በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ ዘገባችን ከአራተኛ ሊግ የሁለት አመት ቆይታ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያደገው ወጣት ኢትዮጵያ ቡናን እየጠቀመ ነው.. ከአዶላ በዩ የወርቅ ምርት መሬት ብቅ ብሎ በስፖርቱ የቦታዋ አምባሳደር ነኝ የሚለው የቡናማዎቹ አንተነህ ተፈራ ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ ከግል ክብር ይልቅ የኢትዮጵያ ቡና ክብር ይቀድምብኛል ሲል ተናግሯል…. ተጨዋቹ ለአቡበከር ናስር ያለውን ክብር የገለጸ ሲሆን “እኔ ገና ነኝ ጊዜ ያስፈልገኛል ከአቡበከር ናስር ጋር አልነጻጸርም” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል…ቃለምልልሱን ይዘናል….
*….ዋሊያዎቹ ረቡዕ ምሽት ያደረጉት ልምምድ ላይ አሰልጣኙ ገብረመድህን ሃይሌ አልተገኘም ምክንያቱ ደግሞ ድሬዳዋ ያለውን የዋና ቡድኑን የኢትዮጵያ መድን ልምምድ ለመምራት ሲል ነበር ተብሏል… በዚህ ላይ መረጃ ይዘናል
….በውጪ ዘገባ ደግሞ….
*….ሊቨርፑሎች አዲስ ዘመን ሊጀምሩ የግድ ሆኖባቸዋል… ያለ የርገን ክሎፕ አዲሱን የውድድር አመት የመጋፈጥ ፈተና ውስጥ ገብተዋል…ስለ አዲሱ የቀዮቹ ዘመን የምንላችሁ አለ…..
*….ሜሰን ማውንት ከጉዳት ተመልሷል…ማን.ዩናይትድ ተጨዋቹን እንዴት ይጠቀመው…? የኮቤ ማይኖ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ጉዞ እንዲሁም ዩናይትድ ስለተሳሳተባቸው ተጨዋቾች የምንላችሁ አለ….
*….የቶተንሃሙ አሰልጣኝ ፖስቴኮጎሉ “አራተኛ ሆኖ ከመጨረስ የቡድን እድገት ይቀድማል” ማለታቸው አነጋጋሪ ሆኗል…በዚህ ዙሪያ መረጃዎችን ይዘናል…
*…በባርሴሎናም በአትሌቲኮም አልተፈለገም…መስቀለኛ መንገድ ላይ ስለቆመው ዣኦ ፊሊክስ የምንለው አለ….
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…