Google search engine

“ኮትዲቯርን ማሸነፋችን ማንንም እንዳንፈራ አድርጎናል” ረመዳን ዮሱፍ

“ለአፍሪካ ዋንጫ ብሔራዊ ቡድናችንን በማሳለፍ የቅርብ ዘመዴ ሳላህዲን ሰይድ የሰራውን ታሪክ መድገም እፈልጋለሁ”

“ኮትዲቯርን ማሸነፋችን ማንንም እንዳንፈራ አድርጎናል”
ረመዳን ዮሱፍ

በመሸሻ_ወልዴ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የብዙ የውድድር ዘመናት ቆይታዎችን ሳያደርግ ነው በአንዴ እና በፍጥነት ለብሔራዊ ቡድናችን ለመመረጥ እና በቋሚ ተሰላፊነትም ለመጫወት የቻለው፤ ረመዳን ዩሱፍ ይባላል፤ ይህ ተጨዋች ወጣት ሲሆን ተወልዶ ያደገው በቤንሻንጉል አሶሳ ከተማ ውስጥ ነው፤ በክለብ ደረጃ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የታዳጊዎች ቡድን ከተጫወተ በኋላ ያደገበት የዋናው ቡድን ሲፈርስ ወደ ተወለደበት ክልሉ ቤንሻንጉል በማምራት ለነስር ቡድን በብሔራዊ ሊግ ሊጫወት ችሏል፤ ከዛም በፕሪምየር ሊግ ደረጃ ወደ ስዑል ሽረ እግር ኳስ ቡድን ገብቶም ላለፉት አንድ ዓመታት ከስድስት ወራት ሊጫወት ችሏል፤ ከክለብ ባሻገር በብሔራዊ ቡድን ደረጃም በግራ መስመር የተከላካይ ስፍራው ላይ አበረታች እንቅስቃሴን በማሳየት ባለፉት የውድድር ጊዜያቶች ላይ የተመለከትነውን ረመዳን ዩሱፍን የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ አናግሮታል፤ ተጨዋቹም በሚከተለው መልኩ ምላሹን ሰጥቷል፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የቅ/ጊዮርጊሱ ምርጥ አጥቂ ሳላህዲን ሰይድ የቅርብ ዘመድ መሆንህን ሰማን?
ረመዳን፡- የእውነት ነው፤ ሳላህዲን ሰይድ የቅርብ ዘመዴ ነው፤ በዛ ላይ ደግሞ በጣም የማደንቀው እና የምወደውም ተጨዋች ጭምር ከዛ ውጪም በእግር ኳስ ተጨዋችነት ጉዞዬ አሁን ላይ ገና ወጣት ተጨዋች ከመሆኔ አኳያም ለወደፊቱ ትልቅ ተጨዋች እንድሆን ካለው ከፍተኛ እና የተካበተ ልምዱ አንፃር ብዙ ጠቃሚ ነገሮችንም እያካፈለኝ ያለ ተጨዋች በመሆኑ ለእሱ ትልቅ ምስጋናን ነው የማቀርብለት፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን መጫወት በጀመርክበት ሰዓት በእናንተ ቤተሰብ ውስጥ ከአንተ ውጪ ሌላ እግር ኳስ ተጨዋች ነበር?
ረመዳን፡- አዎን፤ እሱም ታላቅ ወንድሜ ነው፤ ሳዳት ዩሱፍ ይባላል፤ ለሲዳማ ቡናና ከዛምለጥቂት ጊዜ ወደ ቅ/ጊዮርጊ ገብቶ ከተጫወተ በኋላ ባጋጠመው ጉዳት የእግር ኳስን ሊያቆም ችሏል፡፡
ሊግ፡- በልጅነት ዕድሜህ ወደ እግር ኳስ ተጨዋችነት ሙያው ስታመራ ማንን አርአያ አድርገህ ነው ያደግከው? ኳስን የትስ ነበር የምትጫወተው?
ረመዳን፡- የእግር ኳስን መጫወት የጀመርኩት ተወልጄ ባደግኩበት ቤንሻንጉል አሶሳ ከተማ ውስጥ ነው፤ ያኔም ለኳስ የነበረኝ ፍቅር ከፍ ያለ ስለነበር በየቀኑም ነበር የምጫወተው፤ በወቅቱ ኳስን ስጫወት አድንቄ እና ተምሳሌቴ /ሞዴሌ/ አድርጌ ያደግኩት ተጨዋች ቢኖር የአሁን ሰዓት ላይ ለአዳማ ከተማ በመጫወት ላይ የሚገኘው የቀድሞው የብሔራዊ ቡድናችን ተጨዋች ሱሌይማን መሐመድን ነው፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን ልጅ በነበርክበት ሰዓት ያለ ምንም ተፅህኖ ነበር ስትጫወት የነበረው?
ረመዳን፡- በእኛ ሀገር ላይ ብዙ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ኳስ ከሚጫወቱ ይልቅ ወደ ትምህርታቸው እንዲያዘነብሉ የሚፈልጉበት ዕድል ሰፋ ያለ ቢሆንም የእኔ ቤተሰቦች ግን ሁለቱንም አብሬ እንዳስኬድ በመፈለግ እና በእኔ ላይም ምንም አይነት ተፅህኖንም ባለመፍጠር ከጎኔ ሆነው ይረዱኝ፣ ይመክሩኝ እና ያበረታቱኝም ነበር፤ በኋላ ላይ ግን በሁለቱም ጥቂት ከተጓዝኩ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ወደ ኳሱ በማዘንበል በፈጣሪ እርዳታ አሁን በምገኝበት እስከ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋችነት ባዳረሰኝ ደረጃ ላይ ልገኝ ችያለሁ፤ ከእዚህ በኋላም በእግር ኳሱ ለትልቅ ደረጃ የመድረሱ ራዕይ አለኝ፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ተጨዋች ባትሆን ኖሮስ?
ረመዳን፡- አልዋሽ

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P