Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

ካርሎስ ዳምጠው “በፈለግኩት ስፍራ መጫወት እችላለው፤ ወደ አንድ ቡድን ማምራቴም የማይቀር ነው“

 

ወደ ኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ከተቀላቀለው የመከላከያ ክለብ ጋር የውል ዘመኑ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተለያየው ካርሎስ ዳምጠው እስካሁን ወደየትኛውም ቡድን ባያመራም በእዚህ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ቀነ ገደቡ ከመዘጋቱ በፊት ወደ አንድ የሊጉ ክለብ በማምራት መጫወቱ እንደማይቀር ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

ወደ እግር ኳስ ዓለሙ ከመጣ በኋላ በክለብ ደረጃ ለአርሲ ነገሌ፣ ለመከላከያ ለመቐለ 70 እንደርታና ለወልዋሎ አዲግራት እግር ኳስ ክለቦች ለመጫወት የቻለው ካርሎስ ዳምጠው በመከላከያ ቡድን ቆይታው ክለቡን ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያልፍ ካስቻሉት ተጨዋቾች መካከል አንዱ ሆኖ ቢገኝም የአሰልጣኝ ዩሃንስ ሳህሌ እቅድ አካል ስላልሆነና ውሉንም ስለጨረሰ ከክለቡ ጋር ሊለያይ ችሏል፤ በዚህ ጉዳይ ዙሪያና መከላከያም ወደ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ለማለፍ ስለቻለበት ሁኔታም ተጨዋቹን ጥያቄን አቅርበንለት ሲመለስ “መከላከያ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያለፈው ለእዛ የሚሆን ቡድንን አሰልጣኝ ዩሃንስ  ሳህሌ አስቀድሞ ሊገነባ በመቻሉ ነው፤ ይህ ቡድን በጥሩ ሁኔታ ከተሰራ በኋላም አጠቃላይ ተጨዋቾቹ ወደ ሜዳ በወኔ በመግባትና ላባችንንም ጠብ አድርገን በማፍሰስ ይሄን ክለብ ከአሰልጣኙ የታክቲክ ስራ ጋር አጣምረን ለድል አብቅተነዋልና በዚህ በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ ያም ሆኖ ግን በዚህ ቡድን ውስጥ በነበረኝ ቆይታዬ ዘንድሮ ጥሩ የውድድር ዓመትን ለማሳለፍ ብችልም ከክለቡ ጋር የውል ዘመኔን በማራዘም እቀጥላለው ብዬ ብጠብቅም ይህ ባለመሆኑ አዝኛለው፤ በመከላከያ ቡድን በነበርኩበት ሰዓት ከዚህ ቀደም ከምጫወትበት የአጥቂ ሚና ባሻገር በተከላካይነትም ተጫውቻለው፤ በሁለገብ ሚና ተጨዋችነት መጫወት የሚያስችለኝ አቅምም አለኝ፤ ከእዚህ ቡድን ጋር አሁን ልቀጥል ባልችልም በእዚህ የዝውውር ወቅት ወደ አንዱ ቡድን በማምራት በመጪው የውድድር ዘመን የራሴን ማንነት ማሳየት እፈልጋለው” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

በመከላከያ እንደዚሁም ደግሞ በወልዋሎ አዲግራትና በመቐለ ክለቦች የተጨዋችነት ዘመን ቆይታው የአሰልጣኝ ዩሃንስ ሳህሌ ተፈላጊ ተጨዋች የነበረው ካርሎስ ዳምጠው ከመከላከያ ቡድን መለያየቱ በኋላ በተለያዩ ሰፈሮች በሚካሄድ የክረምት ውድድሮች ላይ ራሱን በማዘጋጀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በእዚህ የውድድር ተሳትፎ ላይም ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ተወዳጅነትን እያተረፈም ይገኛል፤ ተጨዋቹ ስለ እነዚህ ውድድሮችና በኳሱ ራሱንም ስለሚያስቀምጥበት ሁኔታም ጠይቀነው በሰጠን ምላሽ “በእዚህ የክረምቱ ወራት ራሴን ለመጪው የውድድር ዘመን በብቃት ለማቅረብ በመፈለግ አብነት በሚገኘው የዓለሙ ሜዳ ላይ በተደረገው የእኛ አዲስ ከቴ ክለብን እናጠናክር ውድድር ላይ ለመሳተፍ በመቻሌ በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ ሻምፒዮና ከመሆናችን ባሻገር የውድድሩ ኮከብ ተጨዋችና ኮከብ ግብ አግቢም በመባል ከፍተኛ ተወዳጅነትንም በማትረፌ ውድድሩን ለአዘጋጁት አካላቶችና ለሁሉም አድናቆት ለሰጡኝ አካላቶች ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው፤ በህይወት ዘመኔ እንዲህ ያለ ክብርንና ተወዳጅነትን አግኝቼ አላውቅም፤ ተመልካቹ ጭቃ በጭቃ ሆኜ ራሱ እየመጡ ያቅፉኝ ነበር፤ አዲስ ከቴዎች ለኳስ ያላችሁ ፍቅር ይገርማል፤ ይሄ ስራችሁም ለሁሉም ተጨዋችም ራሱን በሚገባ እንዲያዘጋጅበትም ያደርጋልና በድጋሚ ከፍተኛ ምስጋናዬን ነው የማቀርብላችሁ፤ ከዛ ውጪም እኔን በተመለከተም በመጪው ዓመት በሚኖረኝ የውድድር ተሳትፎ በሁለገብ ሚና መጫወት የሚያስችል አቅሙ አለኝና አሰልጣኞች ወስደው ሊጠቀሙብኝ ይገባል በማለት አስተያየቱን አጠቃሏል፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P