Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ከደረሰብን እንግልት አንፃር ሌሴቶን ጥለን ወደቀጣዩ ዙር በማለፋችን በደስታ ብዛት አልቅሰናል” አስቻለው ታመነ

በመሸሻ ወልዴ G.BOYS


ዋልያዎቹ በኳታር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2020ው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የሌሴቶ አቻቸውን በማሴሩ የተፋለሙ ሲሆን በእዚህም የመልስ ጨዋታ 1ለ1 በመለያየት ወደተከታዩ የምድብ ድልድል ዙር ሊያልፉ ችለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ከሌሴቶ ጋር 1ለ1 በመለያየት ወደ ቀጣዩ የምድብ ድልድል ሊያልፉ የቻሉት የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ባህር ዳር ላይ አከናውነው 0ለ0 በመለያየት እና አሁን ደግሞ ከሜዳ ውጪ በነበራቸው ጨዋታ ላይ 1ለ1 ስለወጡ ነው ከሜዳ ውጪ ማን ግብ አስቆጠረህ በሚለው ህግ ሊያልፉ የቻሉት፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ሌሴቶን ካሸነፉ በኋላም በዕለቱ ስለነበረው የጨዋታ እንቅስቃሴ፣ ከዚህ ሲሄዱ ምን አይነት እንግልት እንደደረሰባቸው፣ ግጥሚያውን ካሸነፉ በኋላ ስለማልቀሳቸውና ሌሎችን ተያያዥ ጥያቄዎች ለቡድኑ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አስቻለው ታመነ ጥያቄን አቅርበንለት ምላሹን በሚከተለው መልኩ ሰጥቷል፡፡


ሊግ፡- በቅድሚያ እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰህ?
አስቻለው፡- እናንተንም እንኳን አደረሳችሁ፡፡
ሊግ፡- አዲሱን ዓመት አስመልክተህ እንኳን አደረሳችሁ ማለት የምትፈልገው ሰው ካለ?
አስቻለው፡- በቅድሚያ የእንኳን አደረሳችሁ መልህክቴን ማስተላለፍ የምፈልገው ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፤ በመቀጠል ደግሞ ለቤተሰቦቼና ለእግር ኳሱ አፍቃሪዎች ነው፤ አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅርና የብልፅግናም እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡
ሊግ፡- በሌሴቶ ላይ ከሜዳችሁ ውጪ ያስቆጠራችሁት ጎል ወደ ዓለም ዋንጫው የምድብ ድልድል አስገብቷችዋል፤ ማሴሩ ላይ በሁለታችሁ መካከል የነበረው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ምን መልክ ነበረው?
አስቻለው፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሌሴቶን በተፋለመበት የሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ከተጋጣሚው ተሽሎና ኳስ ይዞ በመጫወት እንቅስቃሴም በልጦ የታየበት ነበር፤ በሁለተኛው አጋማሽም እነሱ የአቻነቱን ጎል እስካስቆጠሩበት ጊዜ ድረስ እኛ ተሽለን የታየንበት ነበርና ወደ ተከታዩ ዙር ለማለፍ ያገኘነው ውጤት የሚገባን ነው፡፡
ሊግ፡- ሌሴቶን አሸንፋችሁ ከውድድር ካስወጣችሁ በኋላ በውስጥህ ምን አይነት ስሜት ነው የተፈጠረብህ?
አስቻለው፡- ከሌሴቶ ብሄራዊ ቡድን ጋር የነበረንን የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ከሜዳችን ውጪ ባስቆጠርናት የአቻነት ጎል በማሸነፍ ወደምድብ ድልድሉ በመግባታችን በጣም ደስ ብሎኛል፤ የእኔን ደስታ ልዩ ያደረገልኝም ለጨዋታው ወደእሷ ልናደርግ በነበረው ጉዞ ደቡብ አፍሪካ ላይ ትራንዚት ስናደርግ እንግልት ደርሶብን ስለነበርና ማሴሩ ከገባን በኋላም በመሰናዶ ደረጃ ለእኛ ጥሩ እንክብካቤ ሊደረግልን ባለመቻሉ ነውና በእዚህ መልኩ ኳሱን ተጫውተን ውጤታማ መሆን መቻላችን የእኛን የአዕምሮ ጥንካሬ ያሳየ ነው፡፡
ሊግ፡- ወደ ሌሴቶ ለጨዋታ ልትጓዙ ስትሉ ምን አይነት እንግልት ነበር የደረሰባችሁ?
አስቻለው፡- ሌሴቶ ልንጓዝ ስንል በመጀመሪያ ደ/አፍሪካ ነበር ትራንዚት ያደረግነው፤ ወደዛም በሄድንበት ሰዓት የዋልያዋቹ ስብስብ ባልተሟላበት እና በማይመችም መልኩ ነበርና የተጓዝነው መጉላላት ደርሶብናል፤ በእዛ ቆይታችንም ወደ ሌሴቶ ለመሄድ ሌሎቹን የቡድን አባላቶቻችንን የግድ መጠበቅ ስላለብንም እዛ ለሁለት ቀን ያህል ቆይተናልና የመጀመሪያው እንግልት ይሄ ነበር፤ በኋላ ላይ ግን በደ/አፍሪካ የሚገኙት የኢትዮጵያ አየር መንግድ ሰራተኞች አዲስ አበባ ከሚገኘው አየር መንገድ ይሁን ከፌዴሬሽኑ ጋር ብዙ አላወቅኩም ስላለንበት ሁኔታ በመነጋገር ወደምናርፍበት ሆቴል አስገቡን፤ ዋልያዎቹ ላይ ሌላው የደረሰው እንግልት ሌሴቶ ከገባን በኋላ ያለው ነው፤ እዛ ያረፍነው ደረጃውን ባልጠበቀ ሆቴል ነው፤ ሆቴሉም አይደለም ለብሄራዊ ቡድን ለአንድ ክለብ የማይመጥን ነበርና በእዚህ መልኩ ሆነን ነው ወሳኙን ጨዋታ ያደረግነው፡፡
ሊግ፡- ከዋልያዎቹ የተጨዋቾች ስብስብ ውስጥ አንድአንዶቻችሁ ሌሴቶን ካሸነፍን በኋላ ማልቀሳችሁ ታይቷል፤ ይሄ ከምን የመጣ ነው?


አስቻለው፡- የእውነት ነው ከጨዋታው በኋላ ያለቀስን ተጨዋቾች አለን፤ ይሄ እምባ የመጣውም ዝም ብሎ ያለምክንያት አይደለም፤ ዋልያዎቹ ለእዚህ ጨዋታ ወደ ሌሴቶ ሲጓዙ የደረሰባቸው እንግልት ነበርና ከጨዋታው በፊት ይሄን ብናወራ የምክንያት ወይንም ደግሞ የሰበብ ቡድን መሆንን ስላልፈለግን በከፍተኛ የሞራል ስሜት ላይ ሆነን በመጫወት ነው ግጥሚያውን ካሸነፍንና ወደቀጣዩም ዙር ካለፍን በኋላ የደረሰብንን እንግልት ወደኋላ በማሰብ ጭምር የቁጭት ስሜትም ስለነበረብን በደስታ ብዛት ልናልቅስ የቻልነው፡፡
ሊግ፡- ዋልያዎቹ በቻን፣ በአፍሪካ ዋንጫና በዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከአዲሱ ዓመት መባቻ ጀምሮ በርካታ ግጥሚያዎችን ያደርጋሉ፤ እንዴትና በምን መልኩ እንጠብቃችሁ?
አስቻለው፡- ብሄራዊ ቡድናችን በመጀመሪያ ደረጃ ከመጪው ዓመት አንስቶ በርካታ ጨዋታዎችን የሚያደርግ መሆኑ ለእኛ ጥሩ ነው፤ ብዙ ጨዋታዎችን ባደረግን ቁጥር መሻሻል ይኖራል፤ ያኔም ሁሉም ተጨዋችም ሆነ ቡድኑ ራሱ አቅሙን ያውቃል፤ ለስፖርተኛውም የተለያዩ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን ባደረገ ቁጥር የፕሮፌሽናል ተጨዋችነትንም እድል የሚያገኝበት አጋጣሚም ይኖረዋልና አዲሱ ዓመት ላይ የዋልያዎቹ ስብስብ ጥሩ የሚባል ውጤት ያመጣል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ሊግ፡- በኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው ጊዜ የነበረው የብሔራዊ ቡድን ስብስብ ከማጣሪያ ጨዋታው አንስቶ እስከዋናው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር እንደዚሁም ደግሞ በዓለም ዋንጫውም ከማጣሪያ አንስቶ እስከምድብ ድልድል ድረስ ብዙ ጨዋታዎችን ሊያደርግና ጥሩም ሊጓዝ ችሏል፤ የአሁኑ ቡድን ያን የመድገም አቅም አለው? በእዚህ ቡድን ላይስ እምነቱ አለህ?
አስቻለው፡- የሰውነት ቢሻው የያኔው ቡድን በጊዜው ብዙ ነገሮችንና ታሪኮችን ሰርቶ አልፏል፤ ታሪክ ደግሞ የሚቆም አይደለም፤ ያን ካልኩ የአሁኑ የእኛ የዋልያዎቹ የተጨዋቾች ስብስብ ሌላ ታሪክን ሰርቶ ማለፍን ስለሚፈልግ ስለ ቡድኑ ጥሩነት በሚገባ መናገር እፈልጋለው፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ…?
አስቻለው፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሀገሪቱን እግር ኳስ በብቃት ለመምራትና ለማሳደግ የመጪው ዓመት ላይ ካለፉት በርካታ ስህተቶቻቸው ብዙ ነገሮችን ሊማሩ ይገባል፤ ስለዚህም ለኳሱ እድገት ሲሉ መስራት ባለባቸው ነገሮች ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው በመስራት ኳሱ የሚሻሻልበትን ነገር ቢፈጥሩ ጥሩ ነው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P