በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ የተወለድኩበት አካባቢ እያለሁ ኳስ ያስጀመረኝ አሰልጣኝ ነበር ኢያሱ ቡናሬ
/ካምፓላ/ ይባላል…”እግርኳስ መጫወት ብፈልግም ጎበዝ ተጨዋች ሆኜ አሁን የደረስኩበት ደረጃ እደርሳለሁ ብዬ አላስብም ነበር ያኔ ግን አቅም አለህ መጫወት አለብህ ትልቅ ደረጃ ትደርሳለህ ብሎ ራሴን ሳላምን እኔን ያመነና እየያዘኝ እየሄደ ኳስ ያስቀጠለኝ አሰልጣኝ ነው በዚህ አጋጣሚ አመሰግነዋለሁ” የሚለው እንግዳችን የሀዋሳ ከተማ የመሃል ተከላካይ ሚሊዮን ስለምን ነው … ሚሊዮን ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ
በባህርዳር ከተማ ስለተሸነፉበት ጨዋታና በወቅቱ ስለተፈጠረው ግርግር ሲናገር “በአገሪቱ ትልቅ ሊግ ላይ ተጨዋች ሲያመናጭቅህ ውጤት የምትቀይር ከሆነ አስቸጋሪ ነው” በማለት ዳኛውን ተቃውሟል…የመሃል ተከላካዩ “የዳኛውን ውሳኔ የቀየረው የባህርዳር ከተማ ተጨዋቾች ጫና እንጂ ረዳቱ አይደለም” በማለት ባደረገው ቃለምልልስ ላይ አብራርቷል….ቃለ ምልልሱን ይዘናል ……
……በውጪ ዘገባ ደግሞ:…..
* ከነገ በስቲያ እሁድ ምሽት የላንክሻየር ደርቢ አንፊልድ ላይ በሊጉ መሪ ሊቨርፑልና ማን.ዩናይትድ መሃል ይከሰታል… መላው አለም በሚከታተለው ጨዋታ የየርገን ክሎፑ ቡድን የኤሪክ ቴንሀግ ቡድን ላይ መከራ ያበዛ ይሆን….? መረጃውን ይዘናል……
* ስፔናዊው አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ከአስቶንቪላ ጋር አስገራሚ ጉዞ እያደረጉ ነው የአሰልጣኙ ተጽዕኖ የገነነበትን የሚድላንዱ ክለብ አስቶን ቪላን ጉዞ ዳሰነዋል…..
* አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖሺቲኖ ሰማያዊያኑ ቸልሲዎችን አሸናፊ ማድረግ ተስኗቸዋል …ስለ ቸልሲ እንቆቅልሽ የምንላችሁ አለ….
* በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቀዳሚዎቹ አማካዮች ኬቨን ደብሩይነና ማርቲን ኦዴጋርድ ናቸው በሚል ብዙዎች ይስማማሉ….ስለሚለያየው የሁለቱ የተለያየ የአጨዋወት ዘይቤና አካሄድ የምንላችሁ አለ…
.
* ኒውዮርክ አሜሪካ ላይ የዓለም ዋንጫው አሸናፊ የሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ ማሊያዎች ለጨረታ ቀረቡ … ስንት ይሸጥ..? እርስዎስ ስንት ይገምታሉ..? 6.1 ሚሊዮን ስለተሸጡት የሜሲ ማሊያዎች የምንሎት አለ…..
*
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ….