Google search engine

…..የሊግ ጉዞ ቀጥሏል …..   በየሳምንቱ ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃው ሊግ ጋዜጣ  በነገው ዕለት ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችን አካትታ እጅዎ ትገባለች….

 

በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ ዘገባችን ሲዳማ ቡና ከተከታታይ ደካማ አቋሙ የተመለሰ ይመስላል …የክለቡ አመራሮች አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው /ሞውሪንሆ/ ካስፈረሙ  በኋላ ክለቡ በተከታታይ እያሸነፈ ነው በተለይ ባህርዳር ከተማን የመሰለ ጠንካራ ክለብ ማሸነፉ ትኩረት ስቧል…በ12ኛ ሳምንት መርሃግብር  ነገ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ከአምበሪቾ ዱራሜ ጋር  ጨዋታ ያለባቸው አሰልጣኙ ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበራቸው ቆይታ “የፈጠረውን ጌታ አይሆንም  ብሎ የሰቀለ ሰው ባለበት  ምድር ላይ ኖሬ ሁሉም ይወደኛል ማለት ይከብዳል” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ቃለ ምልልሱን ይዘናል….

*…. ታሪክ አዋቂውና  እውቁ ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ
/ሊብሮ/ ዕልፈት መላው ኢትዮጵያዊያንን አስደንግጧል…
መታመሙ ሳይሰማ ሞቱ  ስለተነገረለት የጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ  ህልፈት  ዙሪያ ዘገባ ይዘናል….

….በውጪ ዘገባ ደግሞ….

** ቢቢሲ ሰሞኑን  ካወጣው  ዶክመንተሪ የተቀነጨበና የጋርዲዮላ ጉዞ ላይ ያነጣጠረ መረጃ ይዘናል……

**  የታራንግ አናብስት ሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን ስኬት  እንዲሁም የኦናና እና የካሜሩን እንቆቅልሽ ዙሪያ  የምንላችሁ አለ…

**  የስፖርቱ ውበት ስለሆነው  የእግርኳሱ ጠቢባን ሮናልዲንሆ ጎቾ  ዲ አሲስ ሞሪየራና ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ ወዳጅነት ዙሪያ መረጃ ይዘናል…

** ከአውሮፓ  ወደሳኡዲ የሄዱ ተጨዋቾች ወደ መጡበት ተመልሰዋል …ሳኡዲ ለምን አልተማመነችባቸውም …? በዚህ ላይ መረጃ ይዘናል….

**  ስለተቀዛቀዘው  የጥር ወር  የተጨዋቾች የዝውውር ገበያ መረጃዎችን  ይዘናል….

**  ፖርቱጋላዊው ጆዜ ሞውሪንሆ ፊሊክስ ሳንታናን ያሰናበተው የጣሊያኑ ሮማ  የክለቡን ኮከብ ዳንኤል  ደ.ሮሲ ሾሟል…በሹም ሽሩ  ዙሪያ የምንላችሁ አለ…

….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …

ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም  ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ  ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…

….ቅዳሜና እሁድዎ  የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this: