Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ከኢትዮጵያ ቡና ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመግባቴ ተቃውሞ ቢቀርብብኝም ያንን እንደጥላቻ አላየውም” አብዱልከሪም መሐመድ (ቅ.ጊዮርጊስ)



በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/


የእግር ኳስ ተጨዋችነት ህይወቱን በክለብ ደረጃ ለደቡብ ፖሊስ፣ ለሲዳማ ቡና፣ ለሐዋሳ ከተማ እና ለኢትዮጵያ ቡና ቡድኖች ተጫውቶ ያሳለፈው፤ የአሁን ሰዓት ላይ ደግሞ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን በመጫወት ላይ የሚገኘው አብዱልከሪም መሀመድ /ተርምኔተር የሊጋችን ውድድር በኮቪድ 19 ምክንያት ከተቋረጠ በኋላ ያለውን ጊዜ በምን መልኩ እንደሚያሳልፍ ከዛም በተጨማሪ ደግሞ ስለ ኳስ ዘመኑም አንድ አንድ ነገሮችን አጠር ባለ መልኩ አንስተንለት ምላሾቹን ሰጥቶናል፤ የብሔራዊ ቡድናችንን መለያ ከዚህ ቀደም የለበሰው ይኸው ተጨዋች ለቀረቡለት ጥያቄዎች በምላሹ ምን ብሎ ይሆን ተከታተሉት፡፡


ሊግ፡- የፕሪምየር ሊጉ ውድድራችን በኮቪድ 19 ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ተሰርዟል፤ ኳሱ በመቆሙ የአንተ የአዋዋል ሁኔታ ምን ይመስላል?
አብዱልከሪም፡-ኮሮና ቫይረስ ለዓለም እና ለኢትዮጵያም ከፍተኛ ስጋት ሆኖ እየከበደ በመጣበት የአሁን ሰዓት ላይ ጊዜዬን እያሳለፍኩ ያለሁት ቤቴ ውስጥ በመዋል ነው፤ እቤቴ ስውልም የተለያዩ አይነት የስፖርት እንቅስቃሴዎችን በመስራትም ላይ ነው የምገኘው፡፡
ሊግ፡- በኮቪድ 19 ከእግር ኳሱ ከራቅህ ወደ ሶስት ወራት ልታስቆጥር ተቃርበሃልና ለእዚህን ያህል ጊዜ ያለኳስ! አይከብድም?
አብዱልከሪም፡- በጣም ይከብዳል፤ ይጨንቃልም ጭምር፤ ምክንያቱም ከእዚህ በፊት ለእዚህን ያህል ጊዜ ከኳስ የራቅኩበት ወቅት ፈፅሞ የለምም ነበርና ግን ምን ታደርገዋለህ ኮቪድ 19 ከባድና ክፉ ወረርሽኝ ስለሆነ ይህን ጊዜ ማሳለፍ የምንችለው ከኳስ ጨዋታው መራቅም ስንችል ነውና፡፡
ሊግ፡- ከአሁን በፊት ከኳሱ ለረጅም ጊዜ የራቅከው መች ነበር?
አብዱልከሪም፡- ለኢትዮጵያ ቡና በምጫወትበት ሰዓት 2009 ላይ ነው፤ ያኔም በእግሬ ቁርጭምጭምቴ ላይ ነው በአበበ ቢቂላ ስታድየም ልምምድን በምንሰራበት ሰዓት ተጎድቼ ነበርና ለአንድ ወር ከ10 ቀን ያህል የራቅኩት፡፡
ሊግ፡- የአሁን ሰዓት ላይ በቤት ውስጥ ሆነህ የስፖርት እንቅስቃሴዎችን ስትሰራ ኳስ መግፋትና ማንቀርቀብንም ጨምሮ ነው?
