Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ በገለልተኛ ሜዳ መጫወታችን አያሰጋንም” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአማካይ ስፍራ ተጨዋች በዛብህ መላዮ

በኮትዲቯር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2022/23ቱ  የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታዎች  በየከተሞቹ  የተጀመሩ ሲሆን  በመጀመሪያው ቀን በተደረገው  ግጥሚያም አንጎላ ሴንትራል አፍሪካን 2-1፣ ሊቢያ ቦትስዋናን 1-0  እና  ጋና  ማዳጋስካርን  3-0 አሸንፈዋል። ይኸው ግጥሚያ  ከትናንት በስቲያና ትናንትም ቀጥሎ ውሏል።  በእዚሁ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ  ከማላዊ፣ ከግብፅ እና ከጊኒ ብሄራዊ ቡድን ጋር የተደለደለው  የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም /ዋልያዎቹ/  የመጀመሪያ ግጥሚያቸውን ነገ እሁድ ከማላዊ ብሄራዊ ቡድን ጋር   የሚያደርግ ሲሆን ሌሎቹን  ግጥሚያዎችንም  ከሜዳው ውጪ  በገለልተኛ  ሀገራት ጭምር እንደሚያደርግም  ታውቋል። የኢትዮጵያ  ብሄራዊ  ቡድን  /ዋልያዎቹ/  የሚያደርጋቸውን የማጣሪያ ጨዋታዎችን ጨምረን ከክለቡ ፋሲል ከነማ ጋር  በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ  ለብሄራዊ ቡድናችን የተመረጠውን  በዛብህ መላዮን የሀትሪክ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ አናግሮት ተጨዋቹ ተከታዩ  ምላሽ ተሰጥቶታል።

ለአፍሪካ ዋንጫው ማጣሪያ እያደረጋችሁ ስላለው ዝግጅት

“ዝግጅታችን አሪፍ ነው፤ የወዳጅነት ጨዋታዎችንም ከሌሴቶ ብሄራዊ ቡድን ጋር አድርገናል። ስንለማመድ የነበርነውም በተቃራኒ ቡድን ክፍተቶች  እና በእኛም ጠንካራ ያልሆነ ጎን  ዙሪያም  ነበርና   በእዚሁ መልክ ስንጓዝ ቆይተናል”።

ከሌሴቶ ብሄራዊ ቡድን ጋር ያደረጋችሁት  የወዳጅነት ግጥሚያ ስለነበረው ጥቅም

“የወዳጅነት ጨዋታ ጥቅሙ ወደ ማላዊ ስንጓዝና ከእነሱ ጋር ስንጫወት ሊያጋጥሙን የሚችሉትን ነገሮች ታሳቢ ያደረገ ነው፤  በእዚሁ የአቋም መለኪያ ግጥሚያ ሁሉንም ተጨዋቾችንም ያሳተፈም ነበርና ክፍተቶቻችንን በማረም ለዋናው ግጥሚያ በደንብ ስለሚያዘጋጀንና ስህተቶችንም ላለመድገም  ስለሚያደርገን  ያለው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ነው”።

ከማላዊ ብሄራዊ  ቡድን ጋር ስለሚኖራችሁ የመጀመሪያው የማጣሪያ ጨዋታ እና  ግብፅንና ሌሎቹን ግጥሚያዎች በገለልተኛ ሀገር ላይ ስለሚያስተናግዱበት ግጥሚያ

“የአፍሪካ  ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታችንን በሜዳችን ብናደርግ ኖሮ በጣም ደስ ይለን ነበር።  ያንንም ግጥሚያ በድል ብንወጣ ለእኛ ለኢትዮጵያኖች ምን ያህል ደስታን  እንደሚፈጥርልንም እናውቃለን።  ያም ሆኖ ግን በሜዳችን  የምንጫወትበት ነገሮች አልተሳኩልንምና ምንም ማድረግ አይቻልም።  ከማላዊ ጋር የሚኖረንን ጨዋታ ከፈጣሪ እርዳታ ጋር ለማሸነፍ ዝግጁ ነን፤ የመጀመሪያን ግጥሚያ በድል መወጣትም ጥቅሙ ከፍ ያለ ስለሆነ ለጨዋታው ከፍተኛ ትኩረትም ሰጥተነዋል”።

የአፍሪካ ዋንጫ  ሁሉንም  የማጣሪያ ግጥሚያዎች  በገለልተኛ ሀገራት የምናደርግ ከመሆናችን አኳያ  የማለፍ እድላችን የቱን ያህል እንደሆነ

“ለውድድሩ /ለቶርናመንቱ/  ለማለፍ   ዋናው  ነገር ጠንክሮ መስራት ነው።  በስነ-ልቦናውም ጠንካራ መሆን ያስፈልጋል።  በእዚህ ዙሪያ ትምህርት  በሜዳ ላይ  በታክቲክ ዙሪያ   እየተሰጠንም   ይገኛል።  ከእዛ ውጪም በብሄራዊ ቡድን ደረጃም  ተጫውተው  ያለፉ ሰዎች እየመጡ እያስተማሩንም ይገኛል።  ከእዚህ መነሻነትም እኛ  በሜዳችን የምንጫወትበት እድሉ ባይኖረንም  በተቻለን አቅም  ከሜዳችን ውጪ በምናደርጋቸው አጠቃላይ ግጥሚያዎች  ወደ  አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ  በገለልተኛ  ሜዳዎች ግጥሚያዎችን ማድረጋችን  ፈፅሞ  አያሰጋንም፤  ለቶርናመንቱ የምናልፍም ይመስለኛል”።

 

ለአፍሪካ ዋንጫው  ለማለፍ  ከእዚህ ቀደም 31 ዓመታትን በኋላ ላይ ደግሞ 8 ዓመታትን ጠብቀን ነበር፤ አሁንስ ስንት ዓመታትን እንጠብቃለን?

“ያለውን ሁኔታ  በተመለከተ አሁን አንተ ያልከውን  ነገር አሰልጣኛችን ውበቱ አባተ አንስቶታል።  ከእዚህም በመነሳት አሰልጣኙ  በተከታታይ የአፍሪካ ዋንጫዎች የምናልፍበት ሁኔታ እንዲፈጠር ያስቀመጠው ነገር አለና በእዛ መልኩ እንጓዛለን”።

በቤትኪንግ  ፕሪምየር  ሊጉ  እንዳለህ ብቃት እና  ችሎታ  ጥሩ ስም አለህ፤  በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ግን  የጎላ ስም የለህም፤   ከእዚህ በመነሳት የወደፊቱ የዋልያዎቹ ምርጡ  እና ስመኛ ተጨዋች ትሆናለህ?

“ብዬ አስባለሁ። ወደ ዋልያዎቹ አሁን የተቀላቀልኩትም ከአራት ዓመታት በኋላ ነው።  የወደፊቱ ምርጡ ተጨዋች ለመባል  ተስፋ አልቆርጥም።  በክለብ ደረጃ የማሳየውን ብቃት ለሀገሬም መድገም እና መጥቀምም እፈልጋለሁ፤ ለእዛም እንድበቃ ጠንክሬም እሰራለሁ”።

በብሄራዊ  ቡድን ደረጃ  ሀገርህን  በምርጥ ብቃትህ አለማገልገልህ አይቆጭህም?

“የእግር ኳስ ተጨዋች ሆነህ ሁሌም በብሄራዊ ቡድን ውስጥ ብትኖር በጣም ደስ ይልሃል።  ሀገሬን  በእዛው መልኩ  በጥሩ ሁኔታ  ባገለግላትም  ደስ ይለኝ ነበር።  ግን እንደምፈልገው ዕድሉን በሚገባ ስላላገኘሁት ምንም ነገርን ማድረግ አልችልም።  አሁንም ቢሆን ግን  ይህን ዕድል የማገኝበት አማራጭ እድሉ አለኝ።  ይሄን የመጫወት ዕድሉን የማገኝበት በቂ ጊዜም  ስላለኝ  እስከዛው  ድረስ ያለኝ አማራጭ ጠንክሮ እና ጠንክሮ መስራት  እስከሆነ ድረስ   እኔም ልምምዴን ተግቼ እየሰራው  ነው”።

የዋልያዎቹን ማሊያ አጥልቆ መጫወት ምን ያህል ክብር ይሰጣል?

“የእግር ኳስን  በሀገር ውስጥ ደረጃ   ስትጫወት  የእኛ ትልቁ ታርጌታችን  ለብሄራዊ ቡድን ተመርጦ መጫወት መቻል ነው።  ማልያውን ለብሶ መጫወትን  የማይፈልግ ተጨዋች ደግሞ  የለም።  እንደ ሀገር  ሀገርን መወከል እና ሀገርን ማገልገልም ቀላል ነገር አይደለም”።

በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታው ማላዊን  ከገጠማችሁ በኋላ በቀናት ልዩነት ግብፅንም ትገጥማላችሁ። የኢትዮጵያ  የስፖርት አፍቃሪ ከእናንተ ምን ይጠብቅ?

“እኛ ወደዛ ስናመራ 6 ነጥብ ማግኘትን አልመን ነው። ግብፅንም ማሸነፍ እንፈልጋለን”።

በሜዳችን አለመጫወታችን መቻል

“በጣም ያስቆጫል፤ ግን ምን ታደርገዋለህ። በምን ምክንያት እና  ሁኔታ ጨዋታዎቹን  በሜዳችን ልናደርግ ያለመቻላችንም የተሟላ መረጃው እና እውቀቱ ስለሌለኝ ብዙ ነገሮችን ማለትም አልፈልግም።  በሜዳችን አለመጫወታችን  ግን ከምንም በላይ  ያስቆጫል”።

በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ  ግብፆች ከበርካታ ዓመት በኋላ የምድባችን ተፋላሚዎች ሊሆኑ ነው። ዋልያዎቹ ከግብፅ ጋር ሲደለደሉም ይቸገራሉ ይባላል ይሄን በተመለከተ  የምትለው ነገር ካለ?

“ከእነሱ ጋር የሚኖረንን ጨዋታ ከላይም ገልጫለሁ ለማሸነፍ ነው የምንጫወተው።  እኛ ግብፅን  በችሎታዋ  እናከብራታለን እንጂ አንፈራትም።  ባለፈው ጨዋታ  ኮትዲቮርም ትልቅ ቡድን ሆና ነው ያሸነፍናት በዓለም ዋንጫ የተካፈለችም ነበረች። ስለዚህ እነሱንም ለማሸነፍ ነው ወደ ሜዳ የምንገባው”።

በአፍሪካ ዋንጫው  ግብፅን ስትገጥሙ መሀመድ ሳላን የማግኘት ወይንም ደግሞ አብረኸው ፎቶ የመነሳት ፍላጎትህ የቱን ያህል ነው?

“እንደ እኔ  ፍላጎት ጨዋታው ላይ ነው እንጂ ትኩረት የማደርገው  ስለ ሳላ እያሰብኩ ከእሱ ጋር  ፎቶ ግራፍ ስለመነሳትም ሆነ ሌላ ነገርን በፍፁም አላስብም። ከጨዋታው በኋላም ካሸነፍን ደስታዬን እገልፃለው። ካለሸነፍን ደግሞ ያው ከማዘን ውጪ ሌላ ነገርን ፈፅሞ  አላደርግም ምክንያቱም ከእዚህ ቀደምም ቢሆን በአንድ ካምፕ ከእነ  ሳዲዮ ማኔ ጋር  የተገናኘንበትም ሁኔታ ነበርና”።

ከብሄራዊ ቡድን እንውጣና  ወደ ቤትኪንግ ፕሪምየር  ሊጉ እናምራ  ዋንጫውን ቅ/ጊዮርጊስ ወይንስ ፋሲል ከነማ ያነሳል?

“ውድድሩ ገና ነው። አልተጠናቀቀም።  ቡድናችን ከጊዜ በኋላ  ጥሩ  እየሆነ መጥቷል።  ያለፉትን  ስድስት ጨዋታዎችንም አሸንፏል። ባለፉት ሰባት ጨዋታዎች ላይም አልተሸነፈም። ከእዚህ  መነሻነት የ10 እና የ11 የነጥብ ልዩነት የነበረውን ጋብ ስላጠበብነው  እና በእግር ኳስም ምን እንደሚፈጠር ስለማይታወቅ  ዋንጫውን እናነሳለን ብለን ነው እየጠበቅን የምንገኘው”።

ከዓምና  ሻምፒዮናነታችሁ አኳያ   በቅ/ጊዮርጊስ  በሰፊ ነጥብ የመበለጥ  ሁኔታ  ሲያጋጥማችሁ ስሜቱ እንዴት ነበር?

“በእግር ኳስ ጨዋታ ሁሌም የሚፈጠረው ነገር አይታወቅም።  ስህተቶችን እንሰራ ስለነበርም ነው ከእነሱ በነጥቦች ርቀን የነበረው።  አሁን ላይ ግን የተወሰኑ መስተካከል ያለባቸው ነገሮች ነበሩና ያን በማረም ልዩነቱን እያጠበብነው ልንመጣ ችለናል”።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ስንመለከትህ ምርጥ ከሚባሉት ተጨዋቾች መካከል አንዱ ነህ፤   እንደ ራስህ ምልከታስ የሀገሪቱ ምርጡ ተጨዋች ነኝ ብለህ ታስባለህ?

“አላስብም፤ ገናም  ነኝ። ኳሱን  እየተማርኩትም ነው”።

 

ፋሲል ከነማ  አሰልጣኝ ስዩም ከበደን ከሀላፊነት ካነሳ በኋላ በተከታታይ ጨዋታዎች ውጤትን እያስመዘገበ ይገኛል። ቀደም ሲል ላጣቸው ውጤቶች  ችግሩ  የአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ችግር  ወይንስ የእናንተ ተጨዋቾች ችግር

“ቀደም ሲል ላጣነው ውጤት  የአሰልጣኙ ችግር ነው ብዬ አላስብም። ምክንያቱም ሻምፒዮና ስንሆን በስዩም የሀላፊነት ጊዜ ነውና። ያው የውጤት ማጣታችን እግር ኳስ ነው ብዬካለው። የሚፈጠረው ነገር አይታወቅም። ሁሌ ጥሩ ትሆናለህ ማለትም አይደለም።  ውጤት ማጣት የእግር ኳሱ አንዱ አካል ስለሆነ ተቀብለነዋል። ከእዛ ውጪ የእግር ኳስ ተጨዋችም ሆነ አሰልጣኝ አንድ አንድ  ወቅት ላይ ጥሩ የመሆን ሁኔታና ያለመሆንሞ ሁኔታ ስለሚያጋጥማቸው ዋናው የውጤት ማጣት ምክንያት ሊሆን ይችላል ብዬ የማስበው የአሰልጣኝ ሀሳብ  የመስጠት እና የተጨዋቾች ደግሞ ችግሩ የት ጋር ነው ብሎ የመቀበል ድክመት ይመስለኛል”።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P