በየሳምንቱ ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃው ሊግ ጋዜጣ በነገው ዕለት ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችን አካትታ እጅዎ ትገባለች….
በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ ዘገባችን የቅጣት ምት ስፔሻሊስት፣ ጣጣቸውን የጨረሱ ኳሶችን ለአጥቂ የሚያቀብል፣ ለተጋጣሚ ስጋት የሆኑ እግሮች ባለቤት፣ የምርጥ ድሪብል የማራኪ ጎል ባለቤት….ማነው ቢባሉ ለመልሱ ይቸገራሉ ተብሎ አይጠበቅም ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት ባገኘው የፕሮፌሽናልነት ዕድል አግኝቶ ወደ አሜሪካ ጉዞ ለመጀመር ከተዘጋጀው የፋሲል ከነማውና የዋሊያዎቹ ኮከብ ሱራፌል ዳኛቸው ውጪ የለምና ሲሉ ብዙዎች ይመሰክራሉ። ተጨዋቹና ጋዜጠኛው ሲገናኙ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በሆነበት ቃለምልልስ “ኳሷን ከእግራችን የሚነጥቁን ተከላካዮች ብቻ ሳይሆኑ ሜዳው ጭምር ነው” ያለውም ሱራፌል “አንድ ሃያል ቡድን በብዙ ነጥብ እየራቀ ሻምፒዮን የሚሆንበት ጊዜ ያበቃ ይመስለኛል” በማለት ከጋዜጠኛ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቃለምልልስ ላይ ተናግሯል….ቃለ ምልልሱን ይዘናል….
የአፍሪካ ተጨዋቾችን በኢትዮጵያ ደመወዝ ከተከለከሉ ፊፋ አስገድዶ ያስከፍልላቸዋልና በንጽጽር ከኢትዮጵያዊያን የተሻለ መብት አላቸው…. አሁን ግን ፌዴሬሽኑ በያዘው ጠንካራ አቋም ኢትዮጵያዊያኑ ተጨዋቾች መብታቸውም የሚከበር ይመስላል… የሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ያዘጋጀውና በዚህ ዙሪያ የሚያጠነጥን ዘገባ ተካቶበታል…..
….በውጪ ዘገባ ደግሞ….
የማንቹሪያኑ ደርቢ ከነገ በስቲያ እሁድ ምሽት በኢትሃድ
ማን.ሲቲንና ማን.ዩናይትድን ያገናኛል…. ፔፕ ጋርዲዮላ የዋንጫ ፉክክሩ ላይ ለመቆየት ቴንሃግ ደግሞ ለህልውና በሚያደርጉት ፍጥጫ ዙሪያ የሚያጠነጥን መረጃ ይዘናል….
ስለ መድፈኞቹ ኮከብና ልዩነት ፈጣሪ ቡካዮ ሳካ ያዘጋጀነው ዘገባም አለ….
ቸልሲን ረተው የካራባዎ ካፕን ያሸነፉትን የየርገን ክሎፕ ህጻናትን የሚያስተዋውቅ መረጃንም አካተናል…
የሮማና አብራሞቪችን ታሪክ ለማስረሳት እየጣሩ ስላሉት የቸልሲ ባለቤቶች እቅድ የምንላችሁ አለ…
ማን.ዩናይትድ ደካማ አቋም እያሳየ ነው ቢባልም አጥቂው ራስመስ ሀይሉንድ ትልቋ ለውጥና እንዳመጣ እየተነገረ ነው በዚህ ዙሪያ መረጃ ይዘናል…..
አርሰናል በአውሮፓ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ በፖርቶ የደረሰበት ሽንፈት ከማያሰጋቸው ተጨዋቾች መሃል አንዱ ዴክላን ራይስ ነው….የለንደን እግርኳስ ማህበር የአመቱ ኮከብ ዴክላን ራይስ ” የፖርቶ ጨዋታ የተጠናቀቀው የመጀመሪያው አጋማሽ ነው” በማለት ቀሪ ጨዋታው ወሳኝ መሆኑን ተናግሯል….
“አዝኛለሁ ደንግጫለሁ ለቤ ተሰብሯል…” ፈረንሳዊው ፖል ፖግባ አራት አመት ከታገደ በኋላ የተናገረው ነው.. በዚህ ዙሪያ የሚያጠነጥን መረጃ ይዘናል…
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…