አብዱልከሪም፡- አዎን፤ በእርግጥ እንዲህ ያሉ ከኳስ ጋር የተያያዙ ስራዎችን ስትሰራ የግድ ግቢ ሊኖርህ ይገባል፤ ለአንድ አንዶች ይህን ማድረግ ሊቸግራቸውም ይችላል፤ ያም ሆኖ ግን እኔ የአሁን ሰዓት ላይ የምገኘው ወንዶገነት ካሉት ቤተሰቦቼ ጋር በመሆኑ እና ግቢም ስላለው ሁሉን ነገር አመቻችቼ ከኳስ ጋር የተያያዘ ስራን እየሰራው ይገኛል፡፡ ከዛም አልፎም ደግሞ አንድ አንዴም ከቤታችን ፊት ለፊት አንድ ትምህርት ቤት ስላለና ዝግ ስለሆነም እዛም ፈቅደውልኝ እየሰራው ነው፤ ከእዚህ በኋላም እዛም ነው የምለማመደውና በእዚህ አጋጣሚ እነሱንም ለማመስገን እፈልጋለውኝ፡፡
ሊግ፡- በአሁን ሰዓት ያለህ የአመጋገብ ሁኔታ ለየት ይላል?
አብዱልከሪም፡- ብዙም ልዩነት የለውም፤ አሁን የምመገበው ክለብ እያለው የምመገበውን ነው፡፡
ሊግ፡- ወንዶገነት በፍራፍሬ እና በጫት ምርቷ ተለይታ ትታወቃለች፤ ፍራፍሬንስ እየተጠቀምክ ነው?
አብዱልከሪም፡- ብዙም አይደለውም፡፡
ሊግ፡- በእዚህ ሰዓት ምን ናፍቆሃል?
አብዱልከሪም፡- ወደ ኳስ መመለሱና ከጓደኞቼም ጋር ልምምድን እየሰራንና ከሰራንም በኋላ የልምምድ ሜዳው ላይ እና ከዛ ውጪም የምንቀላለዳቸው እና ጊዜውን የምናሳልፈው ነገር፤ ከዛ ውጪም የአዲስ አበባ ስታድየም ላይም ክለባችን ሲጫወት የደጋፊዎቻችን የአደጋገፍ ድባብም በጣሙን ናፍቆኛል፡፡


ሊግ፡- በእግር ኳስ የህይወት ዘመንህ ለአንተ ምርጡ እና በጣም የምትወደው ተጨዋች ማን ነው?
አብዱልከሪም፡- ከባህር ማዶ ተጨዋቾች ውስጥ ብራዚላዊውን ዳንኤል አልቬስን ነው የማደንቀው በጣምም ነው የምወደው፤ ከዛ ቀጥሎ ደግሞ ፖርቹጋላዊውን ክርስቲያኖ ሮናልዶን፡፡
ሊግ፡- ከሀገር ውስጥ ተጨዋቾችስ የቅድሚያ ተመራጭ?
አብዱልከሪም፡- ሙሉጌታ ምህረት ነዋ! እሱ ልዩ ተጨዋች ነበር፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነትህ ዘመን ኢትዮጵያ ቡና እያለህም ሆነ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገብተህ ስትጫወት በደጋፊዎቹ ዘንድ ትወደድ ነበር፤ ከዛ በፊት በነበርክባቸው ክለቦችም ጭምር፤ ያም ሆኖ ግን ከኢትዮጵያ ቡና ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገብተህ ስትጫወት ተቃውሞን ታስተናግድ ነበር፤ እነዚህን ነገሮች በምን መልኩ ነው የምታያቸው?
አብዱልከሪም፡- በዓለም እግር ኳስ ጭምር ነው የእግር ኳስ ተጨዋች ሆነህ ከአንድ ክለብ ወደ ሌላ ክለብ ስትዘዋወር ቅዋሜን ማስተናገድ የሚያጋጥም ነገር ነው፤ ልትጠላም ትችላለህ፡፡ ያንን ቅዋሜና ጥላቻ ግን እኔ በኔጋቲቭ ደረጃ አላየሁም፡፡ ለምሳሌ እኔ ከቡና ወጥቼ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስገባ የቡና ደጋፊዎች በመቃወም ያሉኝ ነገር ነበር፡፡ የሚቃወሙኝ የጠሉኝ እንኳን ቢኖሩ ስለሚወዱኝ እና ከክለባቸው እንዳልሄድ ስለሚፈልጉ እንጂ በሌላ ነገር እንዳልሆነ ጠንቅቄ ነው የማውቀው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ኮከብ ተጨዋች ከዚህ ቀደም ተብለሃል፤ ያ ምርጥ የነበረው ተጨዋች አሁን ላይ ግን ያለው የኳስ ብቃት እንደቀድሞው አይደለም ይባላል፤ ይሄን ትቀበለዋለህ?
