በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ የባህርዳር ከተማ አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው እንግዳችን ነው… አሰልጣኙ በፕሪሚየር ሊጉ ባህርዳር ከተማን ጠንካራ ተፋላሚ አድርጎታል…. በአመቱ ውድድር 2ኛ ሆኖ በመጨረስ በኮንፌዴሬሽን ካፕ ተሳታፊ አድርገውት ወደ ምድብ ድልድል ሳይገባ ቀርቷል…ያም ሆኖ አሰልጣኙ በዘንድሮ የውድድር አመት ቡድኑ ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚሆን እምነቱ እንዳለው ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ተናግሯል… አሰልጣኙ ወደ ወደ ቱኒዝያ ስለተጓዙት ተጨዋቾችና የልኡካን ቡድን፣ በቱኒዝ ስለገጠማቸው ፈተና ፣ ከአራቱ የኮንፌዴሬሽን ካፕ ጨዋታዎች ስላገኙት ትምህርት፣ በኢትዮጵያ መድን ስለደረሰባቸው ሽንፈትና እሁድ ከመቻል ጋር ስላላቸው ጨዋታ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ምላሽ ሰጥቷል… “ወደ ቱኒዚያ የሄዱት 18ቱ ተጨዋቾች እኔ መርጫቸው ነው ስለሌሎቹ ተጓዦች ግን የክለቡ ቦርድና ስራ አስኪያጅን መጠየቅ ይቻላል” ያለው አሰልጣኝ ደግአረገ “አገራችን ኢትዮጵያ ሰላም ሆና ደጋፊዎቹ በነጻነት የሚደግፉበት አመት እንዲሆን እመኛለሁ” ሲል። አስተያየቱን ሰጥቷል…. ከሊግ ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ ይዘናል…
…….በውጪ ዘገባ ደግሞ:…..
**** ብራዚላዊው ጋብርኤል ማርቴኔሊ ማን.ሲቲ ላይ ባስቆጠራት ግብ አርሰናሎች 8 አመት የሞላው ጥቁር ታሪካቸው መቆሚያ ተበጅቶለታል ….. የማርቴኔሊ መንገዶች በሚል በተጨዋቹ ዙሪያ የምንላችሁ አለ….
**** ሉዊስ ዲያዝ ኳሷን ለዳርዊን ኑኔዝ አቀበለው ኡሯጓዊው ለሞ.ሳላህ ሰጠው ጎልልል… ስለ ሊቨርፑሎች አስፈሪ የአጥቂ መስመር ያዘጋጀነው ዘገባም አለን…..
**** ኬቨን ደብሮይነ በጉዳት ከማን.ሲቲ የመሃል ክፍል ከታጣ ሰነባብቷል …ቤልጂየማዊው ላይ የነበረውን ሸክም ፖርቱጋላዊው በርናርዶ ሲልቫ ያቀለለው ይመስላል …በዚህ ዙሪያ የሚያጠነጥን መረጃን አካተናል….
**** ቤልጂየማዊው ኮከብ ኤደን ሃዛርድ በ32 አመቱ እግርኳስን ተሰናብቷል….የላቀ ተሰጥኦ ስለነበረው ሰነፉ ተጨዋች ኤደን ሃዛርድ ያዘጋጀነው መረጃም ተካቶበታል…
**** 40 አመት የአንድ ጎልማሳ ዕድሜ ነው…. በነዚህ 40 አመታት ውስጥ ማን.ዩናይትድና ባርሴሎና ቀልብ የሳበ ፍልሚያዎች አድርገዋል..ሁለቱ ክለቦች በ3 የሻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ፣ በ1 የግማሽ ፍጻሜና በ2 የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ላይ ተፋልመዋል …. የሁለቱን ክለቦች ታሪካዊ ፍልሚያ አካተናል…
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ….