በነገው ዕትም በሀገር ውስጥ ዘገባችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዋንጫ ተፋላሚ የሆነው የመቻሉ በረከት ደስታ እንግዳችን ነው… ስለመቻል ጥንካሬ የሚያወራው ተጨዋቹ የዛሬ አመት ላለመውረድ ዘንድሮ ደግሞ ለዋንጫ መጫወታችን ለውጣችንን ያሳያል ሲል ይናገራል…..” ከእኛና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውጪ ለዋንጫ የሚፎካከር ቡድን የለም” የሚለው በረከት
“ዘንድሮ በተለይ በተሳሳተ የዳኛ ውሳኔ እየተጎዳን ነው” ሲል ቅሬታውን ገልጿል…..ቃለ ምልልሱን ይዘናል…..
*….. በሀምበሪቾ ዱራሜና በኢትዮጵያ መድን የተጨዋቾች ማህበርና ፌዴሬሽኑ እየሞገቱ ነው ….
በሁለቱ ዙሪያ የማያጠነጥን መረጃዎችን ይዘናል…..
*……ከውጪ ዘገባ ደግሞ ………
*…… የአውሮፓ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ የዋንጫ ጨዋታ ነገ ምሽት በዌምብሌይ ቧ ይካሄዳል …ዶርትሙንድ ለሁለተኛ ጊዜ ሪያል ማድሪድ ለ15ኛ ጊዜ ዋንጫውን ለማንሳት ስለሚፋለሙበት ፍልሚያ የምንላችሁ አለ…
*….. ከአሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖሺቲኖ ጋር የተለያየው ቸልሲ ኢንዞ ማሬስካን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል….ስለኚሁ አዲሱ አሰልጣኝ መረጃ ይዘናል…
*…… በሳንቲያጎ በርናባው የደመቀው ጀርመናዊው ኮከብ ቶኒ ክሩስ በይፋ ተሰናብቷል….ስለዚህ ኮከብ የተጠያከረ መረጃ ይዘናል….
*…..ዩሪያን ቲምበር በጉዳት አርሰናልን ባድጠቅምም አሁን ከጉዳት መልስ ተስፋ ተጥሎበታል ….ስለዚህ ሆላንዳዊ መረጃ ይዘናል….
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…