በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ ዘገባችን በተጫወተበት ክለብ …. አምበል ሆኖ ዋንጫ ባነሳበት አሰልጣኝ ሆኖ መሾም ጥቂቶች የሚያገኙት እድል ነው…ይህን ዕድል ካገኙ ዕድለኞች መሃል ደግሞ አንዱ ኮማንደር ሽመልስ አበበ ይገኝበታል…ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ ያያደረጉት አሰልጣኙ ስለ አዲሱ የድረዳዋ ስታዲየም ብቃት ደጋግመው አንስተዋል….” አምና የድሬን ስታዲየም ሲተቹ የነበሩ ወገኖች አሁን አለማመስገናቸው ገርሞኛል” ሲሉ የተናገሩት አሰልጣኙ ” እንደ አሰልጣኝና ተጨዋች ዳኞች ሊሳሳቱ ስለሚችሉ ማጋነን የለብንም” ሲሉ አስረድተዋል….ቃለምልልሱን አካተናል….
*……መቻልና የሊግ ክሚቴው የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ተፋጠዋል… የውድድር ኮሚቴው ውሳኔ ሆን ተብሎ መቻሎችን ጫና ውስጥ ለመክተት የተደረገ መሆኑን የሚገልጸው ክለቡ ለፌዴሬሽኑ አቤት ብሏል..በዚህ ላይ የሚያጠነጥን ዘገባ ይዘናል …..
….በውጪ ዘገባ ደግሞ….
*…..የፊታችን እሁድ ምሽት 12.3ዐ ላይ በኦልድትራፎርድ የላንክሻየሮቹ ታሪካዊ ተቀናቃኞች ማን.ዩናይትድና ሊቨርፑል በኤፍ ኤ ካፑ ሩብ ፍጻሜ ለ213ኛ ጊዜ ይፋጠጣሉ…በኤሪክ ቴንሃግና የርገን ክሎፕ ፍጥጫ ዙሪያ የምንለው አለ….
*……መድፈኞቹ ሲያጠቁ ብቻ ሳይሆን ሲከላከሉም ጠንክረዋል…ስለ አርሰናል ሌላኛው ገጽ ያዘጋጀነው ዘገባን ይዘናል…..
*….. የተቆጠሩበት ግቦች ያን ያህል የሚታሰበውን
ያህል ባይሆንም ማን.ዩናይትድ ላይ ግን ብዙ ይሞከራል…በዚህ ዙሪያ መረጄዎችን አካተናል….
*….የአርሰናሉ ተከላካይ ቤን ኋይት ከእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ራሱን አግልሏል….ውሳኔው ቋሚ ወይስ ጊዜያዊ ..?…የመድፈኞቹ ብርታት ስለሆነውና በክለቡ
አይነኬ ተጨዋች ስለተባለው ዴክላን ራይስ የምንላችሁ አለ….
*…. በማን.ሲቲ ያልተሳካላቸው ተጨዋቾች አሉ..
እንደዚሁም ምክትል ሆነው ከሰሩ አሰልጣኞች አንዳንዶች ብቻ ተሳክቶላቸዋል …በዚህ ዙሪያ የሚያተኩር መረጃዎችን አካተናል….
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…