****በነገው እትም በሀገር ውስጥ ዘገባዋ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ከሆኑት አቶ ባህሩ ጥላሁን ጋር ቆይታ አድርጋለች…ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ ያደረጉት ዋና ስራ አስፈጸሚው ” 2016 በስፖርቱ ዘርፍ የተሻለ ስኬት እንዲገጥም ተመኝተው “በአዲሱ አመት አንዱ ሌላኛውን ለመጥለፍ የሚደረጉ ተንኮሎች ሊወገዱ ይገባል” ሲሉ የሚመኙትን ተናግረዋል….
** ባለፉት 3 ወራት ዋሊያዎቹን የመሩት አሰልጣኞች ኮንትራት ተጠናቋል …በዚህ ዙሪያ የሚያጠነጥን መረጃ አካተናል….
በውጪ ዘገባ ደግሞ:-
**** ማርኮ ቬራቲ ጣሊያናዊው ኮከብ ወደ ኳታር አቅንቷል….. ጣሊያናዊው ከእርሱ ትውልድ ምርጥ አማካዮች አንዱ ነው ….በዝውውሩ ዙሪያ የሚያጠነጥን ዘገባ ተካቷል…
**** በማን.ዩናይትዱ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሃግና እንግሊዛዊው ጄደን ሳንቾ መሃል እሳት ገብቷል… በሳንቾ እና ቴንሃግ ፍጥጫ ዙሪያ የምንለው አለ…..
**** ዳርዊን ኑኔዝ ኡራጓዊው ኮከብ እድል አባካኝነቱን ይቀርፍ ይሆን …? በዚህ ዙሪያ ያዘጋጀነው ዘገባ አለ…..
* የፖል ፖግባ ፀሀይ ልትጠልቅ ይሆን…? አማካዩ በዶፒንግ ጥሰት እገዳ ተጥሎበታል… በፈረንሳዊው የአሁነኑ እውነታ ዙሪያ መረጃዎችን አካተናል…
እና ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ….