Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ወደ ቀጣዩ ዙር እንለፍም አንለፍም አልአህሊን አናሸንፋለን” ያሬድ ዘውድነህ /ጅማ አባጁፋር/

መሸሻ ወልዴ

የአፍሪካ ቶታል ካፕ ቻምፒዮንስ ሊግ
የመልስ ጨዋታዎች ዛሬና ነገ ይካሄዳሉ፤
በአዲስ አበባ ስቴድየምም ኢትዮጵያዊው
ጅማ አባጅፋር በመጀመሪያው ጨዋታ የ2ለ0
ሽንፈት ካደረሰበት የግብፁ አል አህሊ ጋር
ነገ በ10 ሰዓት ይጫወታል፡፡
ጅማ አባጅፋር ከአልአህሊ ጋር
ለሚያደርገው የነገው የመልስ ጨዋታም
ዝግጅቱን በተጠናከረ መልኩ እየሰራ
ሲሆን ይህንን ጨዋታ ተንተርሰን እና
ስለመጀመሪያው የሁለቱ ቡድኖች ፍልሚያ
እንደዚሁም ደግሞ ሌሎችንም ጥያቄዎች
በማንሳት ለቡድኑ ተጨዋች ያሬድ ዘውድነህ
አቅርበንለት ምላሹን እንደሚከተለው
ሰጥቶናል፡፡
ሊግ፡- የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ
የአልአህሊና የጅማ አባጅፋር የመጀመሪያው
ጨዋታ በአልአህሊ አሸናፊነት ተጠናቋል፤
ስለ ግጥሚያው እና ከዚህ በመነሳት
ስላደረጋችሁት ጉዞ ምን ትላለህ?
ያሬድ፡- ወደግብፅ ተጉዘን ከአልአህሊ
ጋር ያደረግነው ያለፈው ሳምንት ዐርብ
ጨዋታ ከዚህ በብዙ ችግር ውስጥ ሆነን
ወደ ስፍራው በመሄድ ያከናወነው ግጥሚያ
ሲሆን ከጨዋታው በፊትም አድካሚ
የመኪና ጉዞን ያደረግንበት ነበር፤ ያም ሆኖ
ግን በጉዞው ላይ የነበረብንን ብዙ ድካም
በጨዋታው ላይ ችግር እንዳይፈጥርብን
በማሰብ የፕሪማች ውይይታችን ላይ በደንብ
ስለተነጋገርንበት ያ በሜዳ ላይ ምን
አይነት ችግር ሳያመጣብን ቀርቷል፤ ለእዚህ
በዋናነት የጠቀመንና የተነጋገርንበት ሁኔታ
እግራችን ላይ ኳስ ሲገባ ብዙም ሳንሯሯጥ
ኳሱን ይዘን ለመጫወት በመቻላችን ነውና
ይህን ሀሳብ ተግባራዊ አድርገናል፤ ኳሱ
ከእኛ ስር አይወጣም ነበር፤ ብዙ ጉልበትም
አንጨርስም ነበርና ኳስ ይዘን መጫወታችን
ካደረግነው አድካሚ የሆነ ጉዞ አንፃር ምንም
እንኳን ሽንፈትን እናስተናግድ እንጂ መልካም
የሚባል እንቅስቃሴ እንድናደርግ አስችሎናል፡፡
ሊግ፡- የአል አህሊን አቋም ጨዋታው
ላይ እንዴት ተመለከትከው?
ያሬድ፡- አልአህሊዎች ኳስን ሲጫወቱ
ደስ ይላሉ፤ በጥራትና በፕሮግራምም ነው
የሚንቀሳቀሱት፤ ከእኛም ጋር በአጨዋወት
ልዩነት እንዳላቸውም ያስታውቋል፤ ኳሱን
ስርአት አስይዘውትም ነው ሲጫወቱ
የነበሩት፤ በፈለጉት ሰአት ምን ማድረግ
እንዳለባቸውም ያውቃሉና በእዚያን ዕለት
ጨዋታ ጥሩ ሆነው ነው ያገኘኋቸው፤
እኛም ደግሞ ያን ጨዋታ በብዙ ችግር
ላይ ሆነንና አድካሚም ጉዞ አድርገን ነበር
የተጫወትነውና የእኛም ቡድን ጥሩ ነበር፡፡
ሊግ፡- በአዲስ አበባ ስታዲየም
ከአልአህሊ የሚኖራችሁን የነገው የመልስ
ጨዋታ እንዴት እንጠብቀው?
ያሬድ፡- አልአህሊዎችን የምንፋለ
ምበት የነገው ጨዋታ ለእኛ በጣም ከባድ
ነው፤ ወደ ቀጣዩም ዙር ለማለፍ ጎሎችን
ስለምንፈልግ አጥቅተን ነው የምንጫወተው፤
የእሁዱ ጨዋታ ላይ በመጀመሪያው ግጥሚያ
አራት ተከላካዮችን እንዳይንቀሳቀሱ አድርገን
ነበር የተጫወትነውና አሁን ግን የመስመር
ላይ ተከላካዮቻችን ስፍራውን ነቅለው
እንዲጫወቱም እናደርጋለንና በእዛ መቻኮል
በሌለበት እንቅስቃሴ ውስጥ ሆነን ግጥሚያውን
አሸንፈን ለመውጣት ጥረትን እናደርጋለን፤
የነገው ጨዋታ ላይ አልአህሊዎች ወደ ቀጣዩ
ዙር ለማለፍ ሰፊ እድል ስላላቸው እነሱ ኳስን
በመያዝ አልያም ደግሞ እየወደቁም ሰአት
ሊገድሉብህና ውጤቱን አስከብረውም ሊወጡ
ስለሚችሉ እኛ ከስሜታዊ አጨዋወት
ውስጥ በመውጣት በተረጋጋ እና ነፃ በሆነ
ሁኔታም ብዙ የሆነውን 90 ደቂቃ በመጫወት
ከተሳካልን እነሱን አሸንፈን ወደ ሚቀጥለው
ዙር ለማለፍ ካልሆነ ደግሞ ባናልፍ እንኳን
አልአሊዎችን ለማሸነፍም ነው የተዘጋጀነው፡፡
ሊግ፡- አል አህሊ እና እናንተ
ባደረጋችሁት የመጀመሪያው ጨዋታ በኳስ
እንቅስቃሴው ማን የተሻለ ነበር?
ያሬድ፡- አልአህሊዎች የተሻሉ ነበር፤
ከእዛ ውጪ እኛም በእዚህ ችግር እና የድካም
ስሜት ውስጥ ሆነን ያደረግነው ጨዋታም
ጥሩ ሊባል የሚችል ነው፤ የሁለታችን ያለፈው
ሳምንት ዐርብ ጨዋታ በሜዳ ላይ እንደታየው
የእነሱ አጨዋወት በጣም ስርዓት የነበረውና
ጥሩ ሆኖ ያየሁት ነው፤ በእኛ በኩል ደግሞ
ኳስ በእነሱ ስር ስትገባ ተጭነን /ፕሬስ
አድርገን/ በመጫወት ብዙ እንነጥቃቸውም
ነበር፤ እነሱ በረጅሙ ሲጥሉትና ሲያበላሹት
ብቻም ነበር ኳስን እናገኝ የነበረውና
ከነበረብን የድካም ችግር አኳያ 90 ደቂቃውን
ሙሉ መልካም በሚባል እንቅስቃሴ ጨርሰን
መጫወታችን ያልተጠበቀም ነበር፡፡
ሊግ፡- ከአልአህሊ የሚኖራችሁ
የመልስ ጨዋታ ነገ ሲከናወን ኃላፊው ወደ
ምድብ ድልድሉ ይገባል፤ ወዳቂው ደግሞ
ወደኮንፌዴሬሽን ካፑ ያመራል? በእዚህ ዙሪያ
የምትለው ነገር ካለ?
ያሬድ፡- ጅማ አባጅፋር የነገው ጨዋታ
ላይ ተጋጣሚውን አልአህሊ ጥሎ ወደምድቡ
ድልድሉ ከገባ ለእኛም ሆነ ለሀገሪቱ እግር
ኳስ የሚያበረክተው ጥቅም ከፍ ያለ ነው
የሚሆነው፤ እነሱን አሸነፍክ ማለት የአገራችን
ክለቦች የመሳተፍ ቁጥሩ ይጨምራል ከዛ
ባሻገር ደግሞ የውድድሩን ጉዞ እያሳመርክ
ስትሄድም የሚገኝ ብዙ ገንዘብ አለና
በፋይናንስም የምትጠናከርበት ሁኔታ
ስለሚኖር ጨዋታውን በአሸናፊነት ለመፈፀም
ከፍተኛ ጥረትና እናደርጋለን፤ ያ ካልተሳካም
በሜዳችን ላይ የምናደርገውን የነገን ጨዋታም
አሸንፈን ነው ወደ ኮንፌዴሬሽኑ ካፑ
ውድድር መግባት የምንፈልገው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P