Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ወልዋሎ በውጤታማነቱ እንደሚቀጥል እርግጠኛ ነኝ” ካርሎስ ዳምጠው /ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ/

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጨዋችነት ተሳትፎው ለክለቡ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ በመጫወት ከወዲሁ ሶስት ግቦችን አስቆጥሯል፤ በእዚህ ግብ አስቆጣሪነቱም ቡድኑን ከጓደኞቹ ጋር በመሆንና በጋራ በመጥቀምም ለሊጉ መሪነት እንዲበቃም አድርጎታል፤ ይሄ ተጨዋች ካርሎስ ዳምጠው ሲባል፤ ተወልዶ ያደገው በናዝሬቷ ቀበሌ 07 ውስጥ ነው፤ በተክለ ሰውነቱ በጣም ግዙፍ የሆነው እና 91 ኪ.ግራም የሚመዝነው ካርሎስ ዳምጠው ወልዋሎ አዲግራትን ከመቀላቀሉ በፊት በተለያዩ ክለቦች ውስጥ በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን እነዚህም ቡድኖቹ አርሲ ነገሌ፣ መቐለ 70 እንደርታ፣ ጅማ አባቡናና የአሁኑ ቡድኑ ደግሞ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ናቸው፡፡
የወልዋሎ አዲግራቱን ተጨዋች ካርሎስ ዳምጠውን ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ በኳስ ሕይወቱ እና በሌሎችም ተያያዥነት ባላቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ያናገረው ሲሆን በቆይታቸውም ወቅት ተጨዋቹ የሰጠው ምላሽ በሚከጸላ መልኩ ቀርቧል፡፡


ሊግ፡- በመጀመሪያ ከስምህ መጠሪያ እንነሳ፤ ካርሎስ በሚል ስምም ነው የምትጠራው፤ ይሄ ስም እንዴት ወጣልህ? ማንስ ነው ስሙን ያወጣልህ?
ካርሎስ፡- ካርሎስ የሚለውን ስም ያወጣልኝ ወላጅ አባቴ አቶ ዳምጠው….. ነው፤ ይሄ ስም ሊወጣልኝ የቻለውም አባቴ የብራዚላዊው ሮቤርቶ ካርሎስ በጣም አድናቂው ስለነበር በእዚሁ ነው ስያሜው ወጥቶልኝ ከልጅነቴ አንስቶ ስሙን እየተጠራሁበት ያለሁት፡፡
ሊግ፡- አባትህ የሮቤርቶ ካርሎስ አድናቂ መሆናቸውን ገልፀሃል፤ አንተስ የየትኛው የእግር ኳስ ተጨዋች አድናቂ ሆነህ ነው ወደ ተጨዋችነቱ ሙያ የመጣኸው?
ካርሎስ፡- የብራዚላዊው ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮ ዳሊማ አድናቂ ሆኜ ነዋ! ከእሱ ውጪ ሌላ በቅድሚያ ማንን አደንቃለሁ ብለህ ነው፤ ሮናልዶ እኮ ልዩ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ነው፤ በጣምም ነው የምወደው፤ እሱ ለእኔ ተምሳሌቴ /ሮል ሞዴሌም/ ጭምር ነው፡፡
ሊግ፡- ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ፕሪምየር ሊጉን በሙሉ የማሸነፍ ሪከርድ ከወዲሁ እየመራ ይገኛል፤ ይሄ ስኬት እንዴት ሊመጣ ቻለ? ድሉስ ከዚህ በኋላ ይቀጥላል?
ካርሎስ፡- ወልዋሎ አዲግራት ለፕሪምየር ሊጉ የእዚህ ዓመት ተሳትፎው ለመወዳደር ሲነሳ ጥሩ ውጤትን ማምጣት አልሞ ስለነበር ዝግጅቱን ጠንከር ባለ መልኩ ነው ሲሰራ የነበረው በእዚህ ሁኔታ ለማለማመድ መቻሉም ነው በሜዳው ላይ ያደረገውን አንድ ጨዋታና ከሜዳው ውጪ ያደረጋቸውንም ሁለት ጨዋታዎች በማሸነፍ የሊጉን አጀማመር ጥሩ ሊያደርግ የቻለውና የእስካሁኑ የስኬቱ ሚስጥር የጥሩ ስራውና የልፋቱም ውጤት ብቻ ነው፡፡ ከዛ ውጪ ቡድናችንን ስኬታማ እያደረገ የሚገኘው ሌላው ነገር በሜዳ ላይ እንቅስቃሴያችን እንደግል ሳይሆን እንደቡድንም ስለምንንቀሳቀስ ነውና ይሄ የውጤታማነት ጉዞአችን ወደፊትም ቀጣይነት እንደሚኖረው ለመናገር እፈልጋለው፡፡
ሊግ፡- ወልዋሎ አዲግራት በሊጉ ጥሩ አጀማመርን አሳይቷል፤ የውድድር ዓመቱ ሲጠናቀቅ በደረጃው ሰንጠረዥ ምን ላይ እንጠብቀው?
ካርሎስ፡- ወልዋሎ አዲግራት በፕሪምየር ሊጉ ላይ ባለው የውድድር ተሳትፎው የራሱ የሆነ እቅድና ግብ ማለትም የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ አሊያም ደግሞ የጥሎ ማለፉን ዋንጫ ማንሳት የሚለውን መርህ በፕሬዝዳንታችን አማካይነት ቢያስቀምጥም እኛም እንደ ቡድኑ ተጨዋችነታችን ከፊታችን ያለውን እያንዳንዳቸውን ጨዋታዎች በማሸነፍ እና ውጤታማም በመሆን ይህንን የቡድኑን ህልም ለማሳካት በሚገባ ተዘጋጅተናል፤ በሊጉ አሁን ላይ እንደአጀማማራችንም በህብረት እና እንደ ቡድንም በመንቀሳቀስ ጥሩ ጉዞንም እያደረግን ይገኛልና ይሄን ስኬታችንን አሁንም እደግመዋለው ወደፊትም የያዝነውን ነገር የምናስቀጥለውም ይመስለኛል፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ አንዳንድ ቡድኖች በሜዳቸውም ሆነ ከሜዳቸው ውጪ ሲጫወቱ ጥሩ አጀማመርን ያሳዩና በኋላ ላይ ይዋዥቃሉ፤ ይሄ ሁኔታ በእዚህ ዓመት እናንተን የሚያጋጥማችሁ ይመስልሃል?
ካርሎስ፡- ወልዋሎ አዲግራት በቡድን ግንባታው ላይ በሜዳውም ሆነ ከሜዳው ውጪ ሲጫወት የራሱ የሆነ አጨዋወት ያለው እና በዛ አጨዋወትም ምን ማድረግ እንዳለበት የሚያውቅ ቡድን ስለሆነ በመጀመሪያ እነዛን ሊጠቀምባቸው በሚገባ ተዘጋጅቷል፤ የእግር ኳስ ላይ በእርግጥ በሜዳህ ላይ ስትጫወት ብዙ ደጋፊዎችህ ሁሌም ከአንተ ጎንህ ስለሚሆኑ በዛ በጣም ልትጠቀም ትችላለህ፡፡ የእኛ ቡድን ግን አሁን ላይ በሜዳውም ሆነ ያለሜዳው ሲጫወት ያለው የቡድን መንፈስ /ቲም ስፕሪት/ በጣም ጥሩ ስለሆነ ቡድናችንን ፈፅሞ መዋዠቅ ያጋጥመዋል ብዬ አላስብም፡፡
ሊግ፡- ለወልዋሎ አዲግራት የድል ጎሎችን እያስቆጠርክ ነው፤ ይሄንን ግብ ማግባትህን ወደፊትስ ታስቀጥላለህ?