አብዱልከሪም፡- አዎን፤ ማለትም በ2010 ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ውስጥ የነበረው አብዱልከሪም አሁን ላይ ያንን ጥሩ የሚባልና በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አስገኝቶለት የነበረውን ችሎታውን እያሳየ ነው ብዬ ፈፅሞ አላስብም፤ ከበፊቱ አንፃርም ወቅታዊ አቋሜ ጥሩ አይደለምምና ስለዚህ ይሄንን አሚን ብዬ እቀበለዋለሁኝ፡፡
ሊግ፡- በእዛ ደረጃ ለመገኘትህ ምክንያቶቹ ምንድን ናቸው?
አብዱልከሪም፡- ብዙ ነገሮችን ለማንሳት ብችልም በዋናነት ግን ከአሰልጣኞች የአጨዋወት ታክቲክ ጋርና እንደ አሰልጣኞቹም አመለካከት ነው፡፡
ሊግ፡- ወደ ፕሪምየር ሊግ ከክልል መጥተው አዲስ አበባ ላይ የሚጫወቱ ተጨዋቾች እና ከአዲስ አበባም ወደ ክልል በመሄድ የሚጫወቱ ተጨዋቾች በችሎታቸው የት ሲጫወቱ ከፍተኛ ስምና ዝናን ያገኛሉ? ለምሳሌ አንተ የት ስትጫወት ነው ስመኛ ተጨዋች የሆንከው?
አብዱልከሪም፡- ወደ አዲስ አበባ መጥቼ በአዲስ አበባ ስታድየም ላይ ስጫወት ነዋ! በተለይ ደግሞ ለቅዱስ ጊዮርጊስና ለኢትዮጵያ ቡና ገብተህ ስትጫወት እና ብቃትህንም በፍጥነት ማሳየት ከቻልክ የሚኖርህ ስም፣ ዝናና እውቅና በየጊዜው ይጨምራል፡፡ እነዚህ ቡድኖች ውስጥ ገብተህ ባትሰለፍ ራሱ መታወቅክ አይቀርምና ሁለቱ ቡድኖች በእዚህ በኩል ለየት ይላሉ፤ እኔን በተመለከተ ሁለቱም ጋር ስጫወት ጥሩ ስምን ዝናንም ላተርፍ ችያለው፤ ስለዚህም ወደ አዲስ አበባ መጥቶ መጫወት ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለብዙዎቹም ተጨዋቾች ከፍተኛ እውቅና ማግኘት መቻልን ልትክደውም ሆነ ልትፍቀው የምትችለው ነገር አይደለም፡፡
ሊግ፡- ይሄ የሆነው ግን ለምን ይመስልሃል?
አብዱልከሪም፡- ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀድሞ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ደጋፊዎች ስላላቸው እና ማንኛውም ተጨዋች ደግሞ የሁለቱን ቡድኖች ተወዳጅነትንና ተፈቃሪነትን እያወቀ እና እየሰማም የሚያድግ በመሆኑ አንዱ ይሄ ነው፤ ለምሳሌ እኔ ወደ አዲስ አበባ ስመጣ መጀመሪያ የተጫወትኩት ለኢትዮጵያ ቡና ነው፤ እዛም ገብቼ ስጫወት የደጋፊው የድጋፍ ድባብ ያስገርማል፤ እነሱን ጨምሮ ብዙ የስፖርት አፍቃሪም ወደ ሜዳ ይገባል፤ ስለዚህም በሜዳ ላይ ጥሩ ነገርን ማድረግ ከቻልክ ትወደዳለህ፣ ትደነቃለህ፤ ስምህ ተጠርቶም ይዘመርልሃልም፤ ይሄን ሁኔታ ደግሞ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ቀጥዬ በገባሁበት ሰዓትም በተመሳሳይ ሁኔታ ተመልክቼዋለው እና የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች የእግር ኳስን የሚመለከቱበት ሁኔታ በጣም ደስም ስለሚል ነው ወደ አዲስ አበባ መጥቶ መጫወቱ ለየት ሊል የቻለው፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነትህ ዘመንህ የሚያስቆጭህ ነገር የለም?
አብዱልከሪም፡- እንዴት አይኖርም! ለምሳሌ በችሎታህ ጥሩ ስምና ዝናን አትርፈህ በዛው ብዙ መቀጠል ሳትችል እና በፊት በነበረህ አቋምህ ላይ ሳትገኝ ስትቀር ይሄ ያስቆጫል፤ እሱ ብቻም አይደለም ጥሩ በነበርክበት ሰዓትም አንድአንዴ ከመዘናጋት እና ከሌሎች ነገሮች ጋር በተያያዘም ሊሆን ይችላልና ጠንክሮ መስራትን አለማስለመድ መቻል የሚያስቆጭ ነገር ነው፤ ስለዚህም ሁሌም ጥሩ በሆንክበትም ባልሆንክበትም ሰዓት ጠንክሮ መስራት በጣም የተሻለ ነገር ነው፤ ከዛ ውጪም እንደእኔ እምነት ከሆነ በእግር ኳሱ ላይ ወደ ቡድንህ ከሚመጣው አሰልጣኝ የጨዋታ ታክቲክ ጋር አብረህ የማትሄድ ከሆነ ጥሩ ላትሆን ትችላለህ፤ ያኔ ቢያንስ ከሪም ጥሩ ነው ከተባለ ሌላው ተጨዋችም ጥሩ ነው ከተባለ የእሱን ጥሩነት እኔ እንዴት እና በምን መልኩ ነው ልጠቀም የምችለው ብሎ ያ አሰልጣኝ በራሱ አንተን ሊጠቀምብህ ካልቻለ በስተቀር ቢያንስ እሱ ከሚጫወተው ወይንም እሱ ከሚፈልገው ነገር ፍፁም ተቃራኒ ከሆንክ ወደሱ ለምምጣት ጊዜ ሊወስድብህ ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ተጨዋችነት ላይ በሚዲያ ብትተች ወይንም ደግሞ ተቃውሞ ቢቀርብብህ ስሜቶችህ እንዴት ነው የሚሆኑት?
አብዱልከሪም፡- ገንቢ ሆነው ካገኘዋቸው እነዚህን ነገሮች እንደ ግብዓት ነው የምጠቀምባቸውና ለምን ተተቸው ብዬ ፈፅሞ የማኮርፍም ሆነ የማለቅስ አይነት ተጨዋች አይደለውም፡፡
ሊግ፡- የአሁን ሠአት ላይ በቤት ውስጥ እንደምታሳልፍ ነግረኸኛልና ከስፖርት ውጪ ሌላስ ጊዜክን የምታሳልፍበት ነገር አለ?
አብዱልከሪም፡- አዎን፤ በተለይ ደግሞ የራሴ የሆኑትን የጨዋታ ፊልሞች እመለከታለሁ፤ በተለይ ደግሞ የቡናና የቅዱስ ጊዮርጊስን የተወሰነ ደግሞ የሲዳማ ቡና ጨዋታ ፊልሞቼንና ለብሄራዊ ቡድንም ስጫወት ከሲሸልስ ጋር ስንጫወት የነበረው አለኝና እነዛን አያቸዋለው፡፡ በዛውም የነበረኝን ጠንካራና ደካማ ጎንንም እመለከትበታለው፡፡


ሊግ፡- ለዳግመኛ ጊዜ የኢትዮጵያ ኮከብ ተጨዋች መባል አትፈልግም?
አብዱልከሪም፡- እፈልጋለው እንጂ፤ ፈጣሪያችን ሁሉንም ነገር አስተካክሎትና ኮሮናንም ከሀገራችን አጥፍቶልን ኳሱ ሲጀመር ያንን ስኬት ዳግመኛ ማግኘቴማ አንድ ቀን አይቀርም፡፡ ሊግ፡-ኮቪድ 19 ከገባ ጀምሮ የወንዶገነቱ ልጅ በማህበራዊ ተሳትፎ ላይ ያለው ሚና ምን ይመስላል?
አብዱልከሪም፡- በኮሮናው ወቅት ይህ ክፉ ወረርሽኝ ወደሀገራችን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እኔ በማህበራዊ ጉዳይ ላይ ያለኝ ተሳትፎ ወደተወለድኩበት ከተማ ወንዶገነት በመሄድ አቅሜ በሚችለው መልኩ የበጎ አድራጎት እርዳታን ለማድረግ ችያለሁ፤ መጀመሪያ እንደውም በብር ነበር እርዳታ ለማድረግ የፈለግኩት፤ እንደአጋጣሚ ሆኖ ግን ታናሽ ወንድሜና የአጎቴ ልጅ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ስናወራ እነሱ ከፈሳሽ ሳሙና ጋር በተያያዘ ሙያ ውስጥ ነበሩና እንዲህ እንዲህ ነገር ብታደርግ ሲሉኝ የፈሳሽ ሳሙና መስሪያ መሳሪያ ማሽኑን እና ሳኒታይዘር እንደዚሁም ደግሞ የእጅ መታጠቢያ ሮቶዎችም በየአካባቢው የሚቀመጡም እነሱን ጭምር ገዛውና ለወረዳው እና ለከተማው አስተዳደር በመስጠት ማህበራዊ ግዴታዬን ልወጣ ችያለው፡፡
ሊግ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ በእዚህን ወቅት ለተጨዋቾቹ የማያቋርጥ ደመወዝ ከሚከፍሉ ክለቦች መካከል አንዱ ነው፤ ምን ትላለህ?
አብዱልከሪም፡- ይሄ የእውነት ነው፤ ክለባችን ሳያቋርጥም ነው እየከፈለን የሚገኘው፤ በዚህ በኩል እንደሌሎች ብዙሀን ቡድኖች የተቸገርንበት ነገር የለም፤ ከዛ ውጪም ቢያንስ በሳምንት ሁለቴም ይደውሉልንናስላለንበትም ሁኔታ ይጠይቁናል ይሄን በማድረጋቸው ላመሰግናቸው እፈልጋለው፡፡
ሊግ፡- ስለቤተሰቦችህ አንድ ነገር በል እስኪ?
አብዱልከሪም፡- እነሱ ሁሌም ቢሆን ለእኔ ከፍተኛ ቦታ አላቸው፤ እዚህ ለመድረሴም ያበረከቱት አስተዋፅኦም አለና በጣምም እወዳቸዋለው፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ?
አብዱልከሪም፡-በኮቪድ 19 በአሁን ሰዓት አብዛኞቻችን በየቤታችን ነው ያለነው፤ በተለይም ደግሞ እግር ኳስ ተጨዋቾችና በስፖርቱ ውስጥ ያለነው አካላቶች በየቤታችን ሆነን ተገቢውን የስፖርት እንቅስቃሴ በመስራት ሰውነታችንን ልንጠብቀው እና ልናቆየው ይገባል፤ በተለይ ደግሞ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ይህን ወረርሽኝ ለመከላከል ከቤታችን ባንወጣ ይሻላል፤ ከወጣንም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እጃችንን በተደጋጋሚ ጊዜ በሳሙና በመታጠብ በአፍና በአፍንጫችንም ማስክ በማድረግ እንደዚሁም ደግሞ ሰው የተሰባሰበበት ቦታ ባለመሄድ ርቀታችንን ጠብቀን እንንቀሳቀስ ነው የምለው፡፡ ከዛ ውጪም ሌላውም የህብረተሰብ ክፍል እነዚህ መሰል መከላከያ ነገሮችን በተግባር ላይ በማዋል ይህን ጊዜ እንድናሳልፈውና ዓላህ ረድቶንም ወደመደበኛው ስራችን ሁላችንም በፍጥነት እንድንመለስም ምኞቴ ነው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P