በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ ዘገባችን የባህርዳር ከተማው ፍጹም ጥላሁን እንግዳችን ነው…በክለብ ደረጃ የመጀመሪያ ማሊያ ያደረገው የቅዱስ ጊዮርጊስ ከ17 አመት በታች ቡድንን በመቀላቀል ነው …. ከታዳጊዎቹ ፈረሰኞች እስከ ባህርዳር ከተማ ድረስ ስኬታማ የውጤት ጊዜ ያሳለፈው ተጨዋቹ ” እናት ከሌላው ጋር እንደማትወዳደር ሁሉ ሀገርህም ከምንም ነገር ጋር አትነጻጸርም” ሲል ተናግሯል። ባለፈው ሳምንት ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ ያደረገው ተጨዋቹ “ቡድንህ ተሸነፈም አሸነፍም ዝም ካልክ ዝምታው ራስወዳድነት ይሆናል ” በማለት አስረድቷል።
ማስታወሻ:-
/ተጨዋቹ ለሊግ ቃለምልልሱን የሰጠው ባለፈው ሳምንት ባህርዳር ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ከመጫወቱ 3 ቀናት በፊት ማክሰኞ ምሽት ላይ ነው…ማተሚያ ቤት በተፈጠረ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ሊግ ባለፈው ሳምንት ባለመውጣቷ ቃለምልልሱ ወደ ዛሬ የዞረ መሆኑን ታሳቢ እንዲደረግ ክቡራን አንባቢዎቻችንን ለማስታወስ እንወዳለን…7
*….. “ዋናው” የተሰኘው ሃገርበቀል የትጥቅ አምራች ኩባንያ የላይቤሪያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆነችውና በዚህም የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊት የተሰኘችው ኢንስትራክተር ሰላም ዘርዓይን ለቀጣዮቹ 3 አመታት የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መርጧታል.. በካፒታል ሆቴል የተካሄደውን ፕሮግራም አካተነዋል…..
….. ከውጪ ዘገባ ደግሞ…..
*……. አርሰናል ሊቨርፑልን ካሸነፈበት መንገድ በላይ ትኩረት የሳበው የአሰልጣኙ ሚካኤል አርቴታና ተጨዋቾቹ የደስታ አገላለጽ ላይ ነው ድጋፍም ተቃውሞም የገጠመው አርቴታ ግን ትችት ሳይሆን ውዳሴ ይገባዋል እየተባለ ነው …መረጃዎችን አካተናል….
*…..በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማን.ሲቲ ከቸልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረት ስቧል…የማውሪሲዮ ፖሺቲኖ ቡድን የሚፈተንበት ጨዋታ ነው በተባለው የኢትሃዱ ፍልሚያያ ዙሪያ የምንላችሁ አለ…
*……የማን.ዩናይትዱ አለቃ ኤሪክ ቴንሃግ በመጨረሻም ቡድን ገንብተው ይሆን..? በዚህ ዙሪያም የምንላችሁ አለ
*….የማን.ሲቲው ግብ ጠባቂ ኤደርሰን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ቃለ ምልልስ ሰጥቷል…የክለቡ የመሃል ሜዳ ታጋይ ሮድሪ ለአንድ አመት ሙሉ አልተሸነፈም ቢባሉስ ያምናሉ…? ሁለቱንም የሲቲ ኮከቦች የሚመለከተውን ዘገባ ይዘናል…
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…