Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ክለባችን ዋንጫ ማንሳት እንዴት እንደሆነ ስለሚያውቅበት ሻምፕዮና እንሆናለን” አስቻለው ታመነ /ቅዱስ ጊዮርጊስ/

በመሸሻ ወልዴ

የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብን በተከላካይ ስፍራው ላይ በማገልገል የሚታወቀው ጠንካራው ተጨዋች አስቻለው ታመነ ሰሞኑን ከአዳማ ከነማ ጋር በነበረው የህዳሴው ግድብ ጨዋታ ላይ ጉዳትን አስተናግዶ የነበረ ሲሆን ወደ ሜዳ የሚመለስበት ቀን ለማወቅ የኤም አር አይ ምርመራን ማድረጉንና የክለባቸው ሀኪምን ውሳኔ እንደሚጠብቅም ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተከላካይ አስቻለው ከደረሰበት ጉዳት አንፃር ወደ ሜዳ የሚመለስበት ጊዜም ሩቅ እንደማይሆንም ተስፋን የሰነቀ ሲሆን በሚመለስበትም ወቅት በሁለተኛው ዙር የክለባቸው የሊጉ ተሳትፎ ለክለቡ ውጤት ማማር የሚቻለውን ሁሉ ጥረት አድርጎ ቡድኑን ሻምፒዮና ለማድረግም እንደሚጫወት ሀሳቡን አክሎ አሳውቋል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ተጨዋች አስቻለው ታመነ ለቡድኑ ከመጫወት ባሻገር የአንደኛ ዙር ጨዋታቸውን እንዳጠናቀቁ ወደ ትውልድ ሀገሩ ዲላም በመሄድ ለታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት የትጥቅ ድጋፍ ያደረገበት እና ተጨዋቾቹም የሚጫወቱበትን ሜዳ በማመቻቸት የሰራው በጎ ስራ በብዙዎች ዘንድ አድናቆት ያተረፈበት እና ምስጋናንም ያገኘበት ሲሆን ለሌሎች የእግር ኳስ ተጨዋቾችም እንዲህ ያለ ስራን እንዲሰሩ በምሳሌነት እየተጠቀሰም ይገኛል፡፡
ከቅዱስ ጊዮርጊሱ ተጨዋች ጋር በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ አውርተን ምላሹን ሰጥቷል፤ ተከታተሉት፡፡
ሊግ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከነማ ጋር ባደረገው የህዳሴው ግድብ ጨዋታ በግራ እግር ላይ ጉዳትን አስተናግደሃል፤ ጉዳቱ እንዴት ደረሰብህ.. በአሁን ሰዓት ያለህበት የጤንነት ሁኔታስ ምን ይመስላል?
አስቻለው፡- በአሁን ሰዓት ላይ የምገኝበት የጤንነት ሁኔታ የህመም ስሜት ስላለብኝ ገና አልተሻለኝም፤ የተጎዳሁትም ኳስ እየገፋሁ በምሄድበት ሰአት ላይ እግሬን ወለም ብሎኝ በመውደቄ ነው፡፡
ሊግ፡- ለቅዱስ ጊዮርጊስ ከደረሰብህ ጉዳት መች አገግመህ ወደ ሜዳ ትመለሳለህ?
አስቻለው፡- ወደሜዳ የምመለስበት ቀናት ገና አልታወቀወም፤ የኤም አር አይ ምራመርዬን ያደረግኩበት ረቡዕ እለት ስለሆነ ውጤቱን በቀናት ጊዜ ውስጥ እየጠበቅኩኝ ነው የምገኘው፡፡ /ያነጋገርነው ሐሙስ ዕለት ነው/፡፡
ሊግ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን የአንደኛው ዙር ውድድር እንዳጠናቀቀ ለእረፍት ወደ ትውልድ ሀገርህ ዲላ አምርተህ ነበር፤ ከዛ ባሻገርም እዛ ስትጓዝ በዲላ ለሚገኙ የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት የትጥቅ ስጦታ ማበርከትክንም ሰማን ይህን ለማድረግ ያነሳሳክ ዋናው ነገር ምንድን ነው?
አስቻለው፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ውድድር በተጠናቀቀበት እና በእረፍቱም ወቅት ቤተሰቦቼን ለመጠየቅ ወደ ትውልድ ሃገሬ ባመራሁበት ሰአት ለታዳጊ ወጣቶቹ የትጥቅ እርዳታን ለማድረግ ከድምዳሜ የደረስኩበትም ሆነ የሚጫወቱበትንም ሜዳ በማመቻቸት በኩል ከእኔ የሚጠበቅብኝን ነገር ለማድረግ ያነሳሳኝ ዋናው ነገር ዲላ እኔን ለዛሬ ደረጃ ከህፃንነት እድሜዬ አንስቶ በማሳደግ ዛሬ ለደረስኩበት ደረጃ ለጥሩ ተጨዋችነት እንድበቃ ያደረገችኝ ስለሆነ በምችለው አቅም ውለታዋን መመለስ አለብኝ በሚል ስሜት ተነሳስቼ ነው፤ ከዚህ በፊትም ለዲላ ከነማ ዋናው ቡድንም እንዲህ ያለ የትጥቅ ድጋፍም አድርጌም ነበር፡፡
ሊግ፡- ወደ ዲላ በማምራት ይህን በጎ አላማ ስታደርግ ምንድን ነው የተሰማህ…
አስቻለው፡- በእውነቱ በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ የትጥቅ እርዳታውን ለማድረግ ያሰብኩበት ዋና ዓላማም ዲላ እኔን ስላፈራችኝ ብቻ ሳይሆን በአካባቢው የሚገኙ የታዳጊ ወጣቶች ጥሩ የኳስ ብቃት ስላላቸው በእነሱ ላይ ከፍተኛ እምነት ስላለኝ እና ወደፊትም እኛን ተክተው ለሀገር ትልቅ ግልጋሎት ይሰጣሉ የሚል እምነት ስላለኝም በስፍራው የእኛን መገኘት ሲያዩ በራሱ ምንም ነገር እንኳን ባናደርግላቸው እንኳን የመነሳሳት ነገር ስለሚኖራቸውም ነው ወደ ዛ ተጉዤ የጎበኘዋቸው፤ ዲላ ብዙ ተጨዋቾችን ማስገኘት ትችላለች፤ የአሁን ሰዓት ላይ የሊጉ ክለቦች ወደ ተስፋ ቡድኖቻቸው ገብተው የሚጫወቱበትን እድል ቢያመቻቹላቸውም በጣም ነው ደስ የሚለኝ፡፡
ሊግ፡- ዲላ በተጓዝክበት እና ፕሮጀክቱን በጎበኘክበት ጊዜ የእግር ኳሱ ላይ መነቃቃት እንዲኖር አንድ አንድ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ረገድ የረዱክ አካላቶች አሉ..
አስቻለው፡- አዎን፤ ለምሳሌ ሜዳንና አንድ አንድ ሁኔታዎችን በተመለከተ የደምቦስቆ ትምህርት ቤት ዳይሪክተር አባ ተክሌ አሉ፤ ከእሳቸው ጋር ለወደፊቱም ምን ማድረግ እንደሚኖርብን ብዙ ነገር ተነጋግረናል፤ ሌሎቹም አሉና የጋራ እገዛው ካለ ጥሩ ነገር በእግር ኳሱ ላይ መስራት ይቻላል፡፡
ሊግ፡- እንደ እግር ኳስ ተጨዋችነትህ በእግር ኳሱ አካባቢ እንዲህ ያሉ ነገሮች ላይ ስለመስራት ማስተላለፍ የምትፈልገው መልህክት አለህ..
አስቻለው፡- አዎን፤ እኛ ሁላችንም የእግር ኳስ ተጨዋቾች ለእዚህ ደረጃ እንድንበቃ ያደረገንን አካባቢያችንን እና የኋላ ታሪካችንንም ባለመርሳት ወደፊት ለሚመጡ የታዳጊ ወጣት ተጨዋቾች አርኃያ መሆን ይገባናልና በዚህ በኩል እነሱን ብናግዝ ጥሩ ነው፤ በእኛ እገዛ ዛሬ አንድ ተጨዋች በተነሳሽነት ወጣ ማለት ነገ በርካታ ተጨዋቾች እንዲወጡ በሩን ስለምንከፍትላቸው በዚህ በኩል የአቅማችንን ሁላችንም ለየ አካባቢያችን ብናደርግ ጥሩ ነው እላለው፡፡
ሊግ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን የአንደኛው ዙር በሶስተኛነት አጠናቅቋል፤ ውድድሩ በእናንተ በኩል እንዴት አለፈ? በሁለተኛው ዙርስ በምን መልኩ ትቀርባላችሁ…
አስቻለው፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ የአንደኛው ዙር የውድድር ተሳትፎውን ማሸነፍም መሸነፍም አቻ መውጣትም ቢያጋጥመውም በአጠቃላይ በነበረው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ወጥ የሆነ አቋሙን ሳያሳይ ያጠናቀቀበት ነው፤ ከዛ ውጪም በመሪው ክለብ መቐሌ 70 እንደርታና በተከታዩ ሲዳማ ቡናም በ9 ነጥብ እና በ4 ነጥብ ተበልጦ ተከታዩን ስፍራ የያዘበትም የውድድር ዘመን ተሳትፎው ስለሆነ ይሄ ውጤት ክለቡን ይመጥነዋል የምለው አይደለም፤ ያም ሆኖ ግን ክለባችን በእንደዚህ አይነት የነጥብ ልዩነት አይደለም ከዚህም በባሳ የነጥብ ልዩነት ከዚህ ቀደም ተበልጦ የሁለተኛው ዙር ውድድሩን ብቻ ሳይሆን የሊጉንም ውድድር ያሸነፈበት አጋጣሚ አለና ይህ የመጀመሪያው ችግር እንደሚቀረፍ እናምናለን፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ የሁለተኛው ዙር ላይ እንዴት የሊጉን ዋንጫ ማንሳት እንደሚችል ልምድም ስላለው ያውቀዋልና የውድድሩ ሻምፒዮና የምንሆነው እኛ ነን፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድሩ ክስተት የምትለው ቡድን ማን ነው?
አስቻለው፡- የሊጉ ክስተት ማንም በእዚህ የመሪነት ደረጃ ላይ ይገኛል ብሎ ስላልጠበቀው መቐሌ 70 እንደርታ ነው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙርን እንዴት አገኘኸው?
አስቻለው፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮው ውድድር ጥሩ ፉክክር የታየበት ነው፤ በስፖርታዊ ጨዋነቱም ከሌላ ጊዜ አንፃር ከፍተኛ ለውጥንም አይተንበታልና ይሄ አስደሳች እና ሁሌም ሊቀጥል የሚገባው ነው፡፡
ሊግ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን ዋንጫ አምና አጥቷል፤ ዘንድሮም በመሪዎቹ ላይ ከሚገኘው የመቐሌ 70 እንደርታ ክለብ ከወዲሁ በ9 ነጥብ ተበልጧልና ይሄ እናንተን ያሰጋችኋል?
አስቻለው፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊግ ዋንጫን ሳያገኝ በቀረበት በአመቱ ዋንጫ አጥቶ አያውቅም፤ ይሄን ሁሉም ሰው ያውቋል፤ እኛም ተጨዋቾች የምንረዳው ጉዳይ ነውና በዘንድሮው የውድድር ዘመን ላይም ቡድናችን ምንም እንኳን አሁን ላይ በመሪው ክለብ በ9 ነጥብ ይበለጥ እንጂ የሊጉን ዋንጫ አያገኝም የሚል የስጋት ስሜት ፈፅሞ የለብንም፤ የሁለተኛው ዙር ላይ ክለባችንን ታየዋለክ ምክንያቱም ቅዱስ ጊዮርጊስ መጫወት የሚፈልገው ፕሪምየር ሊግ ብቻ አይደለም የቻምፒዮንስ ሊግ ላይ መሳተፍ ይፈልጋል፤ አመራሮችም እኛ ተጨዋቾችም ይህንን ነው የምንፈልገው እና ይሄ የሁለተኛው ዙር ምንም አማራጭ የሌለው ጥያቄ ስለሆነና ለምንም ነገርም ወደኋላ የምንለው ነገር ስለሌለን የፈጣሪ እገዛ ተጨምሮበት ዋንጫውን እናነሳለን፡፡
ሊግ፡- ጌታነህ ከበደን ጨምሮ የቅዱስ ጊዮርጊስ አንዳንድ ተጨዋቾች በጉዳት ላይ ይገኛሉ፤ ይሄ የሁለተኛው ዙር ላይ አይጎዳችሁም?
አስቻለው፡- የፕሪምየር ሊጉ የአንደኛው ዙር ተሳትፎአችን ላይ ክለባችንን በጣም የጎዳው ጉዳት ነው፤ የጌታነህ መጎዳትንም አልጎዳንም አልልክም፤ ብዙ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቾች እሱን ለመያዝ ሲመጡ የቡድናችን ሌሎች ተጨዋቾች ክፍተት የሚያገኙበት አጋጣሚ ስለሚኖር ቢኖርልን ጥሩ ነበር፤ አሁንም ወደ ሜዳ በፍጥነት እንዲመለስልንም ምኞቴ ነው፤ ያም ሆኖ ግን ቡድናችን አሁን ጌታነህን ቢያጣም እንደ እነ አቤል አሜ ሳላህዲን ሰይድ እና በቅርቡ የፈረመው ሪቻርድም ስላሉ እየተቀያየሩ ተጫወተው ቡድናችንን በጋራ ሆነን ለታላቅ ውጤት እናበቀዋለን፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ…
አስቻለው፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ሁሌም ለክለባቸው የሚሰጡት ድጋፍ አስደሳችና የሚያምር ነው፤ በዛም ሊመሰገኑ ነው የሚገባው፤ እነዚህ ደጋፊዎች ከጎናችንም ናቸው፤ የሁለተኛው ዙር ውድድር ላይም የሊጉን ዋንጫ እንድናነሳ የእነሱም አስተዋፅኦ ከፍ ያለ ስለሚሆን ምንም ውጤት ይመዝገብ ትዕግስተኛ በመሆን እና ጠንክረው የሚቀርቡ ከሆነ በጋራ ዋንጫውን የምናነሳው ነው የሚሆነው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P