….የሊግ ጉዞ ቀጥሏል …..
በየሳምንቱ ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃው ሊግ ጋዜጣ በነገው ዕለት ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችን አካትታ እጅዎ ትገባለች….
በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ ዘገባችን ዋሊያዎቹ ከሌሴቶ ብሄራዊ ቡድን ጋር ለነበረባቸው ጨዋታ ከካይሮ ወደ አዲስ አበባ የመጣው አቤል ያለው እንግዳችን ነው …አቤል ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ በርግጠኝነት የምናገረው በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ መጫወት የሚችሉ ተጨዋቾች እንዳሉን ነው” ሲል ተናግሯል…. ቃለምልልሱን ይዘናል….
*…. በ7ኛው የመላው አፍሪካ ውድድር በቦክስ የብር ሜዳሊያ ያመጣው ኮማንደር ጸጋስላሴ አረጋዊ
/ኮሮኮንች/ ” ኢትዮጵያ የምትታወቀው በአትሌቲክስና ቦክስ ስፖርቶች ቢሆንም እግርኳስ ላይ ግን ገንዘቡን እንደ አሲድ እየበሉት ነው ” ሲል ጠንካራ ትችት ሰንዝሯል….
መረጃውን ይዘናል…
….በውጪ ዘገባ ደግሞ….
*…. በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የማን.ሲቲና አርሰናል ጨዋታ እሁድ ምሽት 12.30 ላይ በኢትሃድ ይካሄዳል…እዚህ ሜዳ ላይ ካሸነፉ የቆዩት አርሰናሎች ለጋርዲዮላ ቡድን ምላሽ ይኖራቸው ይሆን..? በጨዋታው ዙሪያ መረጃዎችን ይዘናል……
*….ማን.ዩናይትድ የካሲሚሮ ቦታን እንዴት ይሸፍን..? በብራዚላዊው እንቆቅልሽ ዙሪያ የምንላችሁ አለ..
*…..ተደጋጋሚ የዘረኝነት ጥቃት የደረሰበት ብራዚላዊው ቪኒሺየስ ጁኒየር ዘረኝነትን ለመዋጋት በጋራ እንቁም ሲል ጥሪ አድርጓል…በዚህ ዙሪያ መረጃዎችን አካተናል…
*…..ፔፕ ጋርዲዮላ ሀሰተኛ 9 ቁጥርን መጠቀም ይወዳል ይሉታል …ስለ ስፔናዊው ልክፍት የምንላችሁ ነገር አለ…
*…በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እየመሩ ቆይተው ባለቀ ሰአት የተንሸራተቱ ክለቦች አሉ … ለዛሬም መለስ ብለን ተንሸራታች ክለቦችን እናስታውሳችኋለን…
*….ስለ ኒኮላ ጃክሰን ቸልሲና ስለ ቀድሞ የሊቨርፑል አምበል ኤንደርሰን ረጅም ጉዞ የሚገልጽ መረጃም አካተናል….
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…