ሊግ ስፖርት በቅዳሜ እትሟ
የሊግ ስፖርትን የነገ ጋዜጣ ሲያነቡ የተለያዩ
የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ የሚወዱትን ዘገባዎችን ታነባላችሁ።
ሊግ በዕለተ ቀኗ ምንን ይዛሎት በመቅረብ ታስነብቦት ይሆን?
በሀገር ውስጥ መረጃ የፋሲል ከነማን ክለብ ለዘንድሮ ቤትኪንግ ሻምፒዮንነት እንዲበቃ ካደረጉት ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነውና አይድከሜው ተጨዋች ሽመክት ጉግሳ በቡድናቸው ድል መደሰቱን በመግለፅ “በአቡበከር ኮከብነት ፈፅሞ አልተከፋሁም፤ ሀዝን የነበረው ደስተኛ ያደረገኝ ፋሲል ከነማ ሻምፒዮና ባይሆን ነበር” የሚል አስተያየትንም ሰጥቷል።
ሊግ በሀገር ውስጥ ለኢትዮጵያ 23 ዓመት በታች ቡድን ከተመረጡት ተጨዋቾች መካከል ዘንድሮ በሊጉ ለባህርዳር ከተማ በመጫወት ጥሩ እንቅስቃሴን ካሳዩት ተጨዋቾች መካከል አንዱ ከሆነው ሰለሞን ወዴሳ ጋርም ቆይታ አላት። ሊግ አታምልጦት።
ሊግ ስፖርት በባህርማዶ ዘገባዋም ስለ አውሮፓ ሊጎች የተጨዋቾችና የአሰልጣኞች ዝውውርን አስመልክቶና ሌሎች መረጃዎችንም ትሰጦታለች።