በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ የመቻሉ የተከላካይ መስመር ማስፈራሪያ አስቻለው ታመነ እንግዳችን ነው …በመሃል ተከላካይነት ሚና አሁንም ለክለቡም ሆነ ለዋሊያዎቹ አይተኬ ከሆኑት ተጨዋቾች መሃል አንዱ ነው የትኛውም አሰልጣኝ የሚፈልገው አይነት ተከላካይ ነው ሲሉ የሚያቁት ያሞግሱታል …… ተጨዋቹ ከሊጉ ባልደረባ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ ስለ አዲሱ ክለቡ፣ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስና ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ፣ መቻል የዋንጫ ተፎካካሪ ስለመሆኑና ሌሎች ጥያቄዎች ዙሪያ ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሹን ሰጥቷል።
“11 ለ 11 ሆነን ወደ ሜዳ እስከገባን ድረስ ትንሽ ትልቅ የምለው ቡድን የለም” የሚለው አስቻለው “ቅዱስ ጊዮርጊስም ሆነ ፋሲል ከነማ እያለሁ የደጋፊ ጫና አልነበረብኝም ጀማሪ ተጨዋችም አይደለሁም” ሲል ተናግሯል….ቃለምልልሱን ይዘናል….
**** በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በደመወዝ ይከፈለን ጥያቄ የተወጠረው ወልቂጤ ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር 0ለ0 ተለያይቷል…ውስጣዊና ውጫዊ ጫና ያጋጠመው ክለቡ ከአክሲዮን ማህበሩ ሊቀበል የነበረው ገንዘብ ጉዳዩን ወደ በመደበኛ ፍርድ ቤት በወሰደው የቀድሞ ተጨዋች ምክንያት ታግዷል….
የተጨዋቹን ማንነት የታገደው ገንዘብ ብዛትን በነገው ዕትማችን አካተናል……
…….በውጪ ዘገባ ደግሞ:…..
**** በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የነገ ምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ በስታምፎርድ ብሪጅ ቼልሲን ከአርሰናል ያገናኛል
መድፈኞቹ በሰማያዊዎቹ ቁስል ጨው ይነሰንሱ ይሆን ..? በጨዋታው ዙሪያ መረጃ አለን ….
**** በነገው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሜርሲሳይዱ ደርቢ ሊቨርፑልን ከኤቨርተን ያፋጥጣል…. የሜርሲሳይድ ደርቢ እውነታዎችን አካተናል…..
**** የማን .ሲቲው የግብ ቀበኛ ኧርሊንግ ሃላንድ የጎል አስቆጣሪነቱ ቀዝቅዟል የሚሉ ወገኖች አሉ ….የሃላንድ አምና እና ዘንድሮን የሚገልጽ መረጃንም ይዘናል….
**** ቀዮቹ ራሳቸውን የማጠናከርና የራስ መልሶ ግንባታን ተያይዘዋል ….የሊቨርፑል ቀጣዩ ስፖርት ዳይሬክተር ማነውና በሚለውና በቡድን ግንባታቸው ዙሪያ የምንላችሁ አለ…….
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ….