Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“እነሱ ይፍሩን እንጂ እኛ አንፈራቸውም”
አብዱልከሪም መሐመድ /ቅ/ጊዮርጊስ/
“ከቅ/ጊዮርጊስ የምንፈራው አንዳች ነገር የለም”
በረከት ደስታ /ፋሲል ከነማ/

ቅ/ጊዮርጊስ VS ፋሲል ከነማ

በኢትዮጵያ ሊግ ካምፓኒ አዘጋጅነት የሚካሄደው የ2013ቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ /ቤት ኪንግ/ ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ ከ9 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታድየም በይፋ ይጀመራል፤ የአዲስ አበባ ስታድየም የመጀመሪያዎቹን አራት ሳምንታት የሊግ ውድድሮች እንዲያስተናግድ የተመረጠ ሲሆን በቀጣይ አራት ሳምንታት የሚከናወኑትን የሊግ ጨዋታዎች ደግሞ የባህር ዳር ስታድየም እና በመጨረሻም እስከ አንደኛው ዙር ፍፃሜ ያሉትን ግጥሚያዎች የጅማ ስታድየም የሚያስተናግዱት ይሆናል፡፡
የ24ኛ ዓመቱን የያዘው፣ በወቅታዊው የአገራችን ችግር ምክንያት ሶስቱን የትግራይ ክለቦች መቐለ 70 እንደርታን፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲን እና ስዑል ሽረን የማያሳትፈው እንደዚሁም ደግሞ በ13ቱ የፕሪምየር ሊጉ ተወዳዳሪ ክለቦች መካከል የሚከናወነው ይኸው የቤት ኪንግ ሻምፒዮና ውድደር ዛሬ ሲጀመር ተጋጣሚ ሆነው የሚቀርቡት ክለቦች የፕሪምየር ሊጉ የ14 ጊዜ ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ከተቀላቀለበት አጭር ጊዜው አኳያ ለአንድ ጊዜ ብቻ ያህል የጥሎ ማለፍን እና የአሸናፊዎች አሸናፊን ዋንጫ ያገኘው ፋሲል ከነማ ሲሆኑ በሁለቱ ቡድኖች መካከል የሚካሄደው ይኸው ጨዋታ ከፍተኛ ግምትም ተሰጥቶታል፡፡
ዛሬ በይፋ የሚጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ውድድር ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ጨዋታዎቹ ያለ ተመልካች የሚከናወኑ ሲሆኑ ዲ.ኤስ ቲቪ ግን የዘንድሮውን ውድድር በቀጥታ ስርጭት ለማስተላለፍ የጨረታው አሸናፊ በመሆኑ ለስፖርት ቤተሰቡ ጥሩ አማራጭ ሆኖለት ግጥሚያዎቹን እንዲከታተል ያደርገዋልና በእዚህ በኩል ዲ.ኤስ.ቲቪ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ዛሬ ሲጀመር ቅዱስ ጊዮርጊሶችና ፋሲል ከነማዎች ግጥሚያውን አሸንፈው ለመውጣት ሁለቱም ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጋቸውን እየተናገሩ ሲሆን በተለይ ደግሞ ከእንደዚህ ካሉ ጠንካራ ቡድኖች ጋር በሚካሄድ ጨዋታ ላይ ጣፋጯን ሶስት ነጥብ መውሰድ መቻል ጠቀሜታው ከፍ ያለ እንደሆነም አስተያየታቸውን ጨምረው ተናግረዋል፡፡
የቅ/ጊዮርጊስ እና የፋሲል ከነማ ክለቦች በዛሬው ዕለት ስለሚያደርጉት ተጠባቂው የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታ አስመልክተን ከሁለቱም ቡድን ተጨዋቾች ያናገርን ሲሆን ከቅዱስ ጊዮርጊስ አብዱልከሪም መሐመድን ከፋሲል ከነማ ደግሞ በረከት ደስታ ስለ ጨዋታውና ስለ ቡድኖቻቸው አስተያየታቸውን ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ ሰጥተዋል፤ ተከታተሏቸው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዛሬው ዕለት ይጀመራል፤ ለውድድሩ በምን መልክ ተዘጋጅታችኋል?
አብዱልከሪም፡- የዘንድሮው የውድድር ዘመንን በውጤታማነት ለማጠናቀቅ ቡድናችን መቀመጫውን በቢሾፍቱ በማድረግ ሲሰራ የነበረው የዝግጅት ጊዜ በጣም አሪፍ እና ከጠበቅነው በላይም ነው፤ አብዛኛው የዝግጅት ጊዜ ልምምዳችን ያተኮረው ወደፊት አጥቅቶ በመጫወት ግጥሚያዎችን እንዴት ማሸነፍ እንዳለብን ነው፤ ከዛም ውጪ እያንዳንዱ ተጨዋችም ራሱን በምን መልኩ ብቁ አድርጎ ለውድድሩ መቅረብ እንደሚገባውም ያስመለከተን የዝግጅት ጊዜ ልምምድንም ሰርተናልና ያን ልንወደውም ችለናል፡፡
በረከት፡- የእስካሁኑ ዝግጅታችን በጣም ጥሩ ነው፤ በአካል እና በአህምሮም በኩል ነው በጣም ስንዘጋጅ የነበርነው፤ ከዛ ውጪም ደግሞ ለውድድር ዓመቱ በበቂ ሁኔታ እንድንቀርብ የራሳችንን አቋም በሰራናቸው ልምምዶችም ሆነ ከቱኒዚያው ክለብ ጋር በነበረን ሁለት የኢንተርናሽናል ጨዋታዎቻችን ላይ የለካንበት አጋጣሚም ስላለ ያ ለእኛ በቂ የሚባል ነው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታን በዛሬው ዕለት ቡድናችሁ ማድረጉን አስመልክተህ ምን ትላለህ?
አብዱልከሪም፡- የዛሬን ጨዋታ የምናደርገው የሊጉ ጠንካራ ክለብ ከሆነው ፋሲል ከነማ ጋር ነው፤ ከእዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ጊዜ ተጫውተን እልህ አስጨራሽ ፍልሚያን ለስፖርት አፍቃሪው እና ለደጋፊዎቻችንም ልናስመለክት ችለናል፤ ያም ስለሆነ ዛሬ በሚኖረን የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ጥሩ እንቅስቃሴን ለደጋፊዎቻችን በማሳየትና ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ላለፉት በርካታ ወራቶች በኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ ከስፖርቱ አካባቢ ርቀው የነበሩትንና ቡድናቸውም ናፍቋቸው የነበሩትን ደጋፊዎቻችንንም እንዲነቃቁ በማድረግ እንዲደሰቱ እናደርጋለን፡፡
በረከት፡- የፕሪምየር ሊጉን የመጀመሪያ እና የመክፈቻ ጨዋታን ጠንካራ ክለብ ከሆነው ቅ/ጊዮርጊስ ጋር በዛሬው ዕለት ለማድረግ መዘጋጀታችን ለእኛ ጥሩ ነው የሚሆንልን፤ ምክንያቱም ይሄ ጨዋታ እኛን ለቀጣዮቹ ተከታታይ ፍልሚያዎቻችን በሚገባ የሚያዘጋጀንና የራሳችንንም ወቅታዊ አቋም በሚገባም እንድንፈትሽበት የሚያደርገን ስለሆነ፡፡
ሊግ፡- የዛሬውን ጨዋታ ማን በአሸናፊነት ይወጣል?
አብዱልከሪም፡- ከዓላ እርዳታ ጋር የድል ውጤቱን ቡድናችን ቅ/ጊዮርጊስ ይጎናፀፋል ብዬ ነው በእርግጠኝነት የምናገረው፤ ምክንያቱም ቡድናችን ባለፉት ተከታታይ ዓመታቶች ባልተለመደ ሁኔታ ከሻምፒዮናነት ርቋል፤ ይሄ ደግሞ ድል ለለመደ ቡድን ከባድም ነውና የዛሬው የጨዋታ አሸናፊ የምንሆነው እኛ ነን፡፡
በረከት፡- የጨዋታው አሸናፊማ ፋሲል ከነማ ነው፤ ለእዚህም እርግጠኛ ልሆን የቻልኩት ቡድናችን ውድድር ላይ ስለነበርም ነው፤ ያካሄድነው ውድድሩ ደግሞ ጠንካራ ፉክክክርን ያደረግንበት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ግጥሚያም ስለሆነ ያ ጨዋታ በሚገባ ራሳችንን ያዘጋጀንና ካለን ጥሩ ብቃት አኳያም የዛሬውን ጨዋታ እንድናሸንፍም የሚያደርገን ነውና፡፡
ሊግ፡- ከዛሬ ተጋጣሚያችሁ አንፃር የእዚህ ዓመት የቡድናችሁ የተጨዋቾች ስብስብ ምንድን ነው የሚመስለው?
አብዱልከሪም፡- ቅ/ጊዮርጊስ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ሁሌም ቢሆን ምርጥ የተጨዋቾች ስብስብን በመያዙ በኩል የምታማው ቡድን አይደለም፤ ዘንድሮም ነባር በሆኑትም ሆነ በአዲስ መልክ ቡድኑን በተቀላቀሉት ተጨዋቾቹም የሚኮራ ክለብ ነው፤ በእዚህ ዓመት ወደ ቡድኑ የመጡት ተጨዋቾች የቡድናችን ክፍተቶች ሙሉ ለሙሉ የሚደፍኑልንም ናቸውና በአጠቃላይ በያዝናቸው የተጨዋቾች ስብስብ ከዛሬ ተጋጣሚያችን ፋሲል ከነማ በተሻለ መልኩም ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾችን በስኳዳችን ያቀፍንበትም ሁኔታም ነው ያለው፤ ስለዚህም ይሄ ምርጥ ስብስብ የእዚህ ዓመት ላይ ተመልካቹንና ደጋፊዎቹን የሚያስደስት እግር ኳስን ይጫወታል ብዬም ነው ተስፋን የማደርገው፡፡
በረከት፡- የፋሲል ከነማ የተጨዋቾች ስብስብ እንደተጋጣሚያችን ሁሉ በጣም ጥሩ እና ጠንካራም ነው፤ ከዛ ውጪም ባለፈው ዓመት ላይ ተካሂዶ በነበረው የሊግ ውድድር ላይም በስኳዱ ይዟቸው ከነበሩትና በየጨዋታውም ጥሩ ብቃትን ካሳዩት ተጨዋቾች በተጨማሪ በየቡድኑም ምርጥ የነበሩትን ልጆችም ወደ ክለቡ ያመጣበትም አጋጣሚ ስላለ ከተጋጣሚያችን አንፃር ያ ለየት እንዲል ያደርገዋል፡፡
ሊግ፡- በዛሬው ጨዋታ ከተጋጣሚያችሁ የምትፈሩት ነገር አለ?
አብዱልከሪም፡- ፋሲል ከነማን በምንፋለምበት የዛሬው የመክፈቻ ጨዋታ በሁለታችንም ቡድኖች መካከል ጠንካራ ፉክክር እንደሚደረግበት ብናምንም በሜዳ ላይ በሚደረገው ፍልሚያ እኛ እነሱን ፈፅሞ አንፈራቸውም፤ እንደውም እነሱ እኛን ነው ሊፈሩን የሚገባቸው፡፡
በረከት፡- የፕሪምየር ሊጉን የመክፈቻ ጨዋታ ዛሬ ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ስናደርግ ወደ ሜዳ የምንገባው ተጋጣሚያችንን እንደሌሎች ቡድኖች አስበን ነው፤ የኳስ ነገር ባይታወቅም ሶስት ነጥብን ይዘን ለመውጣትም ነው የተዘጋጀነውና በጨዋታው ላይ ከእነሱ የምንፈራው አንዳች ነገር የለም፡፡
ሊግ፡- ለእዚህ ዓመት የቤት ኪንግ ውድድር ራስህን በምን መልኩ አዘጋጅተከዋል?
አብዱልከሪም፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋች ስትሆን ቡድኑ ካለው ስምና ዝና አንፃር እንደዚሁም ደግሞ በበርካታ ደጋፊዎችም የሚደገፍም ስለሆነና ከዛ ውጪም በየዓመቱም የድል ውጤትንም ማምጣት የግድ የሚጠበቅበት በመሆኑ ክለቡን ከተቀላቀልክበት ጊዜ አንስቶ የስኬት ስራዎችን መስራት ስለሚኖርብህ ራስህን በሚገባ ነው የምታዘጋጀው፤ እኔም የእዚህ ዓመት ላይ በሚኖረን የውድድር ተሳትፎ ከቡድን አጋር ጓደኞቼ ጋር በመሆን ባለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታቶች ያጣነውን የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ማንሳትና ከእዚህ ቀደም ደግሞ አግኝቼው የነበረውን የፕሪምየር ሊግ ኮከብ ተጨዋችነትን ሽልማት ዳግም ማግኘትና ወደ ምርጥ አቋሜም መመለስን ስለምፈልግም ለእነዛ በበቂ ሁኔታ ራሴን እያዘጋጀሁት ነው የምገኘው፡፡
በረከት፡- ፋሲል ከነማ በሚያደርጋቸው የእዚህ ዓመት የሊግ ተሳትፎ ራሴን እያዘጋጀው የሚገኘው ካለፈው ዓመት የአዳማ ከነማ ክለብ ተጨዋችነቴ በተሻለ መልኩ ሊጉ ላይ ለመቅረብ ነው፤ ዓምና በነበረኝ የውድደር ተሳትፎ ጥሩ ግልጋሎትን ሰጥቻለው፤ አንድ ተጨዋች ደግሞ ከዓመት ወደ ዓመት ሲሸጋገር ራሱን በተለየ ብቃት ማቅረብ ይጠበቅበታልና እኔም ምርጥ አቋሜን እንደማሳይ እርግጠኛ ነኝ፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ /ቤት ኪንግ/ ሻምፒዮናን ዘንድሮ ማን ያነሳል?
አብዱልከሪም፡- ይሄን ሁሉም ቡድን ያውቋል፤ ለዋንጫው ከፍተኛ ግምት የሚሰጠንም ለእኛ ነውና ያለ ጥርጥር የእዚህ ዓመትን የሻምፒዮናነት ዋንጫ ቡድናችን ያሳካል፡፡
በረከት፡- የእኛ የውድድሩ ዋንኛው ዓላማችን ባለፉት ዓመታት ለጥቂት ያጣነውን የሊጉን ዋንጫ ማንሳት መቻል ነው፤ ስለዚህም ከፈጣሪ እርዳታ ጋር 99 በመቶ ይህን ድል ሊያጎናፅፉን የሚችሉ ተጨዋቾች ስላሉ ውጤቱ ይሳካልናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡
ሊግ፡-በመጨረሻ?
አብዱልከሪም፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ /ቤት ኪንግ/ የእዚህ ዓመት ውድድር በዲ.ኤስ.ቲቪ መተላለፉ ለአገራችን እግር ኳስም ሆነ ለእኛ ተጨዋቾች የሚያስገኘው ጥቅም ላቅ ያለ ነው፤ በሱፐር ስፖርት ጨዋታዎቹ መተላለፋቸው እግር ኳሳችንን በጣም ያሳድገዋል፤ ከዛ ውጪም እኛ ሀገር ላይ ጥሩ ታለንት ስላለ ተጨዋቾችቻንም ወደ ተለያዩ ሀገራት በመሄድ በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት እንዲጫወቱም ትልቅ እድልን ይፈጥራልና ይሄን በአግባቡ ነው ልንጠቀምበት የሚገባን፤ ሊጉ በዲ.ኤስ. ቲቪ ከመተላለፉ አንፃርም ክለቦች እንዲሁም ተጨዋቾችም ከእዚህ ቀደም ሜዳ ሲገቡ ከሚያሳዩት የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት አኳያም ታርመው መምጣትም የግድ ይገባቸዋልና የእዚህ ዓመት ውድድር በተሳካ መልኩ እንዲጠናቀቅም ቡድናችን ደግሞ የውድድሩ ሻምፒዮና እንዲሆንም በጣም ነው የምመኘው፡፡
በረከት፡- ዲ.ኤስ.ቲቪ የእኛን የፕሪምየር ሊግ ውድድር በሱፐር ስፖርት ሊያስተላልፍ መሆኑ ከፍተኛ ደስታ ነው የተሰማኝ፤ ያ ስለሆነም ከእዚህ በኋላ በሚኖረን እያንዳንዱ ጨዋታዎቻችን እኛ ተጨዋቾች ወገባችንን ጠበቅ አድርገን በመስራት ሁሌም የምናልመውን ወደ ውጪ ሀገር ተጉዞ በፕሮፌሽናል ተጨዋችነትን መጫወትን ልናሳከው ይገባል፡፡ ሌላ ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር ደግሞ ቡድናችንፋሲል ከነማ በዛሬው ዕለት ወደሚጀመረው የፕሪምየር ሊግ ውድድር ከማምራቱ በፊት በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ጨዋታው ላይ ከቱኒዚያው ቡድን ጋር ተጫውቶና ምርጥ ተሳትፎንም አድርጎ እድለኛ ስላልሆነ ብቻ በጥቂት ስህተት ከውድድሩ ውጪ የሆነበት ሁኔታ በጣም እንዳስቆጨኝ መናገር እፈልጋለው፤ ቡድናችን ምንም እንኳን በሜዳው ላይ በተቆጠረበት አንድ ግብ ከውድድሩ ቢሰናበትም ባሳየው ጨዋታ ግን ተደስቻለው፤ ከግጥሚያው ጥሩ ልምድን አግኝተናልና ይሄ ወደፊቱ ለሚያጋጥመን ሌላ የውድድር ተሳትፎአችንም ጥሩ ትምህርት ሰጥቶንም አልፏል፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P