በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ የእግርኳስ ጅማሬዬ በሻሸመኔ ከተማ ነው በዚህ ክለብ ውስጥ በግብ ጠባቂነት አቤል ማሞን እያየሁ ልምዱን እየቀሰምኩ ነው ያደኩት ክለቡን የለቀቅነውም በተመሳሳይ ጊዜ ነው ሲል ይናገራል… ሻሸመኔ የተጀመረው የተጨዋችነት ዘመኑ በአርሲ ነገሌ ቀጥሎ የቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የአዲስ አበባን ከተማና የድሬዳዋ ከተማን በር እንዲጠብቅም አስችሎታል እንግዳችን ፍሬው ጌታሁንን …”ጅማ አባጅፋር ባደገበት አመት የሰራውን ዋንጫ የማንሳት ታሪክ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዳግም ይተገበራል” ያለው ግብ ጠባቂው ፍሬው ጌታሁን ” ኢንተ. አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩ ባጫወተኝ ጨዋታ በሙሉ ቀይ ካርድ አይቻለሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ግን ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ስጫወት ቀይ ካርድ ሳይሰጠኝ በመውጣቱ ገርሞኛል.” ሲልም ተናግሯል። እንግዳችን በከፍተኛ የራስ መተማመን ስለተገነባው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እቅድ፣ ስለ ግብ ጠባቂነት ጫና ፣ ስለ ፕሪሚየር ሊጉ፣ ስለ አርቢትሮችና እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሹን ሰጥቷል….ቃለምልልሱን ይዘናል..
……በውጪ ዘገባ ደግሞ:…..
* ነገ ምሽት አንፊልድ ላይ በሊጉ መሪ አርሰናልና ተከታዩ ሊቨርፑል መሃል ታላቅ ፍልሚያ ይከሰታል… መላው አለም በሚከታተለው ጨዋታ ሊጉን የሚመሩት የሚካኤል አርቴታ ልጆች መሪነታቸውን ወደ 4 ነጥብ ከፍ ለማድረግ የየርገን ክሎፑ ስብስብም በሜዳው አርሰናልን አሸንፎ በ2 ነጥብም ልዩነት መሪነቱን ለመረከብ የሚያደርጉት ትንቅንቅ ተጠባቂ ሆኗል….መረጃውን ይዘናል……
* የአውሮፓ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎማለፉ ድልድል ሰሞኑን ይፋ ሆኗል…የምድብ ድልድሉ የተዳሰሰበትን መረጃ ይዘናል…
*የሊቨርፑሉ ኮከብ አሌክሳንደር አርኖልድ ከሜዳ ውጪ ያለውን ህይወቱን እንዲሁም የአርሰናሉ ጆርጂንሆ በውጣ ውረድ የተሞላ ህይወቱን የሚዳስስ ዘገባ ይዘናል..
*ስለ ባየር ሊቨርኩዘኑ አዲሱ መሪ የቀድሞ የመድፈኞቹ ኮከብ ግራኒት ዣካ የምንላችሁ አለ….
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ….