Google search engine

የሊግ ጉዞ ቀጥሏል……   በየሳምንቱ ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃው ሊግ ጋዜጣ  በነገው ዕለት ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችን አካትታ እጅዎ ትገባለች….

 

በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ  የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ደረጄ አረጋ እንግዳችን ናቸው…… የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት መምራት ከጀመሩ አመት አልፏቸዋል…. ፌዴሬሽኑ ከከተማው ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ  የበጀት ድጋፍ ባይደረግለትም 134 ክለቦችን ውድድር   የመሩበትን በሳቸው አገላለጽ ” አስማት” ያሉበትን አመት አሳልፈዋል። ከሊግ ጋዜጣ ባልደረባው ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ ያደረጉት ፕሬዝዳንቱ  “ቋሚ በጀት  በሌለበትና  ዕዳ ውስጥ ሆኖ በተረከብነው  ፌዴሬሽን  134 ክለቦችን ማወዳደር  አስማት ነው” ሲሉ ገልጸዋል… ፕሬዝዳንቱ ከወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ፣ ስለ አመታዊ ውድድሩ፣ ስለ ሸገር ሰመር ካፕ፣ በግላቸው ስላሰሩት የሁለት አቅመ ደካሞች ቤት፣  እግርኳሱ ላይ ማየት ስለማይፈልጉትና ሌሎች ጉዳዮቸ ምላሻቸውን ሰጥተዋል…ቃለ ምልልሱነን ይዘናል…

…….በውጪ ዘገባ ደግሞ:…..

* በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት  ነገ ይቀጥላል….ነገ ምሽት 1.30 ላይ የሚካሄደው የቶተንሃም ሆትስፐርና ሊቨርፑል ጨዋታ ትልቁ ፍልሚያ ተብሏል…
ቶተንሃሞች ብርታቱን መልሶ ያገኘውን የክሎፕ ቡድን  የሆነውን ሊቨርፑልን በሚያስተናግዱበት ጨዋታ
የቀድሞው የሌስተር አማካይ ማዲሰን በራስ መተማመኑን መልሶ አግኝቷል የቀዮቹ  ኡሩጓዊው ኑኔዥ ከፍ ባለ ብቃት መጫወት ጀምሯል  እየተባለ ባለበት የሚደረግ ጨዋታ መሆኑ አጓጊ አድርጎታል…በዚህ ላይ ሰፋ ያለ ዘገባ ይዘናል…

**** በአሜሪካ ሜጀር ሊግ አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲን ያልያዘው ኢንተር ሚያሚ  ዋንጫ አጥቷል……በተቃራኒው ደግሞ  ክርስቲያኖ ሮናልዶ በመካከለኛው ምስራቅ የራሱን ጡብ አኑሯል…በሁለቱ ዙሪያ መረጃዎቹን አጠናክረናል….

**** “ግላዲያተሩ” አልናፈቆትም..? እሺስ  “ዋዛ” ንስ አላስታወሱትም..? በተለይ ዩናይትድ ደጋፊ ከሆኑ ግን አይረሱትም … የቅጽሎቹ ባለቤት የሆነውን የዌይን ማርክ ሩኒን ትውስታ ይዘንልዎታል…

 

እና ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም  ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…

….ቅዳሜና እሁድዎ  የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ….

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P