዋል፡፡

ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ ቡናን በረታበት ጨዋታ ለቡድኑ የተገኙትን ሁለት የድል ጎሎችን ያስቆጠረውን ስንታየሁ መንግስቱን በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ያናገረው ሲሆን የተጨዋቹ ምላሽም በሚከተለው መልኩ ቀርቧል፡፡

ሊግ፡-ኢትዮጵያ ቡናን አሸንፋችሁ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግመሪውን ፋሲል ከነማን በነጥብ ተስተካክላችዋል፤  ባገኛችሁት የድል ውጤትምን ተሰማህ?

ስንታየሁ፡- ኢትዮጵያ ቡና የሀገሪቱ ትልቅ ቡድን ነው፤ እነሱን ማሸነፋችን ነጥባችንን ከፍ እንድናደርግና ከመሪው ፋሲል ከነማም ጋር  በእኩል ነጥብ ላይ እንድንቀመጥ አደርጎናል፤ ባገኘነው የድል ውጤትም በጣም ደስ ብሎናል፤ ከዛም ውጪ በቡና ላይ የተጎናፀፍነው ድል እኛን የሚያስኮፍሰን ሳይሆን ለተከታታይ ጨዋታዎች ጠንክረን እንድንቀርብም የሚያስችለን ስለሆነ ጨዋታውን  በዛም መልኩ ነው ያየነው፡፡

ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡናን ለማሸነፍ ያስቻላችሁ ዋንኛው ምክንያት ምንድን ነው? ስለተጋጣሚያችሁ አቋምስ ምን የምትለው ነገር አለ?

ስንታየሁ፡- ስለ አንድ ቡድን አቋም ለመናገር  በርካታ ጨዋታዎችን መመልከት ይኖርብሃል፤  ሊጉ ገና ጅማሬ ላይ ነው፤ ከወዲሁ  እንዲህ ነው ብሎ ስለ አንድ ቡድን መገመትም ከባድ  ነውና ስለ ቡናዎችም እንዲህ ናቸው ብዬ ለመናገር አልደፍርም፤ በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ማሸነፍና መሸነፍ ያለና የሚኖር ነው፤ እኛም ቡናን በዕለቱ በነበረው ጨዋታችን ላይ ያሸነፍነው ያገኘናቸውን አጋጣሚዎች ስለተጠቀምንበት ነው፡፡

ሊግ፡- ወላይታ ድቻ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉከአራት ጨዋታዎች በሶስቱ አሸንፎ ጥሩ አጀማመርን አድርጓል፤ የእዚሁ ምክንያት ምንድን ነው…..?

ስንታየሁ፡- በዘንድሮው የሊግ ተሳትፎአችን በውጤት ደረጃ መልካም የሚባል አጀማመርን እያደረግን ያለበት ዋናው ምክንያት ህብረታችንና ፍቅራችን ከከዚህ ቀደሙ በጣም የጠነከረ በመሆኑና አሰልጣኛችንም የሚሰጠንን በቡድን ስራ ላይ ያተኮረን ስራ በአግባቡ ልንተገብር ስለቻልን ነው፡፡

ሊግ፡-ወላይታ ድቻ ጠንካራና ክፍተት ጎኑ ምንድን ነው?

ስንታየሁ፡- ከጠንካራ ጎናችን ውስጥ አንዱ በስብስብ ደረጃ ጥሩ ተጨዋቾችን ይዘናል፤ ሌላው ዋንኛው ጥንካሬያችን ደግሞ በአሰልጣኛችን ከጨዋታዎች በፊት ልምምድ ላይ የሚሰጠንን ስራዎች ሜዳም ስንገባ በአግባቡ የምንሰራና ክለባችንም ተገማች እንዳይሆን ስላደረግንም ይህንን ጥንካሬ ተመልክቼያለው፤ በክፍተት ደረጃ የማነሳው ደግሞ እኔ ተጨዋች ስለሆንኩ ምንም የምለው የለም፤ ከእኔ ይልቅ አሰልጣኛችን ለእዚህ መልስ ቢሰጥበት ነው የምመርጠው፡፡

ሊግ፡- ወላይታ ድቻ ፋሲል ከነማን በነጥብ ተስተካክሎ ከመምጣቱ አንፃር ዘንድሮ የዋንጫው ተፎካካሪ ይሆናል?

ስንታየሁ፡- አዎን፤ ያም ሆኖ ግን የዋንጫው ተፎካካሪዎች እኛ ብቻ ሳንሆን ሁሉም ክለቦች ናቸው፤ በእዚህ ዓመት እከሌ ደካማ ነው የምትለው የለም፤ ዝቅተኛ ግምት የተሰጣቸው ቡድኖች እያሸነፉም ነው፤ ስለዚህ ሁሉም ቡድን በተፎካካሪነቱ ይቀጥላል፡፡

ሊግ፡- ለወላይታ ድቻ ጎል ማስቆጠር ጀምረሃል፤ ከወቅታዊ ብቃትህ በመነሳት ዘንድሮ በምን አቋምህ እንጠብቅህ?

ስንታየሁ፡- ለወላይታ ድቻ ባደረግኳቸው ሶስት ያህል ጨዋታዎች በአሰልጣኜ ውሳኔ ነው ከጉዳት ጋር ታግዬ  ወደ ሜዳ ስገባ የነበረው፤ ከቡና ጋር ስንጫወት ግን ወደ ማገገሙ መጥቼ ስለነበር በእዛ ትልቅ ጨዋታ ላይ ሁለት የድል ጎሎችን ለማስቆጠር ስለቻልኩ በጣም ደስ ብሎኛል፤ አጥቂ ስትሆን ጎል ሁሌም ከአንተ ይጠበቃል፤ ከእዚህ በኋላም ወደ ጤንነቴ ሙሉ ለሙሉ ስመለስም በርካታ ግቦች እንደሚኖሩኝና ክለቤንም በጥሩ አቋሜ ለውጤት እንደማበቃው እርግጠኛ ነኝ፡፡

ሊግ፡- ለወላይታ ድቻ በዘንድሮ የውድድር ተሳትፎ ምን ያህል ግቦችን ልታስቆጥርለት አስበሃል?

ስንታየሁ፡- ባሳለፍነው ዓመት የቡድኑ ቆይታዬ 11 ግቦችን ነበር ለማስቆጠር የቻልኩት፤ ዘንድሮ ይሄን ሪከርድ አሻሽለዋለሁ፡፡

ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉያለፉት አራት ሳምንታት ጨዋታችሁ በድሬዳዋ ከተማ ብቻ ነበር ሽንፈትን ያስተናገዳችሁት፤ ያ ውጤት አስቆጪ ነበር?

ስንታየሁ፡- በጣም፤ ምክንያቱም ባለቀ ሰዓት ላይ ነበር ግቡ የተቆጠረብን፤ ያም ሆኖ ግን ከዛ ጨዋታ ሽንፈት ብዙ የተማርነው ነገር ስላለና በቁጭት ስሜት ላይም ሆነን ስራን ስለሰራን ባለፉት ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ የአሰልጣኛችንን ታክቲክ በመተግበር የድል ውጤትን ልናስመዘግብ ችለናል፡፡

ሊግ፡- ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ዓምናና ዘንድሮ ስታነፃፅረው?

ስንታየሁ፡- በጣም ልዩነት አለው፤ ባለፈው ዓመት የተወሰነ ቡድን ነበር ጠንካራ የነበረው ዘንድሮ ግን አብዛኛው ክለብ ጠንክሮ መጥቷል፤ ከከፍተኛው ሊግ የመጡት አዲስ አበባ ከተማና  አርባምንጭ እራሳቸው የሊጉን የፉክክር ድምቀት እየጨመሩት ይገኛልና በአጠቃላይ በቡድኖች ላይ መሻሻልን ተመልክተናል፡፡

ሊግ፡- ወላይታ ድቻ ከዚህ በፊት ላለመውረድ ከመጫወቱ አንፃር የአሁኑን ውጤት ስትመለከተው?

ስንታየሁ፡- ያ ያለፈ ታሪክ ነው፤ ከዚህ በኋላም በዛ ደረጃ ላይ እኛ አንገኝም፤ የምንጫወተው ለዋንጫው ፉክክር ነው፡፡

ሊግ፡- ባሳለፍከው የኳስ ህይወት ደስተኛ ነህ? ለማን ለማን ቡድኖችስ ተጫወትክ?

ስንታየሁ፡- የኳስ ጅማሬዬ ተወልጄ ካደግኩበት ወላይታ ሶዶ ወረዳ የሚጀምር ሲሆን በክለብ ደረጃ ለአርባምንጭ ከተማና ኮቪድ ገብቶ ውድድር በተቋረጠበት ዓመት ላይ ደግሞ ወደ ባህርዳር ከተማ ላመራ ችያለው፤ አሁን ደግሞ ለወላይታ ድቻ በመጫወት ላይ እገኛለው፤ በእስካሁኑ የኳስ ህይወት ቆይታዬም በምወደው ሙያ ውስጥ ያለው ስለሆንኩም በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡

ሊግ፡- የእግር ኳስን መጫወት ስትጀምር ለአንተ አርኸያ የሆነክና ያደነቅከው ተጨዋች ማንን ነው?

ስንታየሁ፡- በሀገር ውስጥ ደረጃ ብዙ ተጨዋቾች ያሉ ቢሆንም የሽመልስ ጉግሳ አድናቂ ሆኜ ነው የመጣሁት፤ ከባህርማዶ ተጨዋቾች  ደግሞ ያደነቅኳቸው ተጨዋቾች ሮሜሉ ሉካኩንና ዝላታን ኢብራሂሞቪችን ነው፡፡

ሊግ፡- በወላይታ ድቻ የተጨዋቾች ስብስብ ውስጥ የክለቡ አዝናኝ ተጨዋቾች እነማን ናቸው?

ስንታየሁ፡- ብዙ ተጨዋቾች ቢኖሩም ፅዮን መርዕድ፣ አናጋው ባደግ፣ ያሬድ ዳዊትና ደጉ ደበበ ሲኖሩ ጨዋታን ስለሚያደምቁት እነሱን ነው ከሁሉም በላይ የተመለከትኩት፡፡

ሊግ፡- የአንተ ባህሪይ በምን ሁኔታ ይገለፃል?

ስንታየሁ፡- ስራ ላይ ቀልድ አላውቅም፤ ከዛ ውጪ ያለው ባህሪዬ ደግሞ ከጓደኞቼ ጋር መቀላለድ በጣም ደስ ይለኛል፡፡

ሊግ፡- ከእግር ኳስ ውጪ ያለህን ጊዜ በምን መልኩ ታሳልፋለህ?

ስንታየሁ፡- በአብዛኛው ፊሊሞችን በማየትና ከጓደኞቼ ጋር በመጫወት ነው፤ ሌላው ደግሞ በቂ እረፍትንም ለማድረግ ተኝቼ አሳልፋለው፡፡

ሊግ፡- ወላይታን አጠር ባለ ቃላት ግለፃት ብትባል?

ስንታየሁ፡- ወላይታ ለኑሮ በጣም የምትመች ሀገር ናት፤ በእንግዳ ተቀባይነትና የፍቅር ሀገር በመሆኗም ብዙዎች ያውቋታል፤ ከዛም በተጨማሪ ክለቡን በፍቅር የሚወዱና የትም ስንጫወት ደከመኝና ሰለቸኝ ሳይሉ የሚያበረታቱን በርካታ ደጋፊዎች ያሏት ስለሆነም ለእዚህ ቡድን በመጫወቴ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡

ሊግ፡- በእረፍት ጊዜያትህ ወደ ትውልድ መንደርህ ሊመጣ ላሰበ አንድ ወዳጅህ ሰው አንድ ቦታን አስጎብኝ ብትባል ምንን ልታሳየው ትችላለህ? ምንስ ትጋብዘዋለህ…

ስንታየሁ፡- እሱ ይምጣ እንጂ ምንም ችግር የለም፤ የማስጎበኘው በወላይታ ውስጥ የሚገኘውን አጆራ ፏፏቴን ነው፤ የምጋብዘው ደግሞ እኛ ወላይታዎች በጣም ስለምንታወቅበት ቁርጥ ስጋን ከዳጣ ጋር ነው፡፡

ሊግ፡- በእናንተ ቤተሰብ ውስጥ እግር ኳስን የምትጫወተው አንተ ብቻ ነህ?

ስንታየሁ፡- አዎን፤ ኳስ ተጨዋቹም ስፖርተኛውም እኔ የመጨረሻው ልጅ ነኝ፤ ሶስት እህቶቼና አንድ ወንድሜ  ደግሞ በሌላ ሙያ ውስጥ ነው የሚገኙት፡፡

ሊግ፡- የወደፊት ግብና እልምህ ምንድን ነው?

ስንታየሁ፡- ወላይታ ድቻን ለጥሩ ውጤት አብቅቼ ስሙን ከፍ ከማድርግ ባሻገር ለብሔራዊ ቡድን ተመርጦ መጫወትን እፈልጋለው፤ ወደ ውጪ ሀገር በመውጣትም ከፍ ባለ ሊግ ደረጃም መጫወት ዋንኛው እልሜ ነው፡፡

ሊግ፡- በመጨረሻ…..?

ስንታየሁ፡-እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በቅድሚያ ማለት የምፈልገው ሁሉም ነገር የሚኖረው ሀገር ሰላም ስትሆን ነውና ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርገው፤ በመቀጠል  በእግር ኳስ ተጨዋችነት የላቀ ደረጃ ላይ ለመድረስ እንድችል ሁሌም ቢሆን በርትቼ እየሰራው ነው፤ በአቋሜም ላይ ለውጦች እንዲኖረኝ ያደረጉ አካላቶች አሉና እነሱን ማመስገን እፈልጋለው፤ መጀመሪያ ቅድሚያውን የሚወስደው ፈጣሪ ነው፤ ከዛ ቤተሰቦቼ እና በተለይም ደግሞ እህቶቼ አሉ፤ ሲቀጥል ያሰለጠኑኝ አሰልጣኞችና የቡድናችን ኮቺንግ ስታፎች እንዲሁም አብረውኝ የሚጫወቱ ተጨዋቾች ድርሻቸው ከፍተኛ ነውና ሁሉንም ነው ማመስገን የምፈልገው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P