Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ኮትዲቯር የተጓዝነው ለማሸነፍ እንጂ ለአቻ አይደለም”
ተክለማሪያም ሻንቆ /ጎሜዝ/

“የቀድሞ ግብ ጠባቂዎች በጎላቸው ውስጥ ብዙ ቆመው ይውሉ ስለነበር በርካታ ግቦችን ያስተናግዱ ነበር”

“ኮትዲቯር የተጓዝነው ለማሸነፍ እንጂ ለአቻ አይደለም”
ተክለማሪያም ሻንቆ /ጎሜዝ/

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን /ዋልያዎቹ/ በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ከዋሳኞቹ ግጥሚያዎች መካከል አንዱ የነበረውንየማዳጋስካር ብሔራዊ ቡድንን በማሸነፍ በተጠባቂነቱ አቻ የማይገኝለትን የመጨረሻውን ግጥሚያ በመጠባበቅ ላይ ሲሆን ይህ ፍልሚያም የፊታችን ማክሰኞ በኮትዲቯር አቢጃን ከተማ ላይ የሚደረግ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በተደለደለበት ምድብ ረቡዕ ዕለት በባህርዳር ከተማ ከማዳጋስካር ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4-0 በሆነ ውጤት ተጋጣሚውን ያሸነፈ ሲሆን በእዚሁ ድሉ መሰረትም ምድቡን የትናንቱን የኮትዲቯር እና የኒጀርን ጨዋታ ውጤት ሳይጨምርበ9 ነጥብ እየመራም ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን  በጨዋታ ብልጫ ጭምር ማዳጋስካርን በሰፊ የግብ ልዩነት ሲያሸንፍየድሉን ግቦች አማኑኤል ገብረ ሚካኤል፣ ጌታነህ ከበደ፣ አቡበከር ናስር እና ሽመልስ በቀለ ለማስቆጠርም ችለዋል፤  ይህን የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ አስመልክቶና ስለ ብሔራዊ ቡድናችን ለአፍሪካ ዋንጫ ስለማለፍ ተስፋ እንደዚሁም ደግሞ ከራሱ አቋምም ጋር በተያያዘ ባለፉት ሶስት የብሔራዊ ቡድናችን ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ /አንዱ ከማላዊ ጋር የተደረገ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ነው/ ያለ ክሊን ሺት /ምንም ግቦች ሳይቆጠርበት ከወጣው የዋልያዎቹ ግብ ጠባቂ ተክለማሪያም ሻንቆ /ጎሜዝ/ ጋር የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተንለት ምላሹን ሰጥቶናል፤ ተከታተሉት፡፡

ሊግ፡- ማዳጋስካርን 4-0 ማሸነፍ ችላችኋል፤ ጨዋታው ምን መልክ ነበረው? የድሉ ስሜትስ ምን ይመስላል?

ተክለማሪያም፡- በአፍሪካ ዋንጫ ወሳኙ የማጣሪያ ጨዋታ ላይ ቡድናችን ማዳጋስካርን ያሸነፈበት ግጥሚያ ለእኛ በጣም ጥሩ ነበር፤ ይህ ግጥሚያ ማሸነፍ መቻልም ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ እንደ መንደርደሪያ ጭምርም የቆጠርነው ስለነበር ባገኘነው ድል በጣም ልንደሰት ችለናል፡፡

ሊግ፡- ማዳጋስካርን በሰፊ ግብ ለማሸነፍ የረዳችሁ ዋንኛው ጥንካሬያችሁ ምን ነበር?

ተክለማሪያም፡-እኛ እነሱን ያሸነፍናቸው እንደ ቡድን በጋራ ሆነን ስለተጫወትን እንጂ በእነሱ ብቃት ላይ ተመስርተን ብቻ አይደለም፤ በልምምድ ሜዳ ላይ የሰራናቸውንና ያዳበርናቸውን የታክቲክ ትገበራዎችንም ነው በጨዋታችን ላይ ስለደገምናቸውእና እንደ ቡድንም ጥሩ ስለነበርን ግጥሚያውን በድል ልንወጣው የቻልነው፡፡

ሊግ፡- በማዳጋስካር ብሔራዊ ቡድን ላይ 4 ግቦችን ነው ለማስቆጠር የቻላችሁት፤ ያስቆጠራችሁት ጎል ግን አልበዛም?

ተክለማሪያም፡- የጎሉ ብዛት የቡድናችንን ጥንካሬ የሚያሳየን ነው፤ ስለዚህም ጎል በዝቷል ብለን አናስብም፤ በእርግጥ ከዚህ በፊት የነበሩት ብዙ ቡድኖቻችን ጨዋታዎችን የሚያሸንፉበት መንገድ በጠባብ ውጤት ስለነበር ነው ምንአልባት የአሁኑ ጎል የበዛ ሊመስል የቻለው፤ ከዚህ በፊት እኮ በወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ላይ ቡድናችን ጠንካራ የሚባሉትን ሲገጥም በዚህ ደረጃ ብዙ ጎሎችን አያስቆጥርም ነበር፤ እንደውም የኢትዮጵያ ቡድን ላይ በአብዛኛው ጨዋታ ላይ ጠንካራ ሀገሮችን ሲገጥም ስንት ይገባበታል ይባላል እንጂ ያገባል ሲባል ተሰምቶም አይታወቅም ነበርና በአሁኑ ግጥሚያችን ብዙ ጎሎችን አስቆጥረን ያሸነፍንበት መንገድ ኳስን ከኋላ አስጀምረን በመጫወታችንና ይሄም የመጣው ደግሞ ከልምምድ ሜዳው የጨዋታ ትገበራችንም ነውና ይሄን ነው ልናስቀጥለው የሚገባው፡፡

ሊግ፡- በአፍሪካ ዋንጫው የማጣሪያ ጨዋታ አሁን ምድባችንን እየመራን ነው፤ የካሜሮኑን ትኬት ለመቁረጥም ወሳኙን ጨዋታ ከኮትዲቯር ጋር የፊታችን ማክሰኞ እናደርጋለን፤ በዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ? /ቃለ-ምልልሱ የተሰራው ረቡዕ ምሽት ነው/

ተክለማሪያም፡- እኛ ዋልያዎች ለአፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ኮትዲቯርን በሜዳዋ የምንፋለምበት ግጥሚያ ከፊታችን ቢደቀንብንም፤ የአቻ ውጤት ቢበቃንም ወደ እነሱ ሀገር የምንጓዘው ግን ጨዋታውን ለማሸነፍ እንጂ ለአቻ ብለን አይደለም፤ ይህን ጨዋታ ለማሸነፍ የሚያስችልም ጥሩ ቡድን አለን፤ የቡድኑ ጥሩነትም በኳስ ቁጥጥር ላይ ያተኮረና ቅርፅ ያለው ቡድን መሆኑምነው፡፡

ሊግ፡- ከማዳጋስካሩ ጨዋታ በፊት አንድ ነጥብ ኖሮን ቢሆን አስቀድመን ለአፍሪካ ዋንጫው እናልፍ ነበር የሚል ነገር በስፋት እየተደመጠ ይገኛል?

ተክለማሪያም፡- ልክ ነህ፤ ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት አባባሎች በእግር ኳሱ ውስጥ ሊደመጡ እንደሚችሉ የታወቀ ነገር ነው፤ ማዳጋስካርን ከማሸነፋችን በፊት አንድ ነጥብ ኖሮን ቢሆን ኖሮ ይሄኔ ለአፍሪካ ዋንጫው አልፈን ነበር፤ ግን ከኒጀርም ሆነ ከማዳጋስካር ጋር በእነሱ ሀገር ሜዳ ላይ ስንጫወት ይሄን ማሳካት አልቻልንምና ባለፈ ነገር ላይ ተመልሰን ወደ ኋላ መምጣት የለብንም፡፡ 

ሊግ፡- ከኒጀር ጋር በነበረን ጨዋታ ቢያንስ አንድ ነጥብ መያዝን እንችል ነበር የሚል ነገር እየተነሳ ይገኛል?

ተክለማሪያም፡- የእውነት ነው፤ ቡድናችን ከነበረው ጥሩ ብቃት አኳያ ያን ነጥብ መያዝ የምንችልበት ብዙ እድሎች ነበሩን፤ ግን የኳስ ነገር ሆነና ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

ሊግ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ በአብዛኛው በራሱ ዕድል ላይ ተወስኗል፤ ኮትዲቯርን ማሸነፍ አልያም ደግሞ አቻ መለያየት፤ ይሄን የሚያሳካው ይመስልሃል?

ተክለማሪያም፡- የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ በጣም ጠንካራ እና በፕሮፌሽናል ተጨዋቾችም የተዋቀረ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፤ ያ እኛን አያስፈራንም፤ ለእነሱ የተለየ የሚባል ግምትንም አንሰጥም፤ ምክንያቱም እነሱን በሜዳችን ላይ አሸንፈናቸዋልና፤ ከዛ ውጪ አይደለም ኮትዲቯር ማዳጋስካርም እኮ ትልቅ ቡድን ነው፤ ለዛም ነው በምድባችን ጨዋታ ላይ እየተፎካከረን የሚገኘው፤ እነሱን እኛ 4 ጎል አስቆጥረን አሸንፈናቸዋል፤ ስለዚህም ከኮትዲቯርም ጋር በምናደርገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታችን ላይ እኛ የምንጫወተው እግር ኳስንና ምንም የማያስፈራውን ነገር ስለሆነ እነሱን አሸንፈን ወይንም ደግሞ አቻ ተለያይተን ለአፍሪካ ዋንጫው የማናልፍበት ምንም አይነት ምክንያት የለም፡፡

ሊግ፡-ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ሆነ ለኢትዮጵያ ቡና በግብ ጠባቂነት ስትጫወት በአብዛኛው የጨዋታ እንቅስቃሴዎችህ ኳስን በእግርህ ጭምር ነው ከቡድንህ ጓደኞች ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ እየተጫወትክ ያለኸው፤ በእዚህ አጨዋወት ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ?

ተክለማሪያም፡- በአሁን ሰዓት ይሄን አጨዋወት ዓለም ላይ ብዙዎች እየተገበሩት ነው የሚገኘው፤ እኔም ወደ ቡናና ወደ ብሔራዊ ቡድን ተፈልጌ ስጠራም ይሄን እንቅስቃሴ ተከትዬና እንደ ትርፍ ሰውምሆኜ ነው ከጓደኞቼ ጋር ተጫውቼ ቡድኖቼን ልጠቅም እንድችል የተፈለግኩት፤ በእዚህ እንቅስቃሴ ውስጥም በቡና ቡድን ቆይታዬም ሆነ በብሔራዊ ቡድን ደረጃም  የግብ ጠባቂነት አጨዋወቱን  እና ታክቲኩን ገና በመላመድም  ላይ ስለሆንኩኝ ጥሩ ነገር እንዳለኝ ሁሉ ስህተቶችንም የሰራሁባቸው አጋጣሚዎች አሉና እነዛን ለማረም እየተዘጋጀው ነው፡፡ በዘመናዊ ፉትቦል እግር ኳስበግብ ጠባቂዎች ላይ ተመስርቶ  ነው አንድ ቡድን የቢውልድ ሀፕ አጨዋወቱን ተግባራዊ የሚያደርገው፤ በዓለም እግር ኳስ ታላላቅ የሚባሉት ግብ ጠባቂዎች በዚህ ውስጥ እያለፉ በመምጣት ነው አንድአንዶቹ አሁን ላይ ለትልቅ ደረጃ ላይ የደረሱት እነሱ ኳስን በእግር በመጫወትም ለዛ ጥሩ ደረጃ ላይ የበቁትም ስህተትን እየሰሩም ነው፤ እኛ ሀገር ላይም ይሄ የጨዋታ ትግበራ ለብዙዎቻችን አዲስ እና ገና እየተላመድነውም ያለ ስለሆነ ግብ ጠባቂዎችን ስህተት ቢሰሩ እንኳን ከስህተታቸው የሚማሩበትን ነገር መጠቆም እንጂ አጨዋወቱን መተቸት ተገቢ ነው ብዬ አላምንም፡፡

ሊግ፡- ባለፉት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ እና በአንድ የወዳጅነት ግጥሚያ ላይ ግብን ባታስተናግድም በቡድናችን ላይ ጎል እንዳይቆጠር ያደረግክበት ሁኔታ ቢኖርም ስህተቶችንም የሰራክባቸው አጋጣሚዎች አሉ፤ በተለይ ከማዳጋስካር ጋር በነበረን የማጣሪያ ጨዋታ ላይ፤ በእዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ?

ተክለማሪያም፡- እንደ ግብ ጠባቂነቴ ስህተትን አልሰራሁም የምል አይነት ተጨዋች አይደለሁም፤ እግር ኳስ ጨዋታ በስህተት የተሞላም ጭምር ነው፤ በእኛ ሀገር ላይ ግን ብዙ ጊዜ በረኞች ላይ ነገሮች ይገናሉ፤ በማዳጋስካሩ ጨዋታ እኔ እንደ ቡድኑ አጨዋወት እንደ ሊብሮ ሆኜም ነበር እየተጫወትኩ የነበርኩት፤ አጨዋወቱን በእኛ ሀገር ደረጃ አዲስ ከመሆኑ አኳያ በመላመድ ላይም ነው ያለሁት፤ ከዛ በመነሳት አንድ ኳስን በእግሬ  ለመጫወት እና ለጓደኞቼም ለማቀበል ፈልጌ በእነሱ ተጨዋች ፈጥኖ በመምጣቱ ብሎክ ተደርጎብኝ ስህተትን ፈፅሜ ነበር፤ ሌላ ደግሞ ከክልል ውጪ በአየር ላይ ያገኘዋትንና በጎን በኩል የመጣችሁን ኳስ በእጄ ነክቼያት ቅጣት ምት እንዲሰጥብንም አድርጊያለውና እነዚህ ስህተቶች በኳስ ውስጥ የሚያጋጥሙና ሊስተካከሉም የሚችሉ ናቸውና ይሄን አጨዋወት ደጋግመን ስናዳብረው ዋንኛው ተጠቃሚዎቹ እኛው ነን፡፡

ሊግ፡- በማዳጋስካሩ ጨዋታ የጎላ ስህተትተን ሰርተሃል ተብለህ እየተወቀስክ ይገኛል?

ተክለማሪያም፡- እኔ ደግሞ ስህተትን ብሰራም ከምንከተለው እና ሜዳ ላይ ለመተግበር ከምንሞክረው አዲስ አጨዋወትአኳያ ስህተቱን የጎላ ነበር ብዬ አላምንም፤ እንደውም ያደረግኩት ነገር የሚታረም ነገር ስለሆነም እንደ ስህተት አድርጌም አልቆጥረውም፤ እንደ አጠቃላይ የዛን ዕለት ጨዋታም ስህተትን ሰራው ብዬም ራሴን ወደ ኋላም አላስቀርም፤ ምክንያቱም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ከዚህ በፊት የነበሩት ብዙ ግብ ጠባቂዎች ከሚሰጣቸው ስልጠና አኳያ ግባቸው ውስጥ ብዙ ቆመው ይውሉ ስለነበርና በእግራቸውም ኳሱን ይዘው ብዙም ስለማይጫወቱ በርካታ ግቦች ይቆጠርባቸው ነበር፤ ለበረኞች የሚሰጠው የአሁኑ ስልጠና ግን አልፎ አልፎ ካልሆነና በእግር ኳስ ውስጥ ሊያጋጥሙ ከሚችሉ ነገሮች ካልሆነ በስተቀር ብዙ ግቦችን እንድታስተናግድ የሚያደርጉን ነገሮች አይደሉምና በእዚህ የግብ ጠባቂነቴ ብቃት ዙሪያ ራሴን ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ለማስቀመጥ ጠንክሬ እሰራለሁኝ፡፡ 

ሊግ፡- በመጨረሻ…?

ተክለማሪያም፡- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የማዳጋስካር አቻውን ካሸነፈ በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫው ሊያልፍ የሚችልበትን እድል በራሱ እድል ላይ እንዲወሰን አድርጓል፤ የአሁኑ ቡድን ብዙ ነገሮችንም ለማድረግ የሚያስችል ጥሩ አቅም አለው፤ በየመጫወቻ ስፍራዎቹ ምርጥ የተጨዋቾችን ስብስብ የያዘ ስኳድም ነው ያለን፤ ከዛ በተጨማሪም ከአጥቂ ብቻ ሳይሆን ከየትም የመጫወቻ ቦታዎች ላይም ጎልን ማስቆጠር የሚችሉ ተጨዋቾችም ስላሉን ወደ አቢጃን ባደረግነው ጉዞ ታላቋን የፉትቦል ሀገር ኮትዲቯርን አሸንፈን ወይንም ደግሞ አቻ ተለያይተን ዳግም በአፍሪካ ዋንጫው ላይ ለመሳተፍ እና በብዙ ነገሮች የተከፋፈለውን ህዝባችንን ወደ አንድ በማምጣት በጋራ አብረን ለመጨፈር ዝግጁ ነን፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P