በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ ዘገባችን ከሁለት አመት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን በደርቢ ጨዋታ ረቷል…ደጋፊዎቹን ለከፍተኛ ደስታ ያበቃቸው ደግሞ እንግዳችን ነው … በቀድሞ አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ምክትልነት መጥቶ በአሀኑ ወቅት ቡናማዎችን በዋና አሰልጣኝነት እየመራ ያለው አሰልጣኝ ነጻነት ክብሬ
/ማሜ ቦረና/ እንግዳችን ነው …..ከከፍተኛ ማግባባት
በኋላ ቃለ ምልልሱን የፈቀደው አሰልጣኙ “አሁን ያለንበት 7ኛ ደረጃ እኛን አይመጥነንም ወደላይ ከፍ ለማለት ለኛ አልረፈደም” ሲል ተናግሯል። ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ ያደረገው አሰልጣኝ ነጻነት “በጣም የምጠላው ቋንቋና የማልጠራበት ስም ቢኖር ሰርሳሪ የሚለውን ነው” ሲል አስረድቷል። ቃለምልልሱን ይዘናል…
…..በውጪ ዘገባ ደግሞ….
** ሊቨርፑልና አርሰናል በአንፊልድ ያደረጉትን ጨዋታ ላየ የኢምሬትሱን የመልስ ጨዋታ ቢጓጓበት አይገርምም በሊጉ ከሚገናኙበት የመልስ ጨዋታ በፊት ግን በኤፍ ኤ ካፑ እሁድ ምሽት በኢምሬትስ ይገናኛሉ… አርሰናል በነጩ ማሊያ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ በሚያደርገው ጨዋታ ዙሪያ መረጃ ይዘናል….
** 2023 ተጠናቆ 2024 ተጀምሯል…ለዛሬ የ2023
አበይት እግርኳሳዊ ጉዳዮችን መለስ ብለን ቃኝተናል…
** ጥር ወር የዝውውር መስኮት ከተከፈተ አምስተኛ ቀን ላይ እንገኛለን … ለዛሬው ትኩረት ሊሰጣቸው ስለሚገባ ዝውውሮችና አስጀራሚ የዝውውር መስኮቱ እውነታዎች መረጃም ይዘናል…
** ኬቨን ደብሮይነ ከጉዳት የተመለሰለት የፔፕ ጋርዲዮላው ማን.ሲቲ ይበልጥኑ አስፈሪ ሆኗል…ዩናይትድ በተቃራኒው የሽግግር ቡድን መስሎ ይሆን ..? በሁለቱ የማንቹሪያን ተፋላሚዎች ዙሪያ የምንላችሁ አለ…
** እንግሊዛዊው ራሂም ስተርሊንግ ጥንካሬ ለቸልሲ ውጤት ወሳኝ ሆኗል … አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖሺቲኖም ይህን የተረዱት ይመስላል …በዚህ ዙሪያ የተጠናከረ መረጃ ይዘናል
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…