Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“የሊጉ መሪነትን መነጠቃችን አስከፍቶናል፤ ደጋፊዎቻችን ታገሱን እንክሳችኋለን” ተካልኝ ደጀኔ /ኢት.ቡና/

የኢትዮጵያ ቡናው የግራ መስመር ተከላካይ ተካልኝ ደጀኔ ክለባቸው ጅማ አባጅፋርን በሜዳውና በደጋፊው ፊት አስተናግዶ ሽንፈትን ባስተናገደበት የፕሪምየር ሊጉ የ13ኛ ሳምንት ጨዋታ የሊጉን መሪነት በቅ/ጊዮርጊስ መነጠቃቸው እንዳበሳጨው ገልፆ በቀጣይነት በሚኖራቸው ጨዋታዎች ወደ አሸናፊነት መንፈስ በመመለስ መሪነቱን ዳግም የሚጨብጡበት እድል እንደሚኖራቸው እና ለሻምፒዮናነትም እንደሚጫወቱ አስተያየቱን ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ ሊሰጥ ችሏል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ በሊጉ የ13ኛ ሳምንት ጨዋታው በጅማ አባጅፋር ሲሸነፍ የተመዘገበው ውጤትና በሜዳ ላይ የነበረው የጨዋታ እንቅስቃሴ ደጋፊውን ክፉኛ አበሳጭቶት በክለቡ አሰልጣኝ እና አመራሮች ላይ ተቃውሞውን ያሰማ ሲሆን የቡድኑን ሽንፈት ተንተርሶም ከክለቡ ተጨዋቾች መካከል በተከላካይ ስፍራ ላይ የሚጫወተው ተካልኝ ደጀኔ ኢትዮጵያ ቡና ከጅማ አባ ጅፋር ጋር ባደረገው ጨዋታ ጥሩ ካለመጫወቱ በተጨማሪ ሽንፈትን ማስተናገዱ የሊጉን መሪነት እንዲነጠቅ ስላደረገው በሁላችንም የቡድናችን ተጨዋቾች ላይ የቁጭት ስሜትን ሊፈጥር ችሏል ለደረሰብን ሽንፈትና መሪነቱን መነጠቃችንም የክለቡን ደጋፊዎች ይቅርታ ማለትም እንፈልጋለን ሲል አስተያየቱን አክሎ ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናው ተከላካይ ተካልኝ ደጀኔ በጅማ አባጅፋር ክለብ ሽንፈትን ካስተናገዱበት ጨዋታ በኋላ በክለቡ አቋም ዙሪያና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበንለት ምላሹን እንደሚከተለው ሰጥቷል፤ ተከታተሉት፡፡

በጅማ አባጅፋር ሽንፈትን ስላስተናገዱበት ጨዋታ?

“ከጅማ አባጅፋር ጋር የነበረንን የሜዳችን ላይ ጨዋታ ለማሸነፍ ብንገባም ያን እለት የነበረን የጨዋታ እንቅስቃሴ ደካማ እና ጥሩ ስላልነበር ሽንፈትን ለማስተናገድ ችለናል፤ የእሁድ እለቱ ጨዋታ ቡናን የሚገልፅ አልነበረም፤ ፈፅሞ ጥሩ አልተጫወትንም፤ በጨዋታው በተመዘገበው ውጤትም ሆነ በእንቅስቃሴያችን ሁላችንም የቡድናችን ተጨዋቾች ደስተኞች አልነበርንም፡፡ ደጋፊዎቻችንን በጣም ያስከፋንበት እና ያሳዘንንበትም ቀን ስለነበር ለደጋፊው ይቅርታ መጠየቅን እንፈልጋለን”፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቀጣይ ጨዋታን ከደቡብ ፖሊስ ጋር በዛሬው ዕለት የሚያደርጉ ስለመሆናቸው

“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዛሬ ጨዋታን ከደቡብ ፖሊስ ጋር የምናደርገው ያለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ በጅማ አባጅፋር የደረሰብንን ሽንፈት ወደኋላ ረስተን ነው፤ የዛሬው ተጋጣሚያችን ደቡብ ፖሊስ ምንም እንኳን በደረጃው ሰንጠረዥ በታች ስፍራ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ለጨዋታው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተን ነው ወደሜዳ የምንገባው፤ የዛሬው ጨዋታ ለእኛ በጣም ወሳኝ ነው፤ ወደ አሸናፊነት መንፈስ የግድ መመለስ ስላለብን እና በውጤት ያስከፋናቸውንም ደጋፊዎቻችንን መካስ ስለሚኖርብንም ጨዋታውን አሸንፈን ለመወጣት ዝግጁ ሆነናል”፡፡

የኢትዮጵያ ቡናው ተከላካይ ተመስገን ካስትሮ በእሁዱ ጨዋታ ጉዳትን አስተናግዷል፤ በእሱ ዙሪያ ማለት የምትፈልገው ካለ

“የኢትዮጵያ ቡና የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ተመስገን ካስትሮለክለባችን በሜዳ ላይ በሚሰጠው ግልጋሎት ጠቀሜታው በጣም ከፍተኛ የሆነ ተጨዋች ነው፤ እሱን አሁን ላይ በጉዳት ማጣታችን የሚያጎለን ነገር ቢኖርም ፈጣሪ ቶሎ አሽሎት ወደ ሜዳ ስለሚያስመልሰው ያሉትን ነገሮች በተጋነነ መልኩ መመልከትን ስለማልፈልግ ተመስገን ወደ ሜዳ ቶሎ ተመልሶ የተለመደ ግልጋሎቱን እንደሚሰጠን ሙሉ እምነት ነው ያለኝ”፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ፉክክሩ በአንተ አንደበት ሲገለፅ

“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የእዚህ አመት ውድድርን አሁን ላይ ስመለከተው በርካታ ክለቦች በተቀራራበ ነጥብ ላይ ከመገኘታቸው በተጨማሪ ለዋንጫም እየተፎካከሩ ነውና ጨዋታዎቹን ለየት ባለ እና ከበድ የሚልም ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡በሊግ ውድድሩ በእያንዳንዱ ግጥሚያዎች ላይ ውጤታማ ሆነህ ከሜዳ ካልወጣ ሻምፒዮና መሆን መቻል በጣም ከባድ ነው የሚሆንብህና ለግጥሚያዎቹ ትኩረት ልትሰጥ ይገባሃል”፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ለበርካታ ሳምንታት ከመራችሁ በኋላ አሁን ላይ ለቅዱስ ጊዮርጊስ አስረክበችኋል፤ ይሄ ሲያጋጥማችሁ ምን ስሜት ነው የተፈጠረባችሁ…

“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታችንን ከጅማ አባጅፋር ጋር ስናደርግ ከሽንፈቱ የበለጠ እኛን ያስቆጨን የመሪነቱን ስፍራ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ማስረከባችን ነው፤በጨዋታው መሪነቱን አስቀጥለን እንጓዘለን ብለን ነው እንጂ የጠበቅነው እንነጠቃለን ብለን ፈፅሞ አላሰብንም ነበርና ያ ሊያበሳጨን ችሏል፤ ያም ሆኖ ግን አሁንም መሪነቱን በድጋሚ የምንጨብጥበት ሌሎች እድሎች ስላሉን በቀጣይነት የሚኖሩን ጨዋታዎች ላይ ጠንክረን በመግባት ያን ለማሳካት ከፍተኛ ጥረቶችን እናደርጋለን”

የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋች ሆኖ በቅርቡ ጋብቻውን ስለመፈፀሙ እና ስለነበረው የሰርግ ፕሮግራም ሚዜዎቹስ እነማን ነበሩ

“የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ውስጥ እየተጫወትኩ ባለሁበት የአሁን ሰአት ላይ በቅርቡ የፈፀምኩት የጋብቻ ስነ-ስርአት በጣም ደስ የሚል እና ያማረምሆኖ ያገኘሁት ነው፤በአጠቃላዩ የሰርግ ስነ-ስርአቴም በጣም ነው ደስተኛ የሆንኩት፤ ጋብቻዬን ስፈፅም የእኔ ሚዜዎች የነበሩት የቅርብ ጓደኞቼ እና የእግር ኳስ ተጨዋች የሆነው ሌላኛው ጓደኛዬ ምኞት ደበበ ነበርና የሰርግ ፕሮግራሜን ላደመቁልኝ ሁሉ ምስጋናን ማቅረብ እፈልጋለው”፡፡

በኢትዮጵያ ቡና ውስጥ ስላለው ወቅታዊ አቋሙ እና በቀጣይ ጊዜ ጨዋታዎች ላይ ክለቡን በምን መልኩ ለመጥቀም እንደፈለገ

“የኢትዮጵያ ቡናን ከተቀላቀልኩበት ጊዜ አንስቶ አሁን ላይ ስላለኝ ወቅታዊ አቋም መናገር የምፈልገው ለክለቡ ጥሩ የሆነ ግልጋሎትን ሰጥቻለሁ ብዬ ፈፅሞ አላስብም፤ በቀጣይ ጊዜ ጨዋታዎች ላይ ግን ለቡና ስሜን በጉልህ የማስጠራበትን መልካም እና አበረታች የሚባል ብቃቴን በሜዳ ላይ ለማሳየት ስለምፈልግ በእያንዳንዱ ጨዋታዎች ላይ ጠንክሬ ነው ወደ ሜዳ የምገባው፤ በክለቡ ውስጥ ጥሩ የሆነ ህልሜንም ከክለቡ ጋር እንደማሳካም እርግጠኛ ነኝ”፡፡

በኢትዮጵያ ቡና አቋም ላይ እንደእይታህ ክፍተት ወይንም ደግሞ ጎድሎናል የምትለው ነገር ካለ

“የኢትዮጵያ ቡናን እግር ኳስ ክለብበዘንድሮው የውድድር ዘመን ተሳትፎው ላይ መሪነቱን አጠናክሮ እንዳይቀጥልና ተፎካካሪዎቹንም በነጥብ ጥሏቸው እንዳይሄድ ካደረገው ክፍተት ጎኑና ጉድለቱውስጥ በምክንያትነት መጥቀስ የምፈልገውበአብዛኛዎቹ ጨዋታዎች ላይ ክለቡ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚታወቅበትን ኳስን እንደ ቡድን መስርቶና ተቆጣጥሮ የመጫወት እንቅስቃሴውን አሁን ላይ እያሳየ ባለመሆኑ ነውና ይሄ ብዙ ርቆ እንዳይጓዝ አድርጎታል”፡፡

በመጨረሻ….

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ለማንሳት ገና በርካታ ግጥሚያዎች የሚቀሩ ከመሆኑ አንፃር አሁንም እድሉ አለን፤ ይህን ዋንጫ ለማንሳት እንድንችልም እስከመጨረሻ ጨዋታዎቻችን ድረስ ደጋፊዎቻችን ታግሰውን ከጎናችን ሊሆኑ እና ሊቆሙ ይገባል”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P