Google search engine

“እንደ አሰልጣኝ ዋንጫ አለማንሳታችን ትንሽ ሊሰማኝ ቢችልም የዓምና ውጤታችን ከበቂም በላይ ነው” አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ /ሲዳማ ቡና/


በመሸሻ ወልዴ (ጂ.ቦይስ)


ሲዳማ ቡና ያሳለፍነውን ዓመት
የፕሪምየር ሊግ ተሳትፎውን ከመቐለ 70
እንደርታ በመቀጠል በሁለተኛነት ያጠናቀቀ
ሲሆን ይህን ውጤት አስመልክቶም ወጣቱ
የቡድኑ አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ “እንደ
አሰልጣኝ የሊጉን ዋንጫ አለማንሳታችን
ትንሽ ሊሰማኝ ቢችልም የዓምና ውጤታችን
ከበቂም በላይ ነው” ሲል አስተያቱን ለሊግ
ስፖርት ጋዜጣ ሰጥቷል፡፡
ሲዳማ ቡና በዓምናው የሊጉ ተሳትፎ
ይህን የሁለተኝነት ደረጃ ውጤት ለማግኘት
የቻለው በስኳዱ ከጥቂቶች በስተቀር
ብዙ ልምድ ያላቸውን ተጨዋቾች ሳይዝ
ሲሆን ያመጣው ውጤትም በክለቡ ታሪክ
የመጀመሪያውና ትልቅ ስኬት የተጎናፀፈበት
መሆኑም ታውቋል፤ የሲዳማ ቡና ውጤት
ለአሰልጣኙ ዘርዓይ ሙሉም ቢሆን ክለቡን
በዋና አሰልጣኝነት መስራት በጀመረበት
የመጀመሪያ ዓመት የተገኘ ስለሆነም
ለእሱ እጅግ ታሪካዊና አስደሳች ሊሆንለት
መቻሉንም ይናገራል፡፡
የሲዳማ ቡና ክለብ የዘንድሮውን የፕሪ
ሲዝን ልምምዱን በጀመረበት በአሁኑ ወቅት
እያደረጉት ስላለው ዝግጅት፣ በእዚህ ዓመት
በምን መልኩ እንደሚቀርቡና ምን ውጤት
እንደሚያመጡ? እንደዚሁም ሌሎችንም
ጥያቄዎች ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/
አቅርቦለታል፤ አሰልጣኙም ምላሽ ሰጥቷል፤
ተከታተሉት፡፡


ሊግ፡- የፕሪ ሲዝን ዝግጅታ
ችሁን ከጀመራችሁ ቆያችሁ
ልበል?
አሰልጣኝ ዘርዓይ፡- አዎን፤ከ25
ቀን በላይ ሆኖናል፤ አስቀድመን
እዚሁ መዘጋጀት የመረጥነውም
ለዝግጅትወደ ዱባይ ትሄዳላችሁ
ተብሎ ተነግሮን ስለነበር ነው፡፡
ሊግ፡- ሲዳማ ቡና በአምናው
የፕሪምየር ሊግ ቆይታው ሁለተኛ
ሆኖ አጠናቋል፤ እንደቡድኑና እንደ
አንተ አሰልጣኝነትህ ውጤቱ በቂ
የሚባል ነው?
አሰልጣኝ ዘርዓይ፡- አዎን፤
ከበቂም በላይ ነው፤ ይሄን ስል
ያለምክንያት አይደለም፤ የክለቡን
የአሰልጣኝነት ሙሉ ሃላፊነት
የተረከብኩት ለመጀመሪያ
ጊዜ ነው፤ ከዛ ውጪምከዚህ
ቀደምቡድኑን በኃላፊነት የመሩት
አሰልጣኞች በእዚህ ደረጃ ላይ
የተመዘገበን ውጤት ያላመጡ
ስለነበር በውድድሩ ትልቅ ስኬትን
ነው ያገኘሁት፤ እንደ ቡድን
ስትሄድ ደግሞ ሲዳማ ቡናበወጣቶች
ተገንብቶ ነው ይሄን ጣፋጭና
ታሪካዊ ውጤትንያመጣውና
ለሁለታችንም ጊዜው በጣም ጥሩ
ሆኖ ነው ያለፈው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ
ዋንጫን ለጥቂት ነው ያጣችሁት፤ በዚህ
አልተከፋህም?
አሰልጣኝ ዘርዓይ፡- እንደአሰልጣኝነት እዛ
ደረጃ ላይደርሰህና ለዋንጫውም ተፎካክረህ
ውጤቱን ሳታገኝ ስትቀር ትንሽ ሊሰማህ
ይችላል፤ ያም ሆኖ ግን አመቱን ሙሉ በሜዳ
ላይ ካሳየነው ጥሩ እንቅስቃሴና የቡድናችንም
ተጨዋቾች በአብዛኛው ወጣቶች ከመሆናቸው
አንፃር ለዋንጫው እስከ መፎካከር መድረስ
ትልቅ ነገር ነው፡፡
ሊግ፡- ሲዳማ ቡና ዋንጫውን ለጥቂት
ያጣው በምንድነው ብለህ ታስባለህ?
አሰልጣኝ ዘርዓይ፡- ሲዳማ ቡና የፕሪምየር
ሊጉን ዋንጫ እንዲያጣ አድርጎታል ብዬ
የማስበው የመጀመሪያው በጥቂት
ጨዋታዎች ላይ ከሜዳው ውጪ
መጣል የሌለበትን ነጥብ በመጣሉ
ነው፤ እነዚህን ነጥቦች ያጣሁም
ስኳዱ በወጣቶች ላይ የተገነባ
ስለሆነና ልጆቻችንም በስነ-ልቦና
ደረጃ የተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎችን
ጩኸትና አንዳንድ ነገሮችን ሊቋቋሙ
ስላልቻሉ ነው፤ ከዛ ውጪም የዳኝነት
ተፅዕኖም የተደረገብን ግጥሚያዎች
አሉና እነዚህ ተደማምረው ዋንጫውን
እንድናጣ ሆነናል፡፡
ሊግ፡- ሲዳማ ቡና ሀብታሙ
ገዛኸኝን፣ ፈቱዲን ጀማልንና ጫላ
ተሺታን የመሳሰሉትን ተጨዋቾች
በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር
መስኮት ቡድኑን በመልቀቃቸው
አጥቷል፤ ይሄ መከሰት መቻሉ
ከፍተኛ ጉዳት አለው?
አሰልጣኝ ዘርዓይ፡- በሚገባ
እንጂ፤ እነሱ እኮ የክለቡ ቁልፍ
ተጨዋቾች ናቸው፤ በእነሱና
ውል ባለባቸው በእነ አዲስ ግደይን
በመሳሰሉት ተጨዋቾች ነበር
ቡድናችንን የገነባነውና የሰራነው፤
ከዛ ውጪ ደግሞ ከላይ ስማቸውን
የጠቀስኳቸው ተጨዋቾቹ ሲለቁብን
በእነሱ ፋንታ ሌሎች ሊተኩልን
የሚችሉ ልጆችን ልናስፈርም
ብንችልም ፌዴሬሽኑ ባወጣው
አዲሱ የደመወዝ ክፍያ ልንስማማ ሳንችል
ቀርተን ተጨዋቾቹን ስለለቀቅን ቡድናችን ላይ
የምንፈልገውን ውጤት ለማምጣት ተፅህኖ
መፍጠሩ አይቀርም፡፡
ሊግ፡- ከመቐለ 70 እንደርታ፤ ከሲዳማ
ቡና እና ከፋሲል ከነማ ክለቦች በዓምናው
ውድድር ማን ምርጡ ቡድን ነበር?
አሰልጣኝ ዘርዓይ፡- ይሄን ለህዝቡ
እተወዋለሁ፤ ምክንያቱም በዓምናው
የውድድር ቆይታ የእኛ ክለብ ብቻ ነው
ብዙ ወጪ ሳያወጣና በዝቅተኛ የፊርማ
ክፍያ ቡድኑን በወጣት ተጨዋቾች ገንብቶ
በመወዳደርና ጥሩም በመጫወት ሊጉን
በሁለተኝነት ለማጠናቀቅ የቻለውና ለእዚህ
ፍርዱን ህዝቡ ይስጥ እላለሁ፡፡
ሊግ፡- ሲዳማ ቡና በእዚህ አመት በምን
መልኩ ይቀርባል? ምን ውጤትንስ ያመጣል?
አሰልጣኝ ዘርዓይ፡- የሲዳማ ቡና
እግር ኳስ ክለብ የክረምቱ የተጨዋቾች
ዝውውር መስኮት ሲከፈት ሊሰራ አስ
ቦ የነበረው ቡድን በጣም ጠንካራና
በሻምፒዮንነት ደረጃም አምና ያላሳካነውን
የድል ውጤት ዘንድሮ ሊያገኝ የሚችል
ቡድንን ለመገንባት ነበር፤ በእዚህ ሁኔታ
ላይ ሆነንም ክለቡን ሊጠቅሙ የሚችሉ
ተጨዋቾችን ስናስፈርምም ነበር፤ በኋላ
ላይ ግን ከተጨዋቾች የደመወዝ ክፍያ ጋር
በተያያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
ወርሃዊ ክፍያው ከ50 ሺህ ብር በላይ
እንዳይዘል የሚል ውሳኔን በማስተላለፉ
እኛ የያዝናቸውን ጥሩ ጥሩ ልጆች ለቀን
የአሁን ሰአት ላይ በ50 ሺብር ክፍያ ሌሎችን
ወጣት ተጨዋቾች በማስፈረም እንቅስቃሴ
ላይ እንገኛለን፤ ለእዚያም ጠንካራ ተፎካካሪ
ሊያደርገን የሚችል ቡድንንም እየገነባን
እንገኛለን፤ ሲዳማ ቡና ከዛ ውጪም
የቡድኑን ወሳኝ የሆኑ ልጆችን ማለትም
እንደ እነ ሃብታሙ ገዛኸኝ፤ፈቱዲን ጀማልና
ጫላ ተሺታን የመሳሰሉ ጥሩ ችሎታ
ያላቸውንም ተጨዋቾች የለቀቀበት ሁኔታም
አለና የዘንድሮውን የውድድር ዘመን በሊጉ
የምንጫወተው ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን
ብቻ ነው፡፡__

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P