ካርሎስ፡- አሁን ላይ እንደ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ክለብ ተጨዋችነቴ እኔን ስለማስቆጥራቸው ግቦችም ሆኑ በግል ስለማመጣቸው ስኬቶች ፈፅሞ አያስጨንቀኝም፤ እኔን አሁን ላይ የሚያስጨንቀኝ ለቡድኔ እንደቡድን በጋራ በመንቀሳቀስ ጥሩ ውጤትን በምን መልኩ ማምጣት አለብን የሚለው ነገር ነውና በእዚሁ ሁኔታ ነው ከቡድኔ ጋር እየተጓዝኩ የምገኘው፡፡
በእዚህ ቡድን የተጨዋችነት ቆይታዬ ደግሞ አሁን ላይ አሰልጣኜ ዩሃንስ ሳህሌ እኔን በተለያዩ ቦታዎች ላይ እያሰለፈኝ እያጫወተኝና እሱ ደግሞ በስራም የሚያምንና ጥሩም አሰልጣኝ በመሆኑ በብቃቴ ዙሪያም ብዙ ነገሮችን ያሻሽልልኛል ብዬም እያሰብኩ ነው፡፡
ሊግ፡- ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለመጫወት ስትመጣ በሀገሪቱ አጥቂዎች ከዚህ በፊት የተያዘውን የኮከብ ግብ አግቢነት ሪከርድና ክብር እሰብራለው ብለህ ነበር፤ ይህን ግን ፈፅሞ ለማሳካት አልቻልክም፤ እንደውም እኮ ለቡድንህም መከላከያ ብዙ ለመሰለፍና ለመጫወትም አልቻልክምና እነዚህን ሁኔታዎችን ወደኋላ ሄደህ በምን መልኩ ነው የምታስታውሳቸው?
ካርሎስ፡- አሁን ያለፈው አልፏል፤ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን የታችኛው ሊግ ተሳታፊ ከነበረው አርሲ ነገሌ በመምጣት መከላከያን ስቀላቀል አዎን ከላይ የጠቀስካቸውን አስተያየት ሰጥቼ ነበር፤ በጊዜው ያን ለማለት የፈለግኩትም በታችኛው ሊግ ላይ 16 የሚደርሱ ጎሎችን ለክለቤ አስቆጥሬ ስለነበርና በዛን ወቅት የነበረኝን ብቃትም አስቀጥዬ አስጉዛለሁ ብዬ ስላሰብኩ ነው፤ ያም ሆኖ ግን በወቅቱ በፕሪምየር ሊግ ደረጃ ያሳለፍኩት ጊዜ ለእኔ ጥሩ አልነበረም፤ ሊጉን እንደምፈልገው አይነትም ሆኖ አላገኘሁትም፤ ፕሪምየር ሊግና ከፍተኛ ሊግ በጣም እንደሚለያይ ነው ያየሁት፤ ፕሪምየር ሊግ ኳስን በአህምሮ ተጠቅመህ የምትጫወትበት እና የተለያዩ ታክቲኮችንም አውቀህ የምትጫወትበት ነውና ያን ካለማወቅ እና ጠንካራ ስራንም ካለመስራት በምፈልገው ደረጃ ሳልጫወት የቀረሁበት ነው፤ ከዛ ውጪም ፕሪምየር ሊጉ ጠንካራ ሆኖም እኔም ደካማ ነበርኩ ማለት ነው ምክንያቱም ብዙ ጎል አገባለው እና ውጤት አመጣለሁ ስትል ሁሌ ሰርተህ ነው ማሳየት ያለብህ፤ እኔ ደግሞ የመከላከያ ክለብ ውስጥ ይህንን ማድረግ አልቻልኩምና በወቅቱ የተናገርኩት ነገር ከስራው ይልቅ ወሬውን ያስቀደምኩበት ሁኔታ ስለነበር በተናገርኩት ነገር ጊዜው ቢያልፍም ይቆጨኛል፤ አሁን ላይ ግን ስራን በመስራት የሚታወቅን ጥሩ አሰልጣኝ በማግኘቴ ጥሩ ተጨዋች ለመሆን ተዘጋጅቻለው፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ…?
ካርሎስ፡- የእግር ኳስን ስጫወት ለሀገሬ ብሔራዊ ቡድን ተመርጬ መጫወትን አልማለው፤ ይሄን እድል ለማግኘትም ጠንክሬ እሰራለው፤ ከዛ ውጪ ማለት የምፈልገው ዛሬ በኳሱ ለደረስኩበት ደረጃ ለእኔ ብዙ ነገሮችን ያደረጉልኝንና እንደ መምህሬም የምመለከታቸውን ቤተሰቦቼን እንደዚሁም ደግሞ የእኔን ብቃት በሚገባ የተረዳውን አሰልጣኝ ዩሃንስ ሳህሌንና በእኔ የተጨዋችነት ህይወት ውስጥ ያለፉትን ሁሉ ማመስገን እፈልጋለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P