Google search engine

….የሊግ ጉዞ ቀጥሏል …..   በየሳምንቱ ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃው ሊግ ጋዜጣ  በነገው ዕለት ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችን አካትታ እጅዎ ትገባለች….

በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ ዘገባችን በመቻል ድል  የሚደሰተውን ሽንፈቱ  ከእግርኳስ የዘለለ ስሜት ተሰምቶት የሚከፋውን  ምንይሉ  ወንድሙን እንግዳችን አድርገነዋል ….በ2007 በወጣት ቡድን ተሰላፊነቱ ከመቻል ጋር የተጀመረው ግንኙነቱ  አሁንም ዘልቋል… ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ ያደረገው ምንይሉ መቻል የሚወከለው እንደ ክለብ ሳይሆን እንደ ሀገር ነው” ብሏል…የሊጉ የዋንጫ እድል ለሁሉም ክፍት ነው የሚለው ምንይሉ “ለቅዱስ ጊዮርጊስም ይሁን ለአምበሪቾ እኩል ነው  የምንዘጋጀው ” ሲል ተናግሯል ….ቃለምልልሱን ይዘናል….

…ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምበሪቾ ዱራሜ ላይ የግብ መአት አውርዶ የሊጉን መሪነት ተረክቧል…መሪነቱን ለማስመለስ ደግሞ መቻልና ቅዱስ ጊዮርጊስ ነገ ይጫወታሑ …በጨዋታው ዙሪያ የምንለው አለ ….

 

*……በውጪ ዘገባ ደግሞ ………

 

*….በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የላንክሼየር ደርቢ እሁድ ይካሄዳል….ኦልድትራፎርድ ላይ ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ማን.ዩናይትድን ይፋለማል …ቀያይ ሰይጣናቱ የክሎፕን ቡድን  ጉዞ ያደናቅፉ ይሆን..? በዚህ ዙሪያ ዘገባዎችን አካተናል…..

*……ስለማይበገሩትና የመከላከልን ጥበብ ስለተላበሱት መድፈኞች እንነግራችኋለን….ማንነቱን በቀረጹ ቦታዎችና ሰዎች አንደበት ጋብርኤል ማርቲኔሊ ምን ይመስላል..? ስለመድፈኞቹና የማርቴኒሊ መንገድ የምንላችሁ አለ…

*….የሊቨርፑሉ አሌክሲስ ማክሊስተር ተጽዕኖ በአንፊልድ እየታየ ነው ስለዚህ ኮከብ አርጀንቲናዊ የሚገልጹ መረጃዎችን ይዘናል…..

*….ከታላላቆቹ ጋር በሚያሰልፈው ብቃቱ የደመቀውና ቸልሲን የታደገው ወጣቱ  ኮል ፓልመር  የሚገልጹ መረጃዎችን ይዘናል….

*… የእንግሊዛዊው ኮከብ ዴቪድ ቤካም አነጋጋሪ  ገጠመኞችንም  አካተናል….

….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል …

ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም  ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ  ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…

….ቅዳሜና እሁድዎ  የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